ልዳ ሚዲያ - Leda Media
ታህሳስ 1 #ነብዩ_ኤልያስ " ኤልያስ እንደኛ የሆነ ሰው ነበረ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ፀለየ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም ሁለተኛም ፀለየ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች ያዕ ፭÷፲፯-፲፰ "በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህችም በታኅሣሥ አንድ ቀን በእስራኤል ፊት ነቢይ #ኤልያስ የተገለጠበት ነው ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም #ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ #ቶና ነው ስለርሱም እንዲህ ተነገረ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ #በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው እነርሱም ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን ወይም እስራኤልን በሰይፍና በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን ተባባሉ በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ #ነገሥት ተጽፎአል ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ #ዮሐንስ #ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግሮአል ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ #በእግዚአብሔር ፊት የሚያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው አለ ከጠላቶቻቸውም ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸዋለች የሚጠሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ #ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ በሰማይ ላይ ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል ምስክርነታቸውንና ትንቢታቸውን ከፈፀሙ በኋላ ከባህር የወጣው አውሬ ከእሳቸው ጋር ይጣላል ድል ነስቶም ይገድላቸዋል አስከሬናቸውንም ፍጥሞ በምትባል በታላቂቱ አገር ያስጥለዋል ይችውም በምሥጢር ሰዶም ግብጽ የተባለች ጌታቸው የተሰቀለባት ናት አስከሬናቸውንም ሕዝብና አሕዛብ በሀገርም ያሉ ነገዶች ሦስት ቀን ተኩል ያዩታል አስከሬናቸውንም በመቃብር ይቀብሩት ዘንድ አያሰናብቱም በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ሞት ደስ ይላቸዋል እርስ በርሳቸውም በደስታ እጅ መንሻ ይሰጣጣሉ እሊህ #ሁለቱ_ነቢያት በምድር በሚኖሩ ሰዎች መከራ አፅንተውባቸዋልና ይላሉ ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ #ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወት መንፈስ መጥታ ታድርባቸዋለች ተነሥተውም በእግራቸው ይቆማሉ በሚያዩዋቸው ላይም ጽኑ ፍርሀት ይሆናል ከወደ ሰማይ ቃል መጥቶ ወደዚህ ውጡ ይላቸዋል ከዚህ በኋላ ጠላቶቻቸው እያዩአቸው በደመና ያርጋሉ በዚያችም ሰዓት ጽኑ መነዋወጥ ይሆናል የዚያችም አገር ዐሥረኛ እጅዋ ይጠፋል በዚያም መነዋወጥ ሰባት ሽህ ሰዎች ይሞታሉ የቀሩት ግን ደንግጠው #የሰማይ_አምላክን ፈጽመው ያመሰግናሉአምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከታላቁ ነብይ #ነብዩ_ኤልያስ ከልደቱ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን" #ነብዩ_ኤልያስ#ልዳ_ሚዲያ#ቤተ_ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago (edited) | [YT] | 120
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
ታህሳስ 1 #ነብዩ_ኤልያስ
" ኤልያስ እንደኛ የሆነ ሰው ነበረ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ፀለየ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም ሁለተኛም ፀለየ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች ያዕ ፭÷፲፯-፲፰ "
በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህችም በታኅሣሥ አንድ ቀን በእስራኤል ፊት ነቢይ #ኤልያስ የተገለጠበት ነው ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም #ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ #ቶና ነው
ስለርሱም እንዲህ ተነገረ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ #በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው እነርሱም ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን ወይም እስራኤልን በሰይፍና በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን ተባባሉ
በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ #ነገሥት ተጽፎአል ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል
በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ #ዮሐንስ #ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግሮአል ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ #በእግዚአብሔር ፊት የሚያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው አለ
ከጠላቶቻቸውም ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸዋለች የሚጠሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ #ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ በሰማይ ላይ ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል
ምስክርነታቸውንና ትንቢታቸውን ከፈፀሙ በኋላ ከባህር የወጣው አውሬ ከእሳቸው ጋር ይጣላል ድል ነስቶም ይገድላቸዋል አስከሬናቸውንም ፍጥሞ በምትባል በታላቂቱ አገር ያስጥለዋል ይችውም በምሥጢር ሰዶም ግብጽ የተባለች ጌታቸው የተሰቀለባት ናት
አስከሬናቸውንም ሕዝብና አሕዛብ በሀገርም ያሉ ነገዶች ሦስት ቀን ተኩል ያዩታል አስከሬናቸውንም በመቃብር ይቀብሩት ዘንድ አያሰናብቱም በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ሞት ደስ ይላቸዋል እርስ በርሳቸውም በደስታ እጅ መንሻ ይሰጣጣሉ እሊህ #ሁለቱ_ነቢያት በምድር በሚኖሩ ሰዎች መከራ አፅንተውባቸዋልና ይላሉ
ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ #ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወት መንፈስ መጥታ ታድርባቸዋለች ተነሥተውም በእግራቸው ይቆማሉ በሚያዩዋቸው ላይም ጽኑ ፍርሀት ይሆናል
ከወደ ሰማይ ቃል መጥቶ ወደዚህ ውጡ ይላቸዋል ከዚህ በኋላ ጠላቶቻቸው እያዩአቸው በደመና ያርጋሉ በዚያችም ሰዓት ጽኑ መነዋወጥ ይሆናል የዚያችም አገር ዐሥረኛ እጅዋ ይጠፋል በዚያም መነዋወጥ ሰባት ሽህ ሰዎች ይሞታሉ የቀሩት ግን ደንግጠው #የሰማይ_አምላክን ፈጽመው ያመሰግናሉ
አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከታላቁ ነብይ #ነብዩ_ኤልያስ ከልደቱ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን"
#ነብዩ_ኤልያስ
#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago (edited) | [YT] | 120