ልዳ ሚዲያ - Leda Media
#በዓታ_ለማርያም[ታኅሣሥ 3 የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ድንቅ ታሪክና የ8 ሊቃውንት ትምህርት]♥❖♥ ኢያቄምና ሐና ቃል ኪዳናቸውን ለመፈጸም ዘመዶቻቸውን ባልንጀሮቻቸውን ከነልጆቻቸው በመጥራት ሕፃን ልጃቸውን እመቤታችንን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ ያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ በካህናቱ ታጅቦ የምስጋና ዝማሬን ከልኡካኑ ጋር እያሰማ እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ። ♥❖♥ በዚያም ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወደሚገባበት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ሲኖሩ በየደረጃዎቹም መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ ሲደረስባቸው ከሚጸለዩት የዳዊት መዝሙራት ውስጥ መዝ ፻፲፰(፻፲፱)-፻፴፪ (፻፴፫) የሚገኙ ሲኾኑ እነዚኽንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አጥኚዎች “Psalms of Ascent” (የመውጣት መዝሙራት) ይሏቸዋል::♥❖♥ እናትና አባቷም ሊቀ ካህናቱን ካለበት ቅዱስ ቦታ ወደነርሱ እስኪመጣ ለመቆየት ልጃቸው ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯትም ርሷ ግን በድንቅ አምላካዊ ሥራ መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ የሦስት ዓመቷ እመቤታችን ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት በእጅጉ ወደተቀደሰው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወዳለበት ስፍራ ኼደች ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት።♥❖♥ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለሊቀ ካህናቱ የሰው ዘርን በመላ ወደ ገነት የሚያስገባ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የእግዚአብሔር ልጅን የምትወልደው ርሷ እንደኾነች ገልጾለት ቦታዋም በጣም የተቀደሰውና ርሱ መሥዋዕት ለማቅረብ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገባበት ከርሱ በቀር ማንም ሰው የማይገባበት ቅድስት ቅዱሳን ውስጥ መኾኑን ገልጾለታል ፡፡ ♥❖♥ ርሱም ይኽነን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ይኽቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን? ብሎ ሲጨነቅ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብስት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ ፲፮፥፴፩፤ ፩ነገ ፲፱፥፮፤ ዕዝ. ሱቱ. ፲፫፥፴፰-፵፩):: ♥❖♥ ከዚያም “ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት ወጸለላ በአክናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብእሲ ወወሀባ ወመጠዋ ወዐርገ ውስተ ሰማይ” ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊን፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኽል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡♥❖♥ ስላዩትና ስለተደረገው ነገር ኹሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አማናዊት የአምላክ መቅደስ የአካላዊ ቃል ታቦት እመቤታችንን ምሳሌዋ ወደሚኾነው ቤተ መቅደስ ታኅሣሥ ፫ በሦስት ዓመቷ አስገብተዋታል፤ ከዚያም ኢያቄምና ሐና ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡♥♥♥ የቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ መቅደስ ሕይወት በእጅጉ አስደናቂ ሲኾን የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት (Holy Tradition) እንደሚያስረዳን ቤተ መቅደስ በኖረችባቸው 12 ዓመታት የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለቤተ መቅደስ የሚያስፈልገውን ነገር በእጆቿ እየሠራች በፍጹም ንጽሕና ቅድስና ኾና እግዚአብሔርን በማመስገን መላእክት እያገለገሏት ኖራለች፡፡ ይኽነን በቤተ መቅደስ የነበራትን ቆይታ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በጥልቀት ጽፈዋል እነሆ የሊቃውንቱ ቃል፦፩) [አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ] “የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምናአመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐናወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስናምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መናፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”(ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል)♥♥“ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስበድንግልና ማርያም ስርጉተ ሥጋ ወነፍስተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስእምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ”(በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንዳጌጠች ታቦት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ያጌጥሽ ማርያም፤ ቀንሞስ ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቱዎች ኢያቄምና ሐና ለጳጦስ ምሳሌ የኾንሽ አንቺን ከአስገኙሽ ዘንድ በሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ የመኖር ተአምርን አሳየሽ) ++++++++++++++፪) [ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም]♥♥♥ “ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ…” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ) +++++++++++++++++++፫) [በ፭፻፭ (505) ዓ.ም የተወለደው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን]♥“አንቲ ውእቱ ንጽሕት እም ንጹሓን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ…” (ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የኾንሽ አንቺ ነሽ፤ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ በወርቅ እንደተጌጠና ዋጋው ብዙ በኾነ በሚያበራ ዕንቊ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ፤ እንዲኽ ኾነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ፤ መላእክት ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር፤ መላእክት እየጐበኙሽ እንዲኽ ዐሥራ ኹለት ዓመት ኖርሽ፤ መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር፤ ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር)♥ “እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ጸቃውዕ ይውሕዝ እምከናፍሪሃ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ፤ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ” (መላእክት እመቤታችንን እኅታችን ይሏታል፤ በክንፋቸው ይጋርዷታል፤ በማር ወለላ የተመሰለ የእግዚአብሔር ቃል ከከንፈሮቿ ይፈስሳል፤ ጒንጮቿ እንደ ሮማን ቅርፍት ናቸው፤ ልዑል ወደዳት፤ ዳዊት በመዝሙሩ አመሰገናት፤ በቤተ መቅደስ ተቀበሏት) (ቅዱስ ያሬድ፤ መጽሐፈ ድጓ)♥ “ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዝእ ኀረያ ዕፀ ጳጦስ ሰመያ በቤተ መቅደስ ተወክፋ ዘካርያስ ወኲሎሙ ቅዱሳን ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ” (ጌታ የመረጠሽ ማርያም ሆይ ለምኝልን፤ ዕፀ ጳጦስ ተብላ የተጠራችውን እመቤታችን ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ተቀበላት፤ ኹላቸውም ቅዱሳን ዐዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል) ♥ “ጠባብ ወትሕት በቤተ መቅደስ ዘልህቀት ወለተ ዳዊት ቀጸበቶ በትእምርት ለዘወረደ እመልዕልት”(ብልኅና ትሕትናን የተላበሰችው በቤተ መቅደስ ያደገችው የዳዊት ልጅ እመቤታችን ከላይ የወረደውን በምልክት ጠራችው) ይላል ++++++++++++++፬) [ከ፫፻፳-፬፻፫ (320-403) ዓ.ም የነበረው የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ]♥ “She was brave and dignifified in all her action…” (እመቤታችን በኹሉም ርምጃዎቿ ጐበዝና የተከበረች ነበረች፤ የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበር፤ በጣም ዝግጁ ኾና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት፤ ለእያንዳንዱ ሰው አክብሮትና ክብር (ሰላምታ) ትሰጣለች፤ ቁመቷ መኻከለኛ ሲኾን አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ እንደነበር ይናገራሉ፤ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሀት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጯጯኽ ትናገራለች፤ በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም፤ መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጒሯ ቀይማ ነው፤ ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የኾኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ኾኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት-አረንጓዴ ይመስላል፤ የዐይኖቿ ቅንድብ (ሽፋሽፍት) ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው፤ አፍንጫዋም ረዥም፣ ከናፍሮቿ ቀይና ምሉእ ሲኾኑ በቃሎቿ ጣፋጭነት የተመላባቸው ነበሩ፤ ፊቷ ክብ ሳይኾን ግን እንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው፤ እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ፤ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትኾን ግድ የለሽነት ፈጽሞ ጨርሶ የለባትም ነበር፤ የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር፤ ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው (ማለትም በቤት ድር የተሠሩ) ልብሶችን ትለብስ ነበር፤ ይኽም በእጅጉ አብሯት የሚኼደው አለባበስና ይኽ እውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አኹን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው፤ ለማጠቃለል ያኽል በመንገዶቿ ኹሉ በጌታ ስጦታ የተመላች ነበረች) +++++++++++፭) [ከ፫፻፲፭-፫፻፹፮ (315-386) ዓ.ም ድረስ የነበረው የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ]♥♥♥ “They (Joachim and Anna) were in the habit of visiting their daughter once each month,…’’ (እነርሱ (ኢያቄምና ሐና) በወር አንድ ጊዜ ልጃቸውን የመጐብኘት ልምድ ነበራቸው፤ ለርሷ የሚያስፈልጋትን ነገር ይዘው ይመጡ ነበር፤ እናም ትንሿ ድንግል ልጃቸው ከርሷ በዕድሜ ከፍ ከሚሉ ደናግል ጋር በቤተ መቅደስ ታገለግል ነበር፤ እነርሱም በእጆቿ እንዴት መሥራት እንደምትችል ያስተምሯት ነበር፤ ርሷም ዐዋቂ በኾነች ጊዜ በራሷ ወደ ቤተ መቅደሱ ዐደባባይ ስትኼድ ከካህናትና ከአባቷ በቀር ማንም ወንድ ከቶ አይቷት አያውቅም…ትንሿ ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ነበረች፤ የመላእክት አለቃው ገብርኤል በጣፋጭ መዐዛው ወደ ርሷ ቀረባት…የርሷ ውበቷ ምንም ወሰን አልነበረውም፤ ቤተ መቅደሱም ከጣፋጭ መዐዛዋ የተነሣ በመላእክት ይመላ ነበር፤ ለንግግሯ ሲሉ ብቻ ይጐበኟት ነበረ) ++++++++++++++++፮) [በ፪፻፶፮ (256) ዓ.ም የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ የነበረው ዲሜጥሮስ]♥♥♥ “At the moment when her mother Anna set her upon her feet, inside the door of the temple…” (እናቷ ሐና በካህናቱ ፊት በቤተ መቅደሱ በር ላይ ርሷን በእግሯ ባኖረቻት ጊዜ በራሷ ለጌታ መሥዋዕት ወደሚቀርብበት ወደ መሠዊያዉ መጋረጃ ወደ ቤተ መቅደስ እስክትደርስ ድረስ ኼደች፤ ከገባችም በኋላ ለመውጣት አልተመለሰችም በልቡናዋም የቤተሰቦቿ ሐሳብና ምድራዊ ነገራትን ከቶ አላሰበችም…እናም ባደገችና ስምንትና ዐሥር ዓመት በመላትም ጊዜ ለካህናቱ ኹሉ አብነት (ምሳሌ) ነበረች ርሷንም ለማየት ይፈሩ ነበር፤ መላ ሰውነቷ ንጹሕ ነበር ልቡናዋም በጌታ የጸና ነው፤በሥጋዋም በነፍሷም ንጽሕት ናት፤ ፊቷንም ከቤተ መቅደሱ በር ውጪ በፍጹም አላዞረችም፤ እንግዳ ሰውንም ከቶ አላየችም የወጣት ሰው ፊትን ለመመልከት ፊቷን ከቶ አላዞረችም፤ በቅድስና እግዚአብሔርን በማገልገል ለቤተ መቅደስ በመላላክ ኖረች እንጂ፤ ልብሷ ያማረ ዕጥፋቱ በማኅተሟ ላይ ወደ ታች የወረደ ሲኾን የራሷ መሸፈኛም እስከ ዐይኖቿ ይደርሳል…በዐይኖቿ ላይ በጭራሽ መዋቢያ ቀለም አልተጠቀመችም፤ በጉንጮቿ ላይ ምንም ዐይነት የማጌጫ አበባ አላኖረችም፤ በእግሮቿ ላይ መጫሚያ ሰንደሎች አላደረገችም፤ በክንዶቿና በእጆቿ ላይ አልቦ ወይም አምባር ወይም ጌጣጌጥ አላደረገችም ነበር፤ ከልክ ያለፈ ምግብ በጭራሽ ፈልጋ አታውቅም፤ በከተማው የገበያ ስፍራ ውስጥ በጭራሽ ተጉዛ አታውቅም፤ ለዚኽ ዓለም ሥራዎች በጭራሽ ጉጉት ዐድሮባት አያውቅም) +++++++++++++፯) [ከ፫፻፸፮-፬፻፵፬ (376-444) ዓ.ም የነበረው እስክንድርያዊዉ ቅዱስ ቄርሎስ]♥♥♥ “Come, O all ye women who desire virginity…” (ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን እናት የኾነችውን የማርያምን ምሳሌ ተከተሉ፤ የርሷንም መንገድ መናኛ ምግብ መብላቷንና መሬት ላይ መተኛቷን ዐስቡ፤ ለዚኽ ዓለም ነገሮች ምንም ዐይነት ጉጉት የላትምና የርሷ ስምም ኹልጊዜም በካህናት አፍ ውስጥ ነበር፤ ሰውነቷን በጭራሽ በሕዝብ መታጠቢያ ውስጥ ታጥባ አታውቅም፤ ራሷን በፍጹም በመዋቢያ የፊት ቀለም፣ በዐይን ኩልና በቅባት በጭራሽ አስውባ አታውቅም፤ በጣም ያጌጠ ልብስ እንደሚወድዱ ኹሉም በዘመኗ የነበሩ ሴቶች በደማቅ ባለቀለም ልብስ በጭራሽ አስጌጣ አታውቅም፤ በጭራሽ የወይንን ጣዕም ቀምሳ አታውቅም፤ ኹልጊዜም ዓለማትን የፈጠረ ፈጣሪዋን ትጠብቅ ስለነበር ፊቷን ወደ ምሥራቅ አዙራ ትቀመጥ ነበር፤ ከእናቷና ከአባቷ በስተቀር ከማንም ጋር ተገናኝታና አውርታ አታውቅም) +++++++++++++++++++፰) [ ከ፪፻፺፮-፫፻፸፫ (296-373) ዓ.ም የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ]♥♥♥ “Mary was pure virgin, with a harmonius disposition…” (ማርያም ንጽሕት ድንግል ስትኾን በጣም ጥሩ አቋም የነበራትና መልካም ሥራዎችን የምትወድድ ነበረች፤ በወንዶች መታየትን ፈጽማ አትፈልግም ነበር፤ ግን እግዚአብሔርን እንዲመረምራት ጠይቃዋለች፤ ያለማቋረጥ በቤቱ ውስጥ ቆይታለች፤ ከጨዋታ የራቀ (የመናኝ) ሰውን ኑሮ ትኖር የነበረ ሲኾን ማር ከምትሰጥ ንብ ጋር ትመሳሰላለች፤ በእጆቿ ከሠራቻቸው ሥራዎች የምታገኘውን ገንዘብ ለድኾች ታከፋፍላለች፤ በብቸኝነት ኹለት ነገራትን እንዲያደርግላት ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች፤ ይኸውም መጥፎ ሐሳብ በልቧ ውስጥ እንዳይሠርጽና ልቧ በጭራሽ ከፍቅር አምላካዊ እየቀዘቀዘ እንዳይኼድ ነበረ፤ ንግግሯ የተረጋጋ እና ድምፆቿም ዝግ ያሉ ናቸው፤ በየቀኑም መንፈሳዊ ርምጃ (ብቃታዊ መሻሻል ዕድገት) ማድረግ ትፈልጋለች፤ በየቀኑም ያነን ታደርጋለች፤ በጠዋት ስትነሣም ከዚኽ በፊት አስቀድማ ከሠራቻቸው አስበልጣ ሥራዎቿን ለመሥራት ትፈልጋለች፤ ሞትን ፈጽማ አትፈራም ነበር ይልቁኑ በሐዘን ኹና የመንግሥተ ሰማያት መዠመሪያ (መግቢያ) እንዳላቋረጠች በየቀኑ እያየች በጸሎቷ ታነሣለች) በማለት የደናግል መመኪያነቷን በስፋት ገልጾታል፡፡ምንጭ፡- ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፤ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1 እና ክፍል 2 ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ)[የአማናዊት መቅደስ የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፤ መልካም በዓል፡፡][ጸሎቷ እንዲጠብቀን በረከቷ እንዲትረፈረፍልን ወደ ቤተ መቅደስ መግባቷን አስመልክታችሁ እጅግ አብዝተን የምንወዳት የፈጣሪያችን የክርስቶስ እናትን አመስግኗት]✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ#ልዳ_ሚዲያyoutube.com/@Ledamediat.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0 www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago | [YT] | 240
ልዳ ሚዲያ - Leda Media
#በዓታ_ለማርያም
[ታኅሣሥ 3 የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ድንቅ ታሪክና የ8 ሊቃውንት ትምህርት]
♥❖♥ ኢያቄምና ሐና ቃል ኪዳናቸውን ለመፈጸም ዘመዶቻቸውን ባልንጀሮቻቸውን ከነልጆቻቸው በመጥራት ሕፃን ልጃቸውን እመቤታችንን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ ያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ በካህናቱ ታጅቦ የምስጋና ዝማሬን ከልኡካኑ ጋር እያሰማ እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ።
♥❖♥ በዚያም ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወደሚገባበት ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ሲኖሩ በየደረጃዎቹም መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ ሲደረስባቸው ከሚጸለዩት የዳዊት መዝሙራት ውስጥ መዝ ፻፲፰(፻፲፱)-፻፴፪ (፻፴፫) የሚገኙ ሲኾኑ እነዚኽንም የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አጥኚዎች “Psalms of Ascent” (የመውጣት መዝሙራት) ይሏቸዋል::
♥❖♥ እናትና አባቷም ሊቀ ካህናቱን ካለበት ቅዱስ ቦታ ወደነርሱ እስኪመጣ ለመቆየት ልጃቸው ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯትም ርሷ ግን በድንቅ አምላካዊ ሥራ መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ የሦስት ዓመቷ እመቤታችን ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት በእጅጉ ወደተቀደሰው ሊቀ ካህናቱ ብቻ ወዳለበት ስፍራ ኼደች ርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት።
♥❖♥ያን ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለሊቀ ካህናቱ የሰው ዘርን በመላ ወደ ገነት የሚያስገባ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የእግዚአብሔር ልጅን የምትወልደው ርሷ እንደኾነች ገልጾለት ቦታዋም በጣም የተቀደሰውና ርሱ መሥዋዕት ለማቅረብ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገባበት ከርሱ በቀር ማንም ሰው የማይገባበት ቅድስት ቅዱሳን ውስጥ መኾኑን ገልጾለታል ፡፡
♥❖♥ ርሱም ይኽነን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ይኽቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን? ብሎ ሲጨነቅ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብስት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ ፲፮፥፴፩፤ ፩ነገ ፲፱፥፮፤ ዕዝ. ሱቱ. ፲፫፥፴፰-፵፩)::
♥❖♥ ከዚያም “ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት ወጸለላ በአክናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብእሲ ወወሀባ ወመጠዋ ወዐርገ ውስተ ሰማይ” ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊን፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኽል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡
♥❖♥ ስላዩትና ስለተደረገው ነገር ኹሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አማናዊት የአምላክ መቅደስ የአካላዊ ቃል ታቦት እመቤታችንን ምሳሌዋ ወደሚኾነው ቤተ መቅደስ ታኅሣሥ ፫ በሦስት ዓመቷ አስገብተዋታል፤ ከዚያም ኢያቄምና ሐና ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡
♥♥♥ የቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ መቅደስ ሕይወት በእጅጉ አስደናቂ ሲኾን የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ትውፊት (Holy Tradition) እንደሚያስረዳን ቤተ መቅደስ በኖረችባቸው 12 ዓመታት የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናት ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለቤተ መቅደስ የሚያስፈልገውን ነገር በእጆቿ እየሠራች በፍጹም ንጽሕና ቅድስና ኾና እግዚአብሔርን በማመስገን መላእክት እያገለገሏት ኖራለች፡፡
ይኽነን በቤተ መቅደስ የነበራትን ቆይታ ቀደምት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በጥልቀት ጽፈዋል እነሆ የሊቃውንቱ ቃል፦
፩) [አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ በማሕሌተ ጽጌ]
“የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና
ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስና
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”
(ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል)♥
♥“ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስ
በድንግልና ማርያም ስርጉተ ሥጋ ወነፍስ
ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ
ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ
እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ”
(በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንዳጌጠች ታቦት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ያጌጥሽ ማርያም፤ ቀንሞስ ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቱዎች ኢያቄምና ሐና ለጳጦስ ምሳሌ የኾንሽ አንቺን ከአስገኙሽ ዘንድ በሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ የመኖር ተአምርን አሳየሽ)
++++++++++++++
፪) [ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም]
♥♥♥ “ኦ ድንግል አኮ በተላህዮ ዘልሕቂ ከመ አዋልደ ዕብራውያን እለ ያገዝፋ ክሣዶን አላ በቅድስና ወበንጽሕ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበርኪ…” (ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ)
+++++++++++++++++++
፫) [በ፭፻፭ (505) ዓ.ም የተወለደው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን]
♥“አንቲ ውእቱ ንጽሕት እም ንጹሓን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ…” (ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የኾንሽ አንቺ ነሽ፤ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደተሠራ በወርቅ እንደተጌጠና ዋጋው ብዙ በኾነ በሚያበራ ዕንቊ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ፤ እንዲኽ ኾነሽ በቤተ መቅደስ ውስጥ ኖርሽ፤ መላእክት ዘወትር ምግብሽን ያመጡ ነበር፤ መላእክት እየጐበኙሽ እንዲኽ ዐሥራ ኹለት ዓመት ኖርሽ፤ መጠጥሽም የሕይወት መጠጥ ነበር፤ ምግብሽም የሰማይ ኅብስት ነበር)
♥ “እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ጸቃውዕ ይውሕዝ እምከናፍሪሃ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ፤ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ”
(መላእክት እመቤታችንን እኅታችን ይሏታል፤ በክንፋቸው ይጋርዷታል፤ በማር ወለላ የተመሰለ የእግዚአብሔር ቃል ከከንፈሮቿ ይፈስሳል፤ ጒንጮቿ እንደ ሮማን ቅርፍት ናቸው፤ ልዑል ወደዳት፤ ዳዊት በመዝሙሩ አመሰገናት፤ በቤተ መቅደስ ተቀበሏት) (ቅዱስ ያሬድ፤ መጽሐፈ ድጓ)
♥ “ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዝእ ኀረያ ዕፀ ጳጦስ ሰመያ በቤተ መቅደስ ተወክፋ ዘካርያስ ወኲሎሙ ቅዱሳን ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ”
(ጌታ የመረጠሽ ማርያም ሆይ ለምኝልን፤ ዕፀ ጳጦስ ተብላ የተጠራችውን እመቤታችን ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ተቀበላት፤ ኹላቸውም ቅዱሳን ዐዲሲቱ እንቦሳ ይሏታል)
♥ “ጠባብ ወትሕት በቤተ መቅደስ ዘልህቀት ወለተ ዳዊት ቀጸበቶ በትእምርት ለዘወረደ እመልዕልት”
(ብልኅና ትሕትናን የተላበሰችው በቤተ መቅደስ ያደገችው የዳዊት ልጅ እመቤታችን ከላይ የወረደውን በምልክት ጠራችው) ይላል
++++++++++++++
፬) [ከ፫፻፳-፬፻፫ (320-403) ዓ.ም የነበረው የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ]
♥ “She was brave and dignifified in all her action…” (እመቤታችን በኹሉም ርምጃዎቿ ጐበዝና የተከበረች ነበረች፤ የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲኾን ርሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚኾንበት ብቻ ነበር፤ በጣም ዝግጁ ኾና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት፤ ለእያንዳንዱ ሰው አክብሮትና ክብር (ሰላምታ) ትሰጣለች፤ ቁመቷ መኻከለኛ ሲኾን አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ እንደነበር ይናገራሉ፤ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሀት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጯጯኽ ትናገራለች፤ በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም፤ መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጒሯ ቀይማ ነው፤ ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የኾኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ኾኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት-አረንጓዴ ይመስላል፤ የዐይኖቿ ቅንድብ (ሽፋሽፍት) ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው፤ አፍንጫዋም ረዥም፣ ከናፍሮቿ ቀይና ምሉእ ሲኾኑ በቃሎቿ ጣፋጭነት የተመላባቸው ነበሩ፤ ፊቷ ክብ ሳይኾን ግን እንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው፤ እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ፤ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትኾን ግድ የለሽነት ፈጽሞ ጨርሶ የለባትም ነበር፤ የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር፤ ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው (ማለትም በቤት ድር የተሠሩ) ልብሶችን ትለብስ ነበር፤ ይኽም በእጅጉ አብሯት የሚኼደው አለባበስና ይኽ እውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አኹን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው፤ ለማጠቃለል ያኽል በመንገዶቿ ኹሉ በጌታ ስጦታ የተመላች ነበረች)
+++++++++++
፭) [ከ፫፻፲፭-፫፻፹፮ (315-386) ዓ.ም ድረስ የነበረው የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ]
♥♥♥ “They (Joachim and Anna) were in the habit of visiting their daughter once each month,…’’ (እነርሱ (ኢያቄምና ሐና) በወር አንድ ጊዜ ልጃቸውን የመጐብኘት ልምድ ነበራቸው፤ ለርሷ የሚያስፈልጋትን ነገር ይዘው ይመጡ ነበር፤ እናም ትንሿ ድንግል ልጃቸው ከርሷ በዕድሜ ከፍ ከሚሉ ደናግል ጋር በቤተ መቅደስ ታገለግል ነበር፤ እነርሱም በእጆቿ እንዴት መሥራት እንደምትችል ያስተምሯት ነበር፤ ርሷም ዐዋቂ በኾነች ጊዜ በራሷ ወደ ቤተ መቅደሱ ዐደባባይ ስትኼድ ከካህናትና ከአባቷ በቀር ማንም ወንድ ከቶ አይቷት አያውቅም…ትንሿ ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ነበረች፤ የመላእክት አለቃው ገብርኤል በጣፋጭ መዐዛው ወደ ርሷ ቀረባት…የርሷ ውበቷ ምንም ወሰን አልነበረውም፤ ቤተ መቅደሱም ከጣፋጭ መዐዛዋ የተነሣ በመላእክት ይመላ ነበር፤ ለንግግሯ ሲሉ ብቻ ይጐበኟት ነበረ)
++++++++++++++++
፮) [በ፪፻፶፮ (256) ዓ.ም የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ የነበረው ዲሜጥሮስ]
♥♥♥ “At the moment when her mother Anna set her upon her feet, inside the door of the temple…” (እናቷ ሐና በካህናቱ ፊት በቤተ መቅደሱ በር ላይ ርሷን በእግሯ ባኖረቻት ጊዜ በራሷ ለጌታ መሥዋዕት ወደሚቀርብበት ወደ መሠዊያዉ መጋረጃ ወደ ቤተ መቅደስ እስክትደርስ ድረስ ኼደች፤ ከገባችም በኋላ ለመውጣት አልተመለሰችም በልቡናዋም የቤተሰቦቿ ሐሳብና ምድራዊ ነገራትን ከቶ አላሰበችም…እናም ባደገችና ስምንትና ዐሥር ዓመት በመላትም ጊዜ ለካህናቱ ኹሉ አብነት (ምሳሌ) ነበረች ርሷንም ለማየት ይፈሩ ነበር፤ መላ ሰውነቷ ንጹሕ ነበር ልቡናዋም በጌታ የጸና ነው፤በሥጋዋም በነፍሷም ንጽሕት ናት፤ ፊቷንም ከቤተ መቅደሱ በር ውጪ በፍጹም አላዞረችም፤ እንግዳ ሰውንም ከቶ አላየችም የወጣት ሰው ፊትን ለመመልከት ፊቷን ከቶ አላዞረችም፤ በቅድስና እግዚአብሔርን በማገልገል ለቤተ መቅደስ በመላላክ ኖረች እንጂ፤ ልብሷ ያማረ ዕጥፋቱ በማኅተሟ ላይ ወደ ታች የወረደ ሲኾን የራሷ መሸፈኛም እስከ ዐይኖቿ ይደርሳል…በዐይኖቿ ላይ በጭራሽ መዋቢያ ቀለም አልተጠቀመችም፤ በጉንጮቿ ላይ ምንም ዐይነት የማጌጫ አበባ አላኖረችም፤ በእግሮቿ ላይ መጫሚያ ሰንደሎች አላደረገችም፤ በክንዶቿና በእጆቿ ላይ አልቦ ወይም አምባር ወይም ጌጣጌጥ አላደረገችም ነበር፤ ከልክ ያለፈ ምግብ በጭራሽ ፈልጋ አታውቅም፤ በከተማው የገበያ ስፍራ ውስጥ በጭራሽ ተጉዛ አታውቅም፤ ለዚኽ ዓለም ሥራዎች በጭራሽ ጉጉት ዐድሮባት አያውቅም)
+++++++++++++
፯) [ከ፫፻፸፮-፬፻፵፬ (376-444) ዓ.ም የነበረው እስክንድርያዊዉ ቅዱስ ቄርሎስ]
♥♥♥ “Come, O all ye women who desire virginity…” (ድንግልናን የምትፈልጉ ሴቶች በሙሉ የጌታችን እናት የኾነችውን የማርያምን ምሳሌ ተከተሉ፤ የርሷንም መንገድ መናኛ ምግብ መብላቷንና መሬት ላይ መተኛቷን ዐስቡ፤ ለዚኽ ዓለም ነገሮች ምንም ዐይነት ጉጉት የላትምና የርሷ ስምም ኹልጊዜም በካህናት አፍ ውስጥ ነበር፤ ሰውነቷን በጭራሽ በሕዝብ መታጠቢያ ውስጥ ታጥባ አታውቅም፤ ራሷን በፍጹም በመዋቢያ የፊት ቀለም፣ በዐይን ኩልና በቅባት በጭራሽ አስውባ አታውቅም፤ በጣም ያጌጠ ልብስ እንደሚወድዱ ኹሉም በዘመኗ የነበሩ ሴቶች በደማቅ ባለቀለም ልብስ በጭራሽ አስጌጣ አታውቅም፤ በጭራሽ የወይንን ጣዕም ቀምሳ አታውቅም፤ ኹልጊዜም ዓለማትን የፈጠረ ፈጣሪዋን ትጠብቅ ስለነበር ፊቷን ወደ ምሥራቅ አዙራ ትቀመጥ ነበር፤ ከእናቷና ከአባቷ በስተቀር ከማንም ጋር ተገናኝታና አውርታ አታውቅም)
+++++++++++++++++++
፰) [ ከ፪፻፺፮-፫፻፸፫ (296-373) ዓ.ም የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ]
♥♥♥ “Mary was pure virgin, with a harmonius disposition…” (ማርያም ንጽሕት ድንግል ስትኾን በጣም ጥሩ አቋም የነበራትና መልካም ሥራዎችን የምትወድድ ነበረች፤ በወንዶች መታየትን ፈጽማ አትፈልግም ነበር፤ ግን እግዚአብሔርን እንዲመረምራት ጠይቃዋለች፤ ያለማቋረጥ በቤቱ ውስጥ ቆይታለች፤ ከጨዋታ የራቀ (የመናኝ) ሰውን ኑሮ ትኖር የነበረ ሲኾን ማር ከምትሰጥ ንብ ጋር ትመሳሰላለች፤ በእጆቿ ከሠራቻቸው ሥራዎች የምታገኘውን ገንዘብ ለድኾች ታከፋፍላለች፤ በብቸኝነት ኹለት ነገራትን እንዲያደርግላት ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች፤ ይኸውም መጥፎ ሐሳብ በልቧ ውስጥ እንዳይሠርጽና ልቧ በጭራሽ ከፍቅር አምላካዊ እየቀዘቀዘ እንዳይኼድ ነበረ፤ ንግግሯ የተረጋጋ እና ድምፆቿም ዝግ ያሉ ናቸው፤ በየቀኑም መንፈሳዊ ርምጃ (ብቃታዊ መሻሻል ዕድገት) ማድረግ ትፈልጋለች፤ በየቀኑም ያነን ታደርጋለች፤ በጠዋት ስትነሣም ከዚኽ በፊት አስቀድማ ከሠራቻቸው አስበልጣ ሥራዎቿን ለመሥራት ትፈልጋለች፤ ሞትን ፈጽማ አትፈራም ነበር ይልቁኑ በሐዘን ኹና የመንግሥተ ሰማያት መዠመሪያ (መግቢያ) እንዳላቋረጠች በየቀኑ እያየች በጸሎቷ ታነሣለች) በማለት የደናግል መመኪያነቷን በስፋት ገልጾታል፡፡
ምንጭ፡- ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፤ ነገረ ማርያም በሊቃውንት ክፍል 1 እና ክፍል 2 ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ [በድጋሚ ፓስት የተደረገ)
[የአማናዊት መቅደስ የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፤ መልካም በዓል፡፡]
[ጸሎቷ እንዲጠብቀን በረከቷ እንዲትረፈረፍልን ወደ ቤተ መቅደስ መግባቷን አስመልክታችሁ እጅግ አብዝተን የምንወዳት የፈጣሪያችን የክርስቶስ እናትን አመስግኗት]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
#ልዳ_ሚዲያ
youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
1 week ago | [YT] | 240