ልዳ ሚዲያ - Leda Media

#ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ኪሮስ

የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ የልደት መታሠቢያ ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ

#አቡነ_ኪሮስ አባታቸው ንጉስ ዮናስ እናታቸው እንስራ
ይባላሉ እሊህም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው ሀገራቸው ሮም ሲሆን በታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ የመጀመሪያ ስማቸው ዲላሶር ይባል ነበር

በኋላ አባታቸዉ ከሞቱ በኋላ ሀብት ንብረታቸዉን ተካፍለዉ ለድሆች ከመፀወቱ በሑዋላ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገቡ

በ17 አመታቸው ስርአተ ምንኩስናን ተምረው ከአባ በቡነዳ እጅ ስርአተ ምንኩስናን ተቀበሉ ከዚህ በሁዋላ በፆምና በፀሎት ተወስነው ኖሩ

ስለ አለም መከራ ለ 40 ዘመን ተኝተው ሲፀልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላዕክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡርን ቃል ሰምቶ ወድቋልና ጌታም ድምፁን ያሰማኝ አሏቸው በኋላም ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይቷቸው በመጨረሻም ጌታችን ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል

ቃል ኪዳናቸውም መካኖችን ልጅ የሌላቸው #ገድላቸውን
አቅፈው ቢያለቅሱ #ፀበሉን ቢጠጡ ስምሕን ቢጠሩ የመካኒቱን ማሕፀን እከፍታለሁ

ህፃናት የሚሞትባቸው #እንዳይሞትባቸው አደርጋለሁ በንፁህ ገንዘቡ ቂም እና በቀልን ሳይዝ በሕግ በስጋ ወደሙ ለፀና ሰው በስምህ በተሰራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ እሰጠዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል

ከዚህም በኋላ በተወለዱ በ 270 አመታቸው ሐምሌ 8 ቀን አርፈዋል #የፃድቁ_አቡነ_ኪሮስ ረድኤት በረከታቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን የቅዱሳን #አበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን "አሜን"

#አቡነ_ኪሮስ
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ

youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL

5 days ago | [YT] | 212