ልዳ ሚዲያ - Leda Media

#አባ_ሣሙኤል_ዘዋልድባ

#በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሳሙኤል ዘዋልድባ ዓመታዊ ዕእረፍት ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን

ፃድቁ #አባ_ሳሙኤል አባቱ እስጢፋኖስ እናቱ አመተ ማርያም በአክሱም አካባቢ በ14 ኛው ክ/ዘመን ተወለደ ዕድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ቅዱሳት መፅሐፍትን ተምሯል ከወላጆቹ ዕረፍት በኋላ ወደ ደብረ በንኮል ገዳም በመሄድ ሥርዓተ ምንኩስናን ከአባ አድኃኒ እጅ በመቀበል በገዳሙ ውስጥ መነኮሳቱን በትጋት ያገለግል ጀመር

ዘመዶቹ ወደ እርሱ እየመጡ በአስቸገሩት ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ #በፆምና_በስግደት በመቆም ተጋደለ ከዚያም ወደ ሌላ በርሃ ሄዶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ምንም ምን ሳይቀምስ በፆም ኖረ

በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ ተከዜ በደረሰበት ወቅት የተከዜ ወንዝ ሞልቶ የማያሻግረው ሲሆን በትእምርተ መስቀል ባርኮ በአንድ እጁ መጽሐፍ በሌላ እጁ መብራት እሳት ይዞ ገብቶ #መብራቱ_ሳይጠፋ_መፅሐፉ_ሳይበሰብስ ተሻግሮ ዋልድባ ገብቷል

አባታችን #የዋልድባ_ገዳም መሥራች በመሆኑም "አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ" በመባል ይታወቃል በዚህም ገዳም ገድሞ ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማረ በፆም በፀሎት ፀንቶ ሰውነቱን በመግረፍ መዝሙረ ዳዊትን በቀን 5 ጊዜ በማድረስ ከእመቤታችን ፍቅር የተነሣ ውዳሴ ማርያምን እና ቅዳሴ ማርያምን በቀን 64 ጊዜ በዕድሜዋ ልክ ይፀልየው ነበር

ዋልድባ ገዳምን በእጁ እንደ መሶብ ይዞ አስባርኳታል ከሰማይም #የወርቅ_መስቀል ወርዶለታል በተጋድሎው ጽኑዕ ስለነበር ሰይጣን በሚያስፈሩ አራዊት እየተመሰለ ይፈታተነው ነበር፡፡

ብዙ አናብስት እየተከተሉ ግማሾቹ ለመፅሐፍት መያዣ ግማሾቹ ለዕቃ መያዣ ሆነው #የአባ_ሳሙኤልን የእግራቸውን አቧራ እንደ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብስት እየላሱ ይኖሩ ነበር

በቅዳሴ ጊዜ #ቅዳሴ_ማርያምን ሲቀድሱ ከመሬት ሦስት ክንድ ከፍ ይላሉ በዚህም በውኃ ላይ ቅዳሴ ማርያምን ደግመው ቢባርኩት ኅብስት ሆኖላቸዋል

ለዚህም መታሰቢያ እመቤታችን #ለአባ_ሳሙኤል የሚያበራ ዕንቁ እና ንጹሕ ዕጣን ሰጠችው ከዚህም በተጨማሪ በአርያም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ያጥን ነበር የብቃት ደረጃ ላይ ስለደረሱ አባ ሳሙኤል በዋልድባ አባ ብንያም በግብፅ አባ አንበስ በሐዘሎ ሆነው ይተያዩ ነበር

እነዚህ ሦስቱ ቅዱሳን ተቀጣጥረው ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ወደ ምድረ ከብድ በሔዱበት ጊዜ የተጫኑባቸውን አናብስት የአቡነ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ አናብስት ሰባብረው በሏቸው

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ፈጣሪ ያላዘዘላችሁን ለምን በላችሁ ብሎ እንዲተፏቸው አዝዞ ሕያዋን አድርጎላቸዋል ከዚህ በኋላ ቡራኬ ተቀብለው መንፈሳዊ ጨዋታ ተጨዋውተው #በአናብስታቸው ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል፡

የአባ ሳሙኤል ዕረፍታቸው በተቃረበ ጊዜ #ቅዱስ_ሚካኤል በክንፉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ወስዶ #ከእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አቀረባቸው፡፡

አምላካችን #እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶላቸው ከሰማይ ተመልሰው በታኅሣሥ 12 ቀን #በክብር_አርፈዋል ፍልሰተ ዐፅማቸው ከብዙ ጊዜ በኋላ ከዋልድባ ወደ ደብረ ዐባይ መስከረም 6 ቀን ተዛዉሯል

የፃድቁ አባታችን #አባ_ሣሙኤል ዘዋልድባ ረድኤት በረከታቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን ምልጃ ፀሎታቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን "አሜን"

#ልዳ_ሚዲያ
#ቤተ_ልዳ_ሚዲያ

youtube.com/@Ledamedia
t.me/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL

1 day ago | [YT] | 163