መንፈሳዊ መርሐ ግብር የሚተላለልፍት #ልዳ ሚዲያ Leda Media በYouTube እና #ልዳ ዩቱብ Leda በፊስቡክ Page
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። #ታኅሣሥ ፲፫ (13) #እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለፈታሔ_ማሕፀን_ለቅዱስ_ሩፋኤል ለቅዳሴ ቤቱና ተአምር ላደረገበት ዓመታዊ መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላም አደረሰን #የመላእክት_አለቃ_የከበረ_መልአክ_የቅዱስ_የሩፋኤል_የቅዳሴ_ቤት_ክብርና_ያደረገው_ተአምር፦ ከእስክድርያ ውጭ በደሴት የታነፀች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸባት የከበረችበት፦ ይህም እንዲህ ነው ሀብታም ሴት ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ መጥታ ሳለ ከእርሷ ጋርም ብዙ ሰው ነበር። ከባሏም የወረሰችው ብዙ ገንዘብ አላት በሊቀ ጳጳሳቱ ቤት አንጻር ያለውን ኮረብታ አስቆፈረች በጥቅምት ወር ዐሥራ ስምንት ቀን እንደጻፍን የወርቅ መዝገብ ተገለጠ። በዚያም ወርቅ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትን አነፀ ከእርሳቸውም አንዲቱ የመላእክት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል በስሙ የታነፀች ይህች ናት። ሥራዋንም በፈጸመ ጊዜ እንደዛሬው በዚች ቀን አከበራት። ብዙ ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈጽማ ተናወጸች ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና። የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው። ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔርም በከበረ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ስም ጮኹ ያን ጊዜ ይህ የከበረ ቅዱስ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ እንዲህ አለው "እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም"። አንበሪውም ጸጥ ብሎ ቆመ አልታወከም በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጳጒሜን 3 ስንክሳር#ቅዱስ_ሩፋኤል#ልዳ_ሚዲያ#ቤተ_ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 hour ago (edited) | [YT] | 17
View 0 replies
#አባ_ሣሙኤል_ዘዋልድባ#በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሳሙኤል ዘዋልድባ ዓመታዊ ዕእረፍት ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን ፃድቁ #አባ_ሳሙኤል አባቱ እስጢፋኖስ እናቱ አመተ ማርያም በአክሱም አካባቢ በ14 ኛው ክ/ዘመን ተወለደ ዕድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ቅዱሳት መፅሐፍትን ተምሯል ከወላጆቹ ዕረፍት በኋላ ወደ ደብረ በንኮል ገዳም በመሄድ ሥርዓተ ምንኩስናን ከአባ አድኃኒ እጅ በመቀበል በገዳሙ ውስጥ መነኮሳቱን በትጋት ያገለግል ጀመርዘመዶቹ ወደ እርሱ እየመጡ በአስቸገሩት ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ #በፆምና_በስግደት በመቆም ተጋደለ ከዚያም ወደ ሌላ በርሃ ሄዶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ምንም ምን ሳይቀምስ በፆም ኖረ በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ ተከዜ በደረሰበት ወቅት የተከዜ ወንዝ ሞልቶ የማያሻግረው ሲሆን በትእምርተ መስቀል ባርኮ በአንድ እጁ መጽሐፍ በሌላ እጁ መብራት እሳት ይዞ ገብቶ #መብራቱ_ሳይጠፋ_መፅሐፉ_ሳይበሰብስ ተሻግሮ ዋልድባ ገብቷልአባታችን #የዋልድባ_ገዳም መሥራች በመሆኑም "አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ" በመባል ይታወቃል በዚህም ገዳም ገድሞ ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማረ በፆም በፀሎት ፀንቶ ሰውነቱን በመግረፍ መዝሙረ ዳዊትን በቀን 5 ጊዜ በማድረስ ከእመቤታችን ፍቅር የተነሣ ውዳሴ ማርያምን እና ቅዳሴ ማርያምን በቀን 64 ጊዜ በዕድሜዋ ልክ ይፀልየው ነበርዋልድባ ገዳምን በእጁ እንደ መሶብ ይዞ አስባርኳታል ከሰማይም #የወርቅ_መስቀል ወርዶለታል በተጋድሎው ጽኑዕ ስለነበር ሰይጣን በሚያስፈሩ አራዊት እየተመሰለ ይፈታተነው ነበር፡፡ብዙ አናብስት እየተከተሉ ግማሾቹ ለመፅሐፍት መያዣ ግማሾቹ ለዕቃ መያዣ ሆነው #የአባ_ሳሙኤልን የእግራቸውን አቧራ እንደ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብስት እየላሱ ይኖሩ ነበርበቅዳሴ ጊዜ #ቅዳሴ_ማርያምን ሲቀድሱ ከመሬት ሦስት ክንድ ከፍ ይላሉ በዚህም በውኃ ላይ ቅዳሴ ማርያምን ደግመው ቢባርኩት ኅብስት ሆኖላቸዋል ለዚህም መታሰቢያ እመቤታችን #ለአባ_ሳሙኤል የሚያበራ ዕንቁ እና ንጹሕ ዕጣን ሰጠችው ከዚህም በተጨማሪ በአርያም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ያጥን ነበር የብቃት ደረጃ ላይ ስለደረሱ አባ ሳሙኤል በዋልድባ አባ ብንያም በግብፅ አባ አንበስ በሐዘሎ ሆነው ይተያዩ ነበርእነዚህ ሦስቱ ቅዱሳን ተቀጣጥረው ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ወደ ምድረ ከብድ በሔዱበት ጊዜ የተጫኑባቸውን አናብስት የአቡነ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ አናብስት ሰባብረው በሏቸውአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ፈጣሪ ያላዘዘላችሁን ለምን በላችሁ ብሎ እንዲተፏቸው አዝዞ ሕያዋን አድርጎላቸዋል ከዚህ በኋላ ቡራኬ ተቀብለው መንፈሳዊ ጨዋታ ተጨዋውተው #በአናብስታቸው ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል፡ የአባ ሳሙኤል ዕረፍታቸው በተቃረበ ጊዜ #ቅዱስ_ሚካኤል በክንፉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ወስዶ #ከእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አቀረባቸው፡፡ አምላካችን #እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶላቸው ከሰማይ ተመልሰው በታኅሣሥ 12 ቀን #በክብር_አርፈዋል ፍልሰተ ዐፅማቸው ከብዙ ጊዜ በኋላ ከዋልድባ ወደ ደብረ ዐባይ መስከረም 6 ቀን ተዛዉሯልየፃድቁ አባታችን #አባ_ሣሙኤል ዘዋልድባ ረድኤት በረከታቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን ምልጃ ፀሎታቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን "አሜን"#ልዳ_ሚዲያ#ቤተ_ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 day ago | [YT] | 159
View 8 replies
#ቅዱስ_ሚካኤል " ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።" ዳን. 10፥21 የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይ ጭምርም ነው ቅዱስ ሚካኤሌ ለእኛ ለሰዎች አማላጅ ሲሆን ለቅዱሳን፣ ጻድቃን ሰማዕታት ደግሞ አጋዣቸው ነው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል፥ ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ዘወትር የሚቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃበሰማይም ለሚኖሩ ሀይሎች ሁሉ አለቃቸው የሆነ ነውየሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ምልጃው ተራዳኢነቱ አይለየን#ልዳ_ሚዲያ#ቤተ_ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 day ago | [YT] | 71
View 3 replies
#ማኅሌታዊዉ_ቅዱስ_ያሬድ #በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት #ማህሌታዊዉ_ቅዱስ_ያሬድ ዜማዎቹን ለቅድስት ቤተክርስቲያን ላዋለበት ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን #ቅዱስ_ያሬድ አንደበቱ ጣፋጭ ልቡናው የቅድስና ማሕደር ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈፀም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱቅዱስ ያሬድ #ለኢትዮዽያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ሙሉ አካሏ ነው ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ #ቅዱስ_ያሬድ በሕፃንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር ትምሕርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም በጥበበ #እግዚአብሔር እንጂ ምን ትምሕርት ባይገባው ፆምና ጸሎትን ያዘወትር ነበርልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምሕሩ ኮብልሎ #ማይ_ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና ከዚህ በኋላ #ቅዱስ_ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው #ካህኑ_ቅዱስ_ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ወሰነ በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት #ሦስት_መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት ድንገትም ነጥቀው ወደ #ሰማያት ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር ልዩ #ምስጋናና ልዩ #ዜማን አዳመጠ ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ፅዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ #ቅዱስ_ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላታል #ቅዱስ_ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት አምስት ያሕል መጻሕፍትን ፅፏል በጣና ቂርቆስ በዙር አንባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋት እንደ #መላእክት በተባሕትዎ ኑሯል በተወለደ በ71 አመቱ ተሰዉሯል የአባታችን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል የማኅሌታይ #ቅዱስ_ያሬድ ረድኤትና በረከት ለሁላችንም ይድረሰን የቅዱሳን #አበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" #ቅዱስ_ያሬድ #ልዳ_ሚዲያ#ቤተ_ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
2 days ago | [YT] | 197
View 2 replies
#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ #በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ዓመታዊ የልደት መታሠቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን #እግዚአብሔር በፃድቁ እንደተገለጠ እወቁ" መዝ፤4፣3 #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው #መላከ እናታቸው #ወለተ_ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው በተወለዱ ዕለት ተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ በአንድነት በሶስትነት ለሚመሰገን ለአጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ #ስብሐት_ለአብ #ስብሐት_ለወልድ #ስብሐት_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው አመስግነዋልየስማቸው ትርጓሜ #የአብ_የወልድ_የመንፈስ_ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ_እስትንፋስ ማለት ነው ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቦናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍት ቃላትን ብሉያትንና ሐዲሳትን ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋልበተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ #እግዚአብሔር በፀለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን ገብተዋልሦስት ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን በማውጣት አገልግለዋልአባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ #ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋልአቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው ወይን ተክለው ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን #ለቤተ_ክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሰዋልአባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸውጌታም #በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል ሁሉንም #የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትንም ተሳልመዋልየአባታችን #የፃድቁ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ፀሎትና ቃል ኪዳን ከኛ ጋር ይሁን #የአበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን "አሜን" #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ #ልዳ_ሚዲያ#ቤተ_ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
3 days ago | [YT] | 273
View 4 replies
#ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ኪሮስ የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ የልደት መታሠቢያ ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ #አቡነ_ኪሮስ አባታቸው ንጉስ ዮናስ እናታቸው እንስራ ይባላሉ እሊህም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው ሀገራቸው ሮም ሲሆን በታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ የመጀመሪያ ስማቸው ዲላሶር ይባል ነበርበኋላ አባታቸዉ ከሞቱ በኋላ ሀብት ንብረታቸዉን ተካፍለዉ ለድሆች ከመፀወቱ በሑዋላ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገቡበ17 አመታቸው ስርአተ ምንኩስናን ተምረው ከአባ በቡነዳ እጅ ስርአተ ምንኩስናን ተቀበሉ ከዚህ በሁዋላ በፆምና በፀሎት ተወስነው ኖሩስለ አለም መከራ ለ 40 ዘመን ተኝተው ሲፀልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላዕክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡርን ቃል ሰምቶ ወድቋልና ጌታም ድምፁን ያሰማኝ አሏቸው በኋላም ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይቷቸው በመጨረሻም ጌታችን ቃል ኪዳን ሰቷቸዋልቃል ኪዳናቸውም መካኖችን ልጅ የሌላቸው #ገድላቸውንአቅፈው ቢያለቅሱ #ፀበሉን ቢጠጡ ስምሕን ቢጠሩ የመካኒቱን ማሕፀን እከፍታለሁ ህፃናት የሚሞትባቸው #እንዳይሞትባቸው አደርጋለሁ በንፁህ ገንዘቡ ቂም እና በቀልን ሳይዝ በሕግ በስጋ ወደሙ ለፀና ሰው በስምህ በተሰራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ እሰጠዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል ከዚህም በኋላ በተወለዱ በ 270 አመታቸው ሐምሌ 8 ቀን አርፈዋል #የፃድቁ_አቡነ_ኪሮስ ረድኤት በረከታቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን የቅዱሳን #አበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን "አሜን" #አቡነ_ኪሮስ #ልዳ_ሚዲያ#ቤተ_ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
5 days ago | [YT] | 212
አጋእዝተ አለም ቅድስት ሥላሴ ከክፉዉ ሁሉ ይጠብቁን #ቅድስት_ሥላሴ #ልዳ_ሚዲያ#ቤተ_ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
5 days ago | [YT] | 187
#ቅድስት_አርሴማ❖ ታኅሣሥ 6 ክብረ በዓሏ የኾነው የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ❖❖✔💥 በ290 ዓ.ም. በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ስላረፈችው ስለ ቅድስት አርሴማ በአርሜንያ Հռիփսիմէተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች። 💥 እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡ ❖✔💥 እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡❖✔💥 ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡ 💥 ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡ ❖✔💥 የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡❖✔💥 ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡ ❖✔💥 ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ።💥 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም። 💥 ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚልስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች።💥 አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በስሟ በተሰየመው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች ካለ ካታኮምብ ግበበ ምድር በአርመንያ አለ፡፡ 💥 በአርመን ያለው የቅዱስ አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት እውቅና አግኝቶ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም.ተመዝግቧል።❖✔💥 በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ፤ በሰሜን አሜሪካ ቨርጂንያ መካነ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ፨❖✔💥 ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦❖✔💥 ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡-✍️ “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታእንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ”(በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡❖✔💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦✍️“ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ ዘፈጸመት ገድላ በጻማ ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨❖✔💥 እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨❖✔💥 “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥበምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥአመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥአሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ”(በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች (መግረፊያዎች) ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ) ይላል።💥እኔም ከበረከቷ ለመሳተፍ ይህንን ጻፍኩ። እናንተም ከበረከቷ ትሳተፉ ዘንድ በአስተያየት መስጫው ላይ ደስ ያላችሁን ሰላምታና ውዳሴ አቅርቡላት።ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ #ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago | [YT] | 234
View 1 reply
#በዓታ_ለማርያም[ታኅሣሥ 3 የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ድንቅ ታሪክና የ8 ሊቃውንት ትምህርት]♥❖♥ ኢያቄምና ሐና ቃል ኪዳናቸውን ለመፈጸም ዘመዶቻቸውን ባልንጀሮቻቸውን ከነልጆቻቸው በመጥራት ሕፃን ልጃቸውን እመቤታችንን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ ያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ በካህናቱ ታጅቦ የምስጋና ዝማሬን ከልኡካኑ ጋር እያሰማ እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ። ♥❖♥ በዚያም ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወደሚገባበት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ሲኖሩ በየደረጃዎቹም መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ ሲደረስባቸው ከሚጸለዩት የዳዊት መዝሙራት ውስጥ መዝ ፻፲፰(፻፲፱)-፻፴፪ (፻፴፫) የሚገኙ ሲኾኑ እነዚኽንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አጥኚዎች “Psalms of Ascent” (የመውጣት መዝሙራት) ይሏቸዋል::♥❖♥ እናትና አባቷም ሊቀ ካህናቱን ካለበት ቅዱስ ቦታ ወደነርሱ እስኪመጣ ለመቆየት ልጃቸው ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯትም ርሷ ግን በድንቅ አምላካዊ ሥራ መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ የሦስት ዓመቷ እመቤታችን ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት በእጅጉ ወደተቀደሰው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወዳለበት ስፍራ ኼደች ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት።♥❖♥ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለሊቀ ካህናቱ የሰው ዘርን በመላ ወደ ገነት የሚያስገባ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የእግዚአብሔር ልጅን የምትወልደው ርሷ እንደኾነች ገልጾለት ቦታዋም በጣም የተቀደሰውና ርሱ መሥዋዕት ለማቅረብ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገባበት ከርሱ በቀር ማንም ሰው የማይገባበት ቅድስት ቅዱሳን ውስጥ መኾኑን ገልጾለታል ፡፡ ♥❖♥ ርሱም ይኽነን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ይኽቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን? ብሎ ሲጨነቅ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብስት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ ፲፮፥፴፩፤ ፩ነገ ፲፱፥፮፤ ዕዝ. ሱቱ. ፲፫፥፴፰-፵፩):: ♥❖♥ ከዚያም “ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት ወጸለላ በአክናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብእሲ ወወሀባ ወመጠዋ ወዐርገ ውስተ ሰማይ” ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊን፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኽል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡♥❖♥ ስላዩትና ስለተደረገው ነገር ኹሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አማናዊት የአምላክ መቅደስ የአካላዊ ቃል ታቦት እመቤታችንን ምሳሌዋ ወደሚኾነው ቤተ መቅደስ ታኅሣሥ ፫ በሦስት ዓመቷ አስገብተዋታል፤ ከዚያም ኢያቄምና ሐና ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡♥♥♥ የቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ መቅደስ ሕይወት በእጅጉ አስደናቂ ሲኾን የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት (Holy Tradition) እንደሚያስረዳን ቤተ መቅደስ በኖረችባቸው 12 ዓመታት የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለቤተ መቅደስ የሚያስፈልገውን ነገር በእጆቿ እየሠራች በፍጹም ንጽሕና ቅድስና ኾና እግዚአብሔርን በማመስገን መላእክት እያገለገሏት ኖራለች፡፡ ይኽነን በቤተ መቅደስ የነበራትን ቆይታ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በጥልቀት ጽፈዋል እነሆ የሊቃውንቱ ቃል፦፩) [አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ] “የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምናአመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐናወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስናምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መናፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”(ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል)♥♥“ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስበድንግልና ማርያም ስርጉተ ሥጋ ወነፍስተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስእምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ”(በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንዳጌጠች ታቦት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ያጌጥሽ ማርያም፤ ቀንሞስ ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቱዎች ኢያቄምና ሐና ለጳጦስ ምሳሌ የኾንሽ አንቺን ከአስገኙሽ ዘንድ በሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ የመኖር ተአምርን አሳየሽ) ++++++++++++++፪) [ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም]♥♥♥ “ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ…” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ) +++++++++++++++++++፫) [በ፭፻፭ (505) ዓ.ም የተወለደው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን]♥“አንቲ ውእቱ ንጽሕት እም ንጹሓን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ…” (ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የኾንሽ አንቺ ነሽ፤ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ በወርቅ እንደተጌጠና ዋጋው ብዙ በኾነ በሚያበራ ዕንቊ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ፤ እንዲኽ ኾነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ፤ መላእክት ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር፤ መላእክት እየጐበኙሽ እንዲኽ ዐሥራ ኹለት ዓመት ኖርሽ፤ መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር፤ ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር)♥ “እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ጸቃውዕ ይውሕዝ እምከናፍሪሃ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ፤ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ” (መላእክት እመቤታችንን እኅታችን ይሏታል፤ በክንፋቸው ይጋርዷታል፤ በማር ወለላ የተመሰለ የእግዚአብሔር ቃል ከከንፈሮቿ ይፈስሳል፤ ጒንጮቿ እንደ ሮማን ቅርፍት ናቸው፤ ልዑል ወደዳት፤ ዳዊት በመዝሙሩ አመሰገናት፤ በቤተ መቅደስ ተቀበሏት) (ቅዱስ ያሬድ፤ መጽሐፈ ድጓ)♥ “ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዝእ ኀረያ ዕፀ ጳጦስ ሰመያ በቤተ መቅደስ ተወክፋ ዘካርያስ ወኲሎሙ ቅዱሳን ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ” (ጌታ የመረጠሽ ማርያም ሆይ ለምኝልን፤ ዕፀ ጳጦስ ተብላ የተጠራችውን እመቤታችን ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ተቀበላት፤ ኹላቸውም ቅዱሳን ዐዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል) ♥ “ጠባብ ወትሕት በቤተ መቅደስ ዘልህቀት ወለተ ዳዊት ቀጸበቶ በትእምርት ለዘወረደ እመልዕልት”(ብልኅና ትሕትናን የተላበሰችው በቤተ መቅደስ ያደገችው የዳዊት ልጅ እመቤታችን ከላይ የወረደውን በምልክት ጠራችው) ይላል ++++++++++++++፬) [ከ፫፻፳-፬፻፫ (320-403) ዓ.ም የነበረው የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ]♥ “She was brave and dignifified in all her action…” (እመቤታችን በኹሉም ርምጃዎቿ ጐበዝና የተከበረች ነበረች፤ የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበር፤ በጣም ዝግጁ ኾና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት፤ ለእያንዳንዱ ሰው አክብሮትና ክብር (ሰላምታ) ትሰጣለች፤ ቁመቷ መኻከለኛ ሲኾን አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ እንደነበር ይናገራሉ፤ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሀት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጯጯኽ ትናገራለች፤ በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም፤ መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጒሯ ቀይማ ነው፤ ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የኾኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ኾኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት-አረንጓዴ ይመስላል፤ የዐይኖቿ ቅንድብ (ሽፋሽፍት) ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው፤ አፍንጫዋም ረዥም፣ ከናፍሮቿ ቀይና ምሉእ ሲኾኑ በቃሎቿ ጣፋጭነት የተመላባቸው ነበሩ፤ ፊቷ ክብ ሳይኾን ግን እንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው፤ እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ፤ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትኾን ግድ የለሽነት ፈጽሞ ጨርሶ የለባትም ነበር፤ የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር፤ ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው (ማለትም በቤት ድር የተሠሩ) ልብሶችን ትለብስ ነበር፤ ይኽም በእጅጉ አብሯት የሚኼደው አለባበስና ይኽ እውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አኹን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው፤ ለማጠቃለል ያኽል በመንገዶቿ ኹሉ በጌታ ስጦታ የተመላች ነበረች) +++++++++++፭) [ከ፫፻፲፭-፫፻፹፮ (315-386) ዓ.ም ድረስ የነበረው የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ]♥♥♥ “They (Joachim and Anna) were in the habit of visiting their daughter once each month,…’’ (እነርሱ (ኢያቄምና ሐና) በወር አንድ ጊዜ ልጃቸውን የመጐብኘት ልምድ ነበራቸው፤ ለርሷ የሚያስፈልጋትን ነገር ይዘው ይመጡ ነበር፤ እናም ትንሿ ድንግል ልጃቸው ከርሷ በዕድሜ ከፍ ከሚሉ ደናግል ጋር በቤተ መቅደስ ታገለግል ነበር፤ እነርሱም በእጆቿ እንዴት መሥራት እንደምትችል ያስተምሯት ነበር፤ ርሷም ዐዋቂ በኾነች ጊዜ በራሷ ወደ ቤተ መቅደሱ ዐደባባይ ስትኼድ ከካህናትና ከአባቷ በቀር ማንም ወንድ ከቶ አይቷት አያውቅም…ትንሿ ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ነበረች፤ የመላእክት አለቃው ገብርኤል በጣፋጭ መዐዛው ወደ ርሷ ቀረባት…የርሷ ውበቷ ምንም ወሰን አልነበረውም፤ ቤተ መቅደሱም ከጣፋጭ መዐዛዋ የተነሣ በመላእክት ይመላ ነበር፤ ለንግግሯ ሲሉ ብቻ ይጐበኟት ነበረ) ++++++++++++++++፮) [በ፪፻፶፮ (256) ዓ.ም የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ የነበረው ዲሜጥሮስ]♥♥♥ “At the moment when her mother Anna set her upon her feet, inside the door of the temple…” (እናቷ ሐና በካህናቱ ፊት በቤተ መቅደሱ በር ላይ ርሷን በእግሯ ባኖረቻት ጊዜ በራሷ ለጌታ መሥዋዕት ወደሚቀርብበት ወደ መሠዊያዉ መጋረጃ ወደ ቤተ መቅደስ እስክትደርስ ድረስ ኼደች፤ ከገባችም በኋላ ለመውጣት አልተመለሰችም በልቡናዋም የቤተሰቦቿ ሐሳብና ምድራዊ ነገራትን ከቶ አላሰበችም…እናም ባደገችና ስምንትና ዐሥር ዓመት በመላትም ጊዜ ለካህናቱ ኹሉ አብነት (ምሳሌ) ነበረች ርሷንም ለማየት ይፈሩ ነበር፤ መላ ሰውነቷ ንጹሕ ነበር ልቡናዋም በጌታ የጸና ነው፤በሥጋዋም በነፍሷም ንጽሕት ናት፤ ፊቷንም ከቤተ መቅደሱ በር ውጪ በፍጹም አላዞረችም፤ እንግዳ ሰውንም ከቶ አላየችም የወጣት ሰው ፊትን ለመመልከት ፊቷን ከቶ አላዞረችም፤ በቅድስና እግዚአብሔርን በማገልገል ለቤተ መቅደስ በመላላክ ኖረች እንጂ፤ ልብሷ ያማረ ዕጥፋቱ በማኅተሟ ላይ ወደ ታች የወረደ ሲኾን የራሷ መሸፈኛም እስከ ዐይኖቿ ይደርሳል…በዐይኖቿ ላይ በጭራሽ መዋቢያ ቀለም አልተጠቀመችም፤ በጉንጮቿ ላይ ምንም ዐይነት የማጌጫ አበባ አላኖረችም፤ በእግሮቿ ላይ መጫሚያ ሰንደሎች አላደረገችም፤ በክንዶቿና በእጆቿ ላይ አልቦ ወይም አምባር ወይም ጌጣጌጥ አላደረገችም ነበር፤ ከልክ ያለፈ ምግብ በጭራሽ ፈልጋ አታውቅም፤ በከተማው የገበያ ስፍራ ውስጥ በጭራሽ ተጉዛ አታውቅም፤ ለዚኽ ዓለም ሥራዎች በጭራሽ ጉጉት ዐድሮባት አያውቅም) +++++++++++++፯) [ከ፫፻፸፮-፬፻፵፬ (376-444) ዓ.ም የነበረው እስክንድርያዊዉ ቅዱስ ቄርሎስ]♥♥♥ “Come, O all ye women who desire virginity…” (ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን እናት የኾነችውን የማርያምን ምሳሌ ተከተሉ፤ የርሷንም መንገድ መናኛ ምግብ መብላቷንና መሬት ላይ መተኛቷን ዐስቡ፤ ለዚኽ ዓለም ነገሮች ምንም ዐይነት ጉጉት የላትምና የርሷ ስምም ኹልጊዜም በካህናት አፍ ውስጥ ነበር፤ ሰውነቷን በጭራሽ በሕዝብ መታጠቢያ ውስጥ ታጥባ አታውቅም፤ ራሷን በፍጹም በመዋቢያ የፊት ቀለም፣ በዐይን ኩልና በቅባት በጭራሽ አስውባ አታውቅም፤ በጣም ያጌጠ ልብስ እንደሚወድዱ ኹሉም በዘመኗ የነበሩ ሴቶች በደማቅ ባለቀለም ልብስ በጭራሽ አስጌጣ አታውቅም፤ በጭራሽ የወይንን ጣዕም ቀምሳ አታውቅም፤ ኹልጊዜም ዓለማትን የፈጠረ ፈጣሪዋን ትጠብቅ ስለነበር ፊቷን ወደ ምሥራቅ አዙራ ትቀመጥ ነበር፤ ከእናቷና ከአባቷ በስተቀር ከማንም ጋር ተገናኝታና አውርታ አታውቅም) +++++++++++++++++++፰) [ ከ፪፻፺፮-፫፻፸፫ (296-373) ዓ.ም የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ]♥♥♥ “Mary was pure virgin, with a harmonius disposition…” (ማርያም ንጽሕት ድንግል ስትኾን በጣም ጥሩ አቋም የነበራትና መልካም ሥራዎችን የምትወድድ ነበረች፤ በወንዶች መታየትን ፈጽማ አትፈልግም ነበር፤ ግን እግዚአብሔርን እንዲመረምራት ጠይቃዋለች፤ ያለማቋረጥ በቤቱ ውስጥ ቆይታለች፤ ከጨዋታ የራቀ (የመናኝ) ሰውን ኑሮ ትኖር የነበረ ሲኾን ማር ከምትሰጥ ንብ ጋር ትመሳሰላለች፤ በእጆቿ ከሠራቻቸው ሥራዎች የምታገኘውን ገንዘብ ለድኾች ታከፋፍላለች፤ በብቸኝነት ኹለት ነገራትን እንዲያደርግላት ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች፤ ይኸውም መጥፎ ሐሳብ በልቧ ውስጥ እንዳይሠርጽና ልቧ በጭራሽ ከፍቅር አምላካዊ እየቀዘቀዘ እንዳይኼድ ነበረ፤ ንግግሯ የተረጋጋ እና ድምፆቿም ዝግ ያሉ ናቸው፤ በየቀኑም መንፈሳዊ ርምጃ (ብቃታዊ መሻሻል ዕድገት) ማድረግ ትፈልጋለች፤ በየቀኑም ያነን ታደርጋለች፤ በጠዋት ስትነሣም ከዚኽ በፊት አስቀድማ ከሠራቻቸው አስበልጣ ሥራዎቿን ለመሥራት ትፈልጋለች፤ ሞትን ፈጽማ አትፈራም ነበር ይልቁኑ በሐዘን ኹና የመንግሥተ ሰማያት መዠመሪያ (መግቢያ) እንዳላቋረጠች በየቀኑ እያየች በጸሎቷ ታነሣለች) በማለት የደናግል መመኪያነቷን በስፋት ገልጾታል፡፡ምንጭ፡- ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፤ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1 እና ክፍል 2 ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ)[የአማናዊት መቅደስ የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፤ መልካም በዓል፡፡][ጸሎቷ እንዲጠብቀን በረከቷ እንዲትረፈረፍልን ወደ ቤተ መቅደስ መግባቷን አስመልክታችሁ እጅግ አብዝተን የምንወዳት የፈጣሪያችን የክርስቶስ እናትን አመስግኗት]✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ#ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago | [YT] | 240
ታህሳስ 1 #ነብዩ_ኤልያስ " ኤልያስ እንደኛ የሆነ ሰው ነበረ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ፀለየ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም ሁለተኛም ፀለየ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች ያዕ ፭÷፲፯-፲፰ "በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህችም በታኅሣሥ አንድ ቀን በእስራኤል ፊት ነቢይ #ኤልያስ የተገለጠበት ነው ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም #ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ #ቶና ነው ስለርሱም እንዲህ ተነገረ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ #በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው እነርሱም ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን ወይም እስራኤልን በሰይፍና በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን ተባባሉ በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ #ነገሥት ተጽፎአል ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ #ዮሐንስ #ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግሮአል ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ #በእግዚአብሔር ፊት የሚያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው አለ ከጠላቶቻቸውም ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸዋለች የሚጠሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ #ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ በሰማይ ላይ ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል ምስክርነታቸውንና ትንቢታቸውን ከፈፀሙ በኋላ ከባህር የወጣው አውሬ ከእሳቸው ጋር ይጣላል ድል ነስቶም ይገድላቸዋል አስከሬናቸውንም ፍጥሞ በምትባል በታላቂቱ አገር ያስጥለዋል ይችውም በምሥጢር ሰዶም ግብጽ የተባለች ጌታቸው የተሰቀለባት ናት አስከሬናቸውንም ሕዝብና አሕዛብ በሀገርም ያሉ ነገዶች ሦስት ቀን ተኩል ያዩታል አስከሬናቸውንም በመቃብር ይቀብሩት ዘንድ አያሰናብቱም በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ሞት ደስ ይላቸዋል እርስ በርሳቸውም በደስታ እጅ መንሻ ይሰጣጣሉ እሊህ #ሁለቱ_ነቢያት በምድር በሚኖሩ ሰዎች መከራ አፅንተውባቸዋልና ይላሉ ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ #ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወት መንፈስ መጥታ ታድርባቸዋለች ተነሥተውም በእግራቸው ይቆማሉ በሚያዩዋቸው ላይም ጽኑ ፍርሀት ይሆናል ከወደ ሰማይ ቃል መጥቶ ወደዚህ ውጡ ይላቸዋል ከዚህ በኋላ ጠላቶቻቸው እያዩአቸው በደመና ያርጋሉ በዚያችም ሰዓት ጽኑ መነዋወጥ ይሆናል የዚያችም አገር ዐሥረኛ እጅዋ ይጠፋል በዚያም መነዋወጥ ሰባት ሽህ ሰዎች ይሞታሉ የቀሩት ግን ደንግጠው #የሰማይ_አምላክን ፈጽመው ያመሰግናሉአምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከታላቁ ነብይ #ነብዩ_ኤልያስ ከልደቱ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን" #ነብዩ_ኤልያስ#ልዳ_ሚዲያ#ቤተ_ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago (edited) | [YT] | 120
Load more
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
#ታኅሣሥ ፲፫ (13)
#እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለፈታሔ_ማሕፀን_ለቅዱስ_ሩፋኤል ለቅዳሴ ቤቱና ተአምር ላደረገበት ዓመታዊ መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላም አደረሰን
#የመላእክት_አለቃ_የከበረ_መልአክ_የቅዱስ_የሩፋኤል_የቅዳሴ_ቤት_ክብርና_ያደረገው_ተአምር፦ ከእስክድርያ ውጭ በደሴት የታነፀች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸባት የከበረችበት፦ ይህም እንዲህ ነው ሀብታም ሴት ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ መጥታ ሳለ ከእርሷ ጋርም ብዙ ሰው ነበር። ከባሏም የወረሰችው ብዙ ገንዘብ አላት በሊቀ ጳጳሳቱ ቤት አንጻር ያለውን ኮረብታ አስቆፈረች በጥቅምት ወር ዐሥራ ስምንት ቀን እንደጻፍን የወርቅ መዝገብ ተገለጠ።
በዚያም ወርቅ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትን አነፀ ከእርሳቸውም አንዲቱ የመላእክት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል በስሙ የታነፀች ይህች ናት። ሥራዋንም በፈጸመ ጊዜ እንደዛሬው በዚች ቀን አከበራት። ብዙ ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈጽማ ተናወጸች ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና። የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው። ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔርም በከበረ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ስም ጮኹ ያን ጊዜ ይህ የከበረ ቅዱስ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ እንዲህ አለው "እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም"። አንበሪውም ጸጥ ብሎ ቆመ አልታወከም በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፦ የጳጒሜን 3 ስንክሳር
#ቅዱስ_ሩፋኤል
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 hour ago (edited) | [YT] | 17
View 0 replies
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
#አባ_ሣሙኤል_ዘዋልድባ
#በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሳሙኤል ዘዋልድባ ዓመታዊ ዕእረፍት ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን
ፃድቁ #አባ_ሳሙኤል አባቱ እስጢፋኖስ እናቱ አመተ ማርያም በአክሱም አካባቢ በ14 ኛው ክ/ዘመን ተወለደ ዕድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ቅዱሳት መፅሐፍትን ተምሯል ከወላጆቹ ዕረፍት በኋላ ወደ ደብረ በንኮል ገዳም በመሄድ ሥርዓተ ምንኩስናን ከአባ አድኃኒ እጅ በመቀበል በገዳሙ ውስጥ መነኮሳቱን በትጋት ያገለግል ጀመር
ዘመዶቹ ወደ እርሱ እየመጡ በአስቸገሩት ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ #በፆምና_በስግደት በመቆም ተጋደለ ከዚያም ወደ ሌላ በርሃ ሄዶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ምንም ምን ሳይቀምስ በፆም ኖረ
በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ ተከዜ በደረሰበት ወቅት የተከዜ ወንዝ ሞልቶ የማያሻግረው ሲሆን በትእምርተ መስቀል ባርኮ በአንድ እጁ መጽሐፍ በሌላ እጁ መብራት እሳት ይዞ ገብቶ #መብራቱ_ሳይጠፋ_መፅሐፉ_ሳይበሰብስ ተሻግሮ ዋልድባ ገብቷል
አባታችን #የዋልድባ_ገዳም መሥራች በመሆኑም "አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ" በመባል ይታወቃል በዚህም ገዳም ገድሞ ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማረ በፆም በፀሎት ፀንቶ ሰውነቱን በመግረፍ መዝሙረ ዳዊትን በቀን 5 ጊዜ በማድረስ ከእመቤታችን ፍቅር የተነሣ ውዳሴ ማርያምን እና ቅዳሴ ማርያምን በቀን 64 ጊዜ በዕድሜዋ ልክ ይፀልየው ነበር
ዋልድባ ገዳምን በእጁ እንደ መሶብ ይዞ አስባርኳታል ከሰማይም #የወርቅ_መስቀል ወርዶለታል በተጋድሎው ጽኑዕ ስለነበር ሰይጣን በሚያስፈሩ አራዊት እየተመሰለ ይፈታተነው ነበር፡፡
ብዙ አናብስት እየተከተሉ ግማሾቹ ለመፅሐፍት መያዣ ግማሾቹ ለዕቃ መያዣ ሆነው #የአባ_ሳሙኤልን የእግራቸውን አቧራ እንደ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብስት እየላሱ ይኖሩ ነበር
በቅዳሴ ጊዜ #ቅዳሴ_ማርያምን ሲቀድሱ ከመሬት ሦስት ክንድ ከፍ ይላሉ በዚህም በውኃ ላይ ቅዳሴ ማርያምን ደግመው ቢባርኩት ኅብስት ሆኖላቸዋል
ለዚህም መታሰቢያ እመቤታችን #ለአባ_ሳሙኤል የሚያበራ ዕንቁ እና ንጹሕ ዕጣን ሰጠችው ከዚህም በተጨማሪ በአርያም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ያጥን ነበር የብቃት ደረጃ ላይ ስለደረሱ አባ ሳሙኤል በዋልድባ አባ ብንያም በግብፅ አባ አንበስ በሐዘሎ ሆነው ይተያዩ ነበር
እነዚህ ሦስቱ ቅዱሳን ተቀጣጥረው ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ወደ ምድረ ከብድ በሔዱበት ጊዜ የተጫኑባቸውን አናብስት የአቡነ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ አናብስት ሰባብረው በሏቸው
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ፈጣሪ ያላዘዘላችሁን ለምን በላችሁ ብሎ እንዲተፏቸው አዝዞ ሕያዋን አድርጎላቸዋል ከዚህ በኋላ ቡራኬ ተቀብለው መንፈሳዊ ጨዋታ ተጨዋውተው #በአናብስታቸው ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል፡
የአባ ሳሙኤል ዕረፍታቸው በተቃረበ ጊዜ #ቅዱስ_ሚካኤል በክንፉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ወስዶ #ከእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አቀረባቸው፡፡
አምላካችን #እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶላቸው ከሰማይ ተመልሰው በታኅሣሥ 12 ቀን #በክብር_አርፈዋል ፍልሰተ ዐፅማቸው ከብዙ ጊዜ በኋላ ከዋልድባ ወደ ደብረ ዐባይ መስከረም 6 ቀን ተዛዉሯል
የፃድቁ አባታችን #አባ_ሣሙኤል ዘዋልድባ ረድኤት በረከታቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን ምልጃ ፀሎታቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን "አሜን"
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 day ago | [YT] | 159
View 8 replies
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
#ቅዱስ_ሚካኤል
" ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።"
ዳን. 10፥21
የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይ ጭምርም ነው
ቅዱስ ሚካኤሌ ለእኛ ለሰዎች አማላጅ ሲሆን ለቅዱሳን፣ ጻድቃን ሰማዕታት ደግሞ አጋዣቸው ነው
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል፥
ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ
በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ዘወትር የሚቆም
ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ
በሰማይም ለሚኖሩ ሀይሎች ሁሉ አለቃቸው የሆነ ነው
የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ምልጃው ተራዳኢነቱ አይለየን
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 day ago | [YT] | 71
View 3 replies
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
#ማኅሌታዊዉ_ቅዱስ_ያሬድ
#በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት #ማህሌታዊዉ_ቅዱስ_ያሬድ ዜማዎቹን ለቅድስት ቤተክርስቲያን ላዋለበት ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን
#ቅዱስ_ያሬድ አንደበቱ ጣፋጭ ልቡናው የቅድስና ማሕደር ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈፀም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ
ቅዱስ ያሬድ #ለኢትዮዽያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ሙሉ አካሏ ነው ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ
#ቅዱስ_ያሬድ በሕፃንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር ትምሕርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም በጥበበ #እግዚአብሔር እንጂ ምን ትምሕርት ባይገባው ፆምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር
ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምሕሩ ኮብልሎ #ማይ_ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና
ከዚህ በኋላ #ቅዱስ_ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው
#ካህኑ_ቅዱስ_ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ወሰነ በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት #ሦስት_መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት ድንገትም ነጥቀው ወደ #ሰማያት ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት
ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር ልዩ #ምስጋናና ልዩ #ዜማን አዳመጠ ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት
ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ፅዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ #ቅዱስ_ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላታል
#ቅዱስ_ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት አምስት ያሕል መጻሕፍትን ፅፏል በጣና ቂርቆስ በዙር አንባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋት እንደ #መላእክት በተባሕትዎ ኑሯል በተወለደ በ71 አመቱ ተሰዉሯል የአባታችን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል
የማኅሌታይ #ቅዱስ_ያሬድ ረድኤትና በረከት ለሁላችንም ይድረሰን የቅዱሳን #አበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን"
#ቅዱስ_ያሬድ
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
2 days ago | [YT] | 197
View 2 replies
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
#በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ዓመታዊ የልደት መታሠቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን
#እግዚአብሔር በፃድቁ እንደተገለጠ እወቁ" መዝ፤4፣3
#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው #መላከ እናታቸው #ወለተ_ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው በተወለዱ ዕለት ተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ በአንድነት በሶስትነት ለሚመሰገን ለአጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ #ስብሐት_ለአብ #ስብሐት_ለወልድ #ስብሐት_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው አመስግነዋል
የስማቸው ትርጓሜ #የአብ_የወልድ_የመንፈስ_ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ_እስትንፋስ ማለት ነው ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቦናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍት ቃላትን ብሉያትንና ሐዲሳትን ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል
በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ #እግዚአብሔር በፀለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን ገብተዋል
ሦስት ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን በማውጣት አገልግለዋል
አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ #ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል
አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው ወይን ተክለው ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን #ለቤተ_ክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሰዋል
አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው
ጌታም #በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል ሁሉንም #የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትንም ተሳልመዋል
የአባታችን #የፃድቁ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ፀሎትና ቃል ኪዳን ከኛ ጋር ይሁን #የአበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን "አሜን"
#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
3 days ago | [YT] | 273
View 4 replies
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
#ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ኪሮስ
የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ የልደት መታሠቢያ ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
#አቡነ_ኪሮስ አባታቸው ንጉስ ዮናስ እናታቸው እንስራ
ይባላሉ እሊህም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው ሀገራቸው ሮም ሲሆን በታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ የመጀመሪያ ስማቸው ዲላሶር ይባል ነበር
በኋላ አባታቸዉ ከሞቱ በኋላ ሀብት ንብረታቸዉን ተካፍለዉ ለድሆች ከመፀወቱ በሑዋላ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገቡ
በ17 አመታቸው ስርአተ ምንኩስናን ተምረው ከአባ በቡነዳ እጅ ስርአተ ምንኩስናን ተቀበሉ ከዚህ በሁዋላ በፆምና በፀሎት ተወስነው ኖሩ
ስለ አለም መከራ ለ 40 ዘመን ተኝተው ሲፀልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላዕክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡርን ቃል ሰምቶ ወድቋልና ጌታም ድምፁን ያሰማኝ አሏቸው በኋላም ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይቷቸው በመጨረሻም ጌታችን ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል
ቃል ኪዳናቸውም መካኖችን ልጅ የሌላቸው #ገድላቸውን
አቅፈው ቢያለቅሱ #ፀበሉን ቢጠጡ ስምሕን ቢጠሩ የመካኒቱን ማሕፀን እከፍታለሁ
ህፃናት የሚሞትባቸው #እንዳይሞትባቸው አደርጋለሁ በንፁህ ገንዘቡ ቂም እና በቀልን ሳይዝ በሕግ በስጋ ወደሙ ለፀና ሰው በስምህ በተሰራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ እሰጠዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል
ከዚህም በኋላ በተወለዱ በ 270 አመታቸው ሐምሌ 8 ቀን አርፈዋል #የፃድቁ_አቡነ_ኪሮስ ረድኤት በረከታቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን የቅዱሳን #አበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን "አሜን"
#አቡነ_ኪሮስ
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
5 days ago | [YT] | 212
View 0 replies
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
አጋእዝተ አለም ቅድስት ሥላሴ ከክፉዉ ሁሉ ይጠብቁን
#ቅድስት_ሥላሴ
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
5 days ago | [YT] | 187
View 2 replies
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
#ቅድስት_አርሴማ
❖ ታኅሣሥ 6 ክብረ በዓሏ የኾነው የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ❖
❖✔💥 በ290 ዓ.ም. በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ስላረፈችው ስለ ቅድስት አርሴማ በአርሜንያ Հռիփսիմէ
ተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች።
💥 እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡
❖✔💥 እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡
❖✔💥 ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡
💥 ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና
አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡
❖✔💥 የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡
❖✔💥 ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡
❖✔💥 ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ።
💥 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም።
💥 ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚል
ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች።
💥 አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በስሟ በተሰየመው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች ካለ ካታኮምብ ግበበ ምድር በአርመንያ አለ፡፡
💥 በአርመን ያለው የቅዱስ አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት እውቅና አግኝቶ እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም.
ተመዝግቧል።
❖✔💥 በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ፤ በሰሜን አሜሪካ ቨርጂንያ መካነ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ፨
❖✔💥 ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦
❖✔💥 ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡-
✍️ “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ
እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ
ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ
ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ
ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ”
(በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡
❖✔💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦
✍️“ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ
ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ
ዘፈጸመት ገድላ በጻማ
ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡
(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨
❖✔💥 እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨
❖✔💥 “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ
በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ
አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ
አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ
ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ”
(በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች (መግረፊያዎች) ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ) ይላል።
💥እኔም ከበረከቷ ለመሳተፍ ይህንን ጻፍኩ። እናንተም ከበረከቷ ትሳተፉ ዘንድ በአስተያየት መስጫው ላይ ደስ ያላችሁን ሰላምታና ውዳሴ አቅርቡላት።
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
#ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago | [YT] | 234
View 1 reply
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
#በዓታ_ለማርያም
[ታኅሣሥ 3 የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ድንቅ ታሪክና የ8 ሊቃውንት ትምህርት]
♥❖♥ ኢያቄምና ሐና ቃል ኪዳናቸውን ለመፈጸም ዘመዶቻቸውን ባልንጀሮቻቸውን ከነልጆቻቸው በመጥራት ሕፃን ልጃቸውን እመቤታችንን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ ያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ በካህናቱ ታጅቦ የምስጋና ዝማሬን ከልኡካኑ ጋር እያሰማ እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ።
♥❖♥ በዚያም ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወደሚገባበት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ሲኖሩ በየደረጃዎቹም መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ ሲደረስባቸው ከሚጸለዩት የዳዊት መዝሙራት ውስጥ መዝ ፻፲፰(፻፲፱)-፻፴፪ (፻፴፫) የሚገኙ ሲኾኑ እነዚኽንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አጥኚዎች “Psalms of Ascent” (የመውጣት መዝሙራት) ይሏቸዋል::
♥❖♥ እናትና አባቷም ሊቀ ካህናቱን ካለበት ቅዱስ ቦታ ወደነርሱ እስኪመጣ ለመቆየት ልጃቸው ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯትም ርሷ ግን በድንቅ አምላካዊ ሥራ መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ የሦስት ዓመቷ እመቤታችን ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት በእጅጉ ወደተቀደሰው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወዳለበት ስፍራ ኼደች ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት።
♥❖♥ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለሊቀ ካህናቱ የሰው ዘርን በመላ ወደ ገነት የሚያስገባ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የእግዚአብሔር ልጅን የምትወልደው ርሷ እንደኾነች ገልጾለት ቦታዋም በጣም የተቀደሰውና ርሱ መሥዋዕት ለማቅረብ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገባበት ከርሱ በቀር ማንም ሰው የማይገባበት ቅድስት ቅዱሳን ውስጥ መኾኑን ገልጾለታል ፡፡
♥❖♥ ርሱም ይኽነን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ይኽቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን? ብሎ ሲጨነቅ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብስት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ ፲፮፥፴፩፤ ፩ነገ ፲፱፥፮፤ ዕዝ. ሱቱ. ፲፫፥፴፰-፵፩)::
♥❖♥ ከዚያም “ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት ወጸለላ በአክናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብእሲ ወወሀባ ወመጠዋ ወዐርገ ውስተ ሰማይ” ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊን፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኽል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡
♥❖♥ ስላዩትና ስለተደረገው ነገር ኹሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አማናዊት የአምላክ መቅደስ የአካላዊ ቃል ታቦት እመቤታችንን ምሳሌዋ ወደሚኾነው ቤተ መቅደስ ታኅሣሥ ፫ በሦስት ዓመቷ አስገብተዋታል፤ ከዚያም ኢያቄምና ሐና ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡
♥♥♥ የቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ መቅደስ ሕይወት በእጅጉ አስደናቂ ሲኾን የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት (Holy Tradition) እንደሚያስረዳን ቤተ መቅደስ በኖረችባቸው 12 ዓመታት የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለቤተ መቅደስ የሚያስፈልገውን ነገር በእጆቿ እየሠራች በፍጹም ንጽሕና ቅድስና ኾና እግዚአብሔርን በማመስገን መላእክት እያገለገሏት ኖራለች፡፡
ይኽነን በቤተ መቅደስ የነበራትን ቆይታ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በጥልቀት ጽፈዋል እነሆ የሊቃውንቱ ቃል፦
፩) [አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ]
“የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና
ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስና
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”
(ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል)♥
♥“ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስ
በድንግልና ማርያም ስርጉተ ሥጋ ወነፍስ
ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ
ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ
እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ”
(በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንዳጌጠች ታቦት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ያጌጥሽ ማርያም፤ ቀንሞስ ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቱዎች ኢያቄምና ሐና ለጳጦስ ምሳሌ የኾንሽ አንቺን ከአስገኙሽ ዘንድ በሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ የመኖር ተአምርን አሳየሽ)
++++++++++++++
፪) [ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም]
♥♥♥ “ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ…” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ)
+++++++++++++++++++
፫) [በ፭፻፭ (505) ዓ.ም የተወለደው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን]
♥“አንቲ ውእቱ ንጽሕት እም ንጹሓን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ…” (ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የኾንሽ አንቺ ነሽ፤ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ በወርቅ እንደተጌጠና ዋጋው ብዙ በኾነ በሚያበራ ዕንቊ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ፤ እንዲኽ ኾነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ፤ መላእክት ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር፤ መላእክት እየጐበኙሽ እንዲኽ ዐሥራ ኹለት ዓመት ኖርሽ፤ መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር፤ ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር)
♥ “እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ጸቃውዕ ይውሕዝ እምከናፍሪሃ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ፤ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ”
(መላእክት እመቤታችንን እኅታችን ይሏታል፤ በክንፋቸው ይጋርዷታል፤ በማር ወለላ የተመሰለ የእግዚአብሔር ቃል ከከንፈሮቿ ይፈስሳል፤ ጒንጮቿ እንደ ሮማን ቅርፍት ናቸው፤ ልዑል ወደዳት፤ ዳዊት በመዝሙሩ አመሰገናት፤ በቤተ መቅደስ ተቀበሏት) (ቅዱስ ያሬድ፤ መጽሐፈ ድጓ)
♥ “ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዝእ ኀረያ ዕፀ ጳጦስ ሰመያ በቤተ መቅደስ ተወክፋ ዘካርያስ ወኲሎሙ ቅዱሳን ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ”
(ጌታ የመረጠሽ ማርያም ሆይ ለምኝልን፤ ዕፀ ጳጦስ ተብላ የተጠራችውን እመቤታችን ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ተቀበላት፤ ኹላቸውም ቅዱሳን ዐዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል)
♥ “ጠባብ ወትሕት በቤተ መቅደስ ዘልህቀት ወለተ ዳዊት ቀጸበቶ በትእምርት ለዘወረደ እመልዕልት”
(ብልኅና ትሕትናን የተላበሰችው በቤተ መቅደስ ያደገችው የዳዊት ልጅ እመቤታችን ከላይ የወረደውን በምልክት ጠራችው) ይላል
++++++++++++++
፬) [ከ፫፻፳-፬፻፫ (320-403) ዓ.ም የነበረው የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ]
♥ “She was brave and dignifified in all her action…” (እመቤታችን በኹሉም ርምጃዎቿ ጐበዝና የተከበረች ነበረች፤ የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበር፤ በጣም ዝግጁ ኾና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት፤ ለእያንዳንዱ ሰው አክብሮትና ክብር (ሰላምታ) ትሰጣለች፤ ቁመቷ መኻከለኛ ሲኾን አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ እንደነበር ይናገራሉ፤ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሀት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጯጯኽ ትናገራለች፤ በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም፤ መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጒሯ ቀይማ ነው፤ ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የኾኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ኾኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት-አረንጓዴ ይመስላል፤ የዐይኖቿ ቅንድብ (ሽፋሽፍት) ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው፤ አፍንጫዋም ረዥም፣ ከናፍሮቿ ቀይና ምሉእ ሲኾኑ በቃሎቿ ጣፋጭነት የተመላባቸው ነበሩ፤ ፊቷ ክብ ሳይኾን ግን እንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው፤ እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ፤ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትኾን ግድ የለሽነት ፈጽሞ ጨርሶ የለባትም ነበር፤ የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር፤ ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው (ማለትም በቤት ድር የተሠሩ) ልብሶችን ትለብስ ነበር፤ ይኽም በእጅጉ አብሯት የሚኼደው አለባበስና ይኽ እውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አኹን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው፤ ለማጠቃለል ያኽል በመንገዶቿ ኹሉ በጌታ ስጦታ የተመላች ነበረች)
+++++++++++
፭) [ከ፫፻፲፭-፫፻፹፮ (315-386) ዓ.ም ድረስ የነበረው የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ]
♥♥♥ “They (Joachim and Anna) were in the habit of visiting their daughter once each month,…’’ (እነርሱ (ኢያቄምና ሐና) በወር አንድ ጊዜ ልጃቸውን የመጐብኘት ልምድ ነበራቸው፤ ለርሷ የሚያስፈልጋትን ነገር ይዘው ይመጡ ነበር፤ እናም ትንሿ ድንግል ልጃቸው ከርሷ በዕድሜ ከፍ ከሚሉ ደናግል ጋር በቤተ መቅደስ ታገለግል ነበር፤ እነርሱም በእጆቿ እንዴት መሥራት እንደምትችል ያስተምሯት ነበር፤ ርሷም ዐዋቂ በኾነች ጊዜ በራሷ ወደ ቤተ መቅደሱ ዐደባባይ ስትኼድ ከካህናትና ከአባቷ በቀር ማንም ወንድ ከቶ አይቷት አያውቅም…ትንሿ ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ነበረች፤ የመላእክት አለቃው ገብርኤል በጣፋጭ መዐዛው ወደ ርሷ ቀረባት…የርሷ ውበቷ ምንም ወሰን አልነበረውም፤ ቤተ መቅደሱም ከጣፋጭ መዐዛዋ የተነሣ በመላእክት ይመላ ነበር፤ ለንግግሯ ሲሉ ብቻ ይጐበኟት ነበረ)
++++++++++++++++
፮) [በ፪፻፶፮ (256) ዓ.ም የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ የነበረው ዲሜጥሮስ]
♥♥♥ “At the moment when her mother Anna set her upon her feet, inside the door of the temple…” (እናቷ ሐና በካህናቱ ፊት በቤተ መቅደሱ በር ላይ ርሷን በእግሯ ባኖረቻት ጊዜ በራሷ ለጌታ መሥዋዕት ወደሚቀርብበት ወደ መሠዊያዉ መጋረጃ ወደ ቤተ መቅደስ እስክትደርስ ድረስ ኼደች፤ ከገባችም በኋላ ለመውጣት አልተመለሰችም በልቡናዋም የቤተሰቦቿ ሐሳብና ምድራዊ ነገራትን ከቶ አላሰበችም…እናም ባደገችና ስምንትና ዐሥር ዓመት በመላትም ጊዜ ለካህናቱ ኹሉ አብነት (ምሳሌ) ነበረች ርሷንም ለማየት ይፈሩ ነበር፤ መላ ሰውነቷ ንጹሕ ነበር ልቡናዋም በጌታ የጸና ነው፤በሥጋዋም በነፍሷም ንጽሕት ናት፤ ፊቷንም ከቤተ መቅደሱ በር ውጪ በፍጹም አላዞረችም፤ እንግዳ ሰውንም ከቶ አላየችም የወጣት ሰው ፊትን ለመመልከት ፊቷን ከቶ አላዞረችም፤ በቅድስና እግዚአብሔርን በማገልገል ለቤተ መቅደስ በመላላክ ኖረች እንጂ፤ ልብሷ ያማረ ዕጥፋቱ በማኅተሟ ላይ ወደ ታች የወረደ ሲኾን የራሷ መሸፈኛም እስከ ዐይኖቿ ይደርሳል…በዐይኖቿ ላይ በጭራሽ መዋቢያ ቀለም አልተጠቀመችም፤ በጉንጮቿ ላይ ምንም ዐይነት የማጌጫ አበባ አላኖረችም፤ በእግሮቿ ላይ መጫሚያ ሰንደሎች አላደረገችም፤ በክንዶቿና በእጆቿ ላይ አልቦ ወይም አምባር ወይም ጌጣጌጥ አላደረገችም ነበር፤ ከልክ ያለፈ ምግብ በጭራሽ ፈልጋ አታውቅም፤ በከተማው የገበያ ስፍራ ውስጥ በጭራሽ ተጉዛ አታውቅም፤ ለዚኽ ዓለም ሥራዎች በጭራሽ ጉጉት ዐድሮባት አያውቅም)
+++++++++++++
፯) [ከ፫፻፸፮-፬፻፵፬ (376-444) ዓ.ም የነበረው እስክንድርያዊዉ ቅዱስ ቄርሎስ]
♥♥♥ “Come, O all ye women who desire virginity…” (ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን እናት የኾነችውን የማርያምን ምሳሌ ተከተሉ፤ የርሷንም መንገድ መናኛ ምግብ መብላቷንና መሬት ላይ መተኛቷን ዐስቡ፤ ለዚኽ ዓለም ነገሮች ምንም ዐይነት ጉጉት የላትምና የርሷ ስምም ኹልጊዜም በካህናት አፍ ውስጥ ነበር፤ ሰውነቷን በጭራሽ በሕዝብ መታጠቢያ ውስጥ ታጥባ አታውቅም፤ ራሷን በፍጹም በመዋቢያ የፊት ቀለም፣ በዐይን ኩልና በቅባት በጭራሽ አስውባ አታውቅም፤ በጣም ያጌጠ ልብስ እንደሚወድዱ ኹሉም በዘመኗ የነበሩ ሴቶች በደማቅ ባለቀለም ልብስ በጭራሽ አስጌጣ አታውቅም፤ በጭራሽ የወይንን ጣዕም ቀምሳ አታውቅም፤ ኹልጊዜም ዓለማትን የፈጠረ ፈጣሪዋን ትጠብቅ ስለነበር ፊቷን ወደ ምሥራቅ አዙራ ትቀመጥ ነበር፤ ከእናቷና ከአባቷ በስተቀር ከማንም ጋር ተገናኝታና አውርታ አታውቅም)
+++++++++++++++++++
፰) [ ከ፪፻፺፮-፫፻፸፫ (296-373) ዓ.ም የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ]
♥♥♥ “Mary was pure virgin, with a harmonius disposition…” (ማርያም ንጽሕት ድንግል ስትኾን በጣም ጥሩ አቋም የነበራትና መልካም ሥራዎችን የምትወድድ ነበረች፤ በወንዶች መታየትን ፈጽማ አትፈልግም ነበር፤ ግን እግዚአብሔርን እንዲመረምራት ጠይቃዋለች፤ ያለማቋረጥ በቤቱ ውስጥ ቆይታለች፤ ከጨዋታ የራቀ (የመናኝ) ሰውን ኑሮ ትኖር የነበረ ሲኾን ማር ከምትሰጥ ንብ ጋር ትመሳሰላለች፤ በእጆቿ ከሠራቻቸው ሥራዎች የምታገኘውን ገንዘብ ለድኾች ታከፋፍላለች፤ በብቸኝነት ኹለት ነገራትን እንዲያደርግላት ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች፤ ይኸውም መጥፎ ሐሳብ በልቧ ውስጥ እንዳይሠርጽና ልቧ በጭራሽ ከፍቅር አምላካዊ እየቀዘቀዘ እንዳይኼድ ነበረ፤ ንግግሯ የተረጋጋ እና ድምፆቿም ዝግ ያሉ ናቸው፤ በየቀኑም መንፈሳዊ ርምጃ (ብቃታዊ መሻሻል ዕድገት) ማድረግ ትፈልጋለች፤ በየቀኑም ያነን ታደርጋለች፤ በጠዋት ስትነሣም ከዚኽ በፊት አስቀድማ ከሠራቻቸው አስበልጣ ሥራዎቿን ለመሥራት ትፈልጋለች፤ ሞትን ፈጽማ አትፈራም ነበር ይልቁኑ በሐዘን ኹና የመንግሥተ ሰማያት መዠመሪያ (መግቢያ) እንዳላቋረጠች በየቀኑ እያየች በጸሎቷ ታነሣለች) በማለት የደናግል መመኪያነቷን በስፋት ገልጾታል፡፡
ምንጭ፡- ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፤ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1 እና ክፍል 2 ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ)
[የአማናዊት መቅደስ የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፤ መልካም በዓል፡፡]
[ጸሎቷ እንዲጠብቀን በረከቷ እንዲትረፈረፍልን ወደ ቤተ መቅደስ መግባቷን አስመልክታችሁ እጅግ አብዝተን የምንወዳት የፈጣሪያችን የክርስቶስ እናትን አመስግኗት]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
#ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago | [YT] | 240
View 2 replies
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
ታህሳስ 1 #ነብዩ_ኤልያስ
" ኤልያስ እንደኛ የሆነ ሰው ነበረ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ፀለየ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም ሁለተኛም ፀለየ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች ያዕ ፭÷፲፯-፲፰ "
በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህችም በታኅሣሥ አንድ ቀን በእስራኤል ፊት ነቢይ #ኤልያስ የተገለጠበት ነው ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም #ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ #ቶና ነው
ስለርሱም እንዲህ ተነገረ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ #በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው እነርሱም ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን ወይም እስራኤልን በሰይፍና በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን ተባባሉ
በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ #ነገሥት ተጽፎአል ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል
በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ #ዮሐንስ #ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግሮአል ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ #በእግዚአብሔር ፊት የሚያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው አለ
ከጠላቶቻቸውም ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸዋለች የሚጠሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ #ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ በሰማይ ላይ ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል
ምስክርነታቸውንና ትንቢታቸውን ከፈፀሙ በኋላ ከባህር የወጣው አውሬ ከእሳቸው ጋር ይጣላል ድል ነስቶም ይገድላቸዋል አስከሬናቸውንም ፍጥሞ በምትባል በታላቂቱ አገር ያስጥለዋል ይችውም በምሥጢር ሰዶም ግብጽ የተባለች ጌታቸው የተሰቀለባት ናት
አስከሬናቸውንም ሕዝብና አሕዛብ በሀገርም ያሉ ነገዶች ሦስት ቀን ተኩል ያዩታል አስከሬናቸውንም በመቃብር ይቀብሩት ዘንድ አያሰናብቱም በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ሞት ደስ ይላቸዋል እርስ በርሳቸውም በደስታ እጅ መንሻ ይሰጣጣሉ እሊህ #ሁለቱ_ነቢያት በምድር በሚኖሩ ሰዎች መከራ አፅንተውባቸዋልና ይላሉ
ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ #ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወት መንፈስ መጥታ ታድርባቸዋለች ተነሥተውም በእግራቸው ይቆማሉ በሚያዩዋቸው ላይም ጽኑ ፍርሀት ይሆናል
ከወደ ሰማይ ቃል መጥቶ ወደዚህ ውጡ ይላቸዋል ከዚህ በኋላ ጠላቶቻቸው እያዩአቸው በደመና ያርጋሉ በዚያችም ሰዓት ጽኑ መነዋወጥ ይሆናል የዚያችም አገር ዐሥረኛ እጅዋ ይጠፋል በዚያም መነዋወጥ ሰባት ሽህ ሰዎች ይሞታሉ የቀሩት ግን ደንግጠው #የሰማይ_አምላክን ፈጽመው ያመሰግናሉ
አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከታላቁ ነብይ #ነብዩ_ኤልያስ ከልደቱ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን"
#ነብዩ_ኤልያስ
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago (edited) | [YT] | 120
View 2 replies
Load more