ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

እንኳን ወደ ሄመንዘተዋህዶ ቲዩብ በሠላም መጣችሁ!! በዚህ ቻናሌ ላይ የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ትምህርቶችን፣ ዝማሬዎችን፣ እንዲሁም መንፈሳዊ መረጃዎችን የማቀርብበት ነው። የማቀርብላችሁም ናታን ዘ ተዋሕዶ እባላለሁ

ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ‼️‼️
Welcome to hemen zetewahdo Tube! On this channel, I present various Orthodox Tewahedo spiritual teachings, chants, and spiritual information. My name is Nathan the Tewahedo Become a family by subscribing ‼️‼️


ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

ባርከኒ አባ እንሳእ በረከተከ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ሳሙኤል አባ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ"
"ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግዚእትነ ወመድኃኒትነ"
አቡነ ሳሙኤል
በስመአብ🌹ወወልድ🌹ወመንፈስ ቅዱስ🌹አሀዶ አምላክ🌹አሜን🌹እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ዓመታዊ የዕረፍት በዐል አደረሰን አደረሳችሁ።
አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ታህሳስ 12 በዓለ ዕረፍታቸው አባ ሳሙኤል አባቱ እስጢፋኖስ እናቱ አመተ ማርያም በአክሱም አካባቢ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተወለደ፡፡ ዕድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ቅዱሳት መጽሐፍትን ተምሯል፡፡ ከወላጆቹ ዕረፍት በኋላ ወደ ደብረ በንኮል ገዳም በመሄድ ሥርዓተ ምንኩስናን ከአባ አድኃኒ እጅ በመቀበል በገዳሙ ውስጥ መነኮሳቱን በትጋት ያገለግል ጀመር ዘመዶቹ ወደ እርሱ እየመጡ በአስቸገሩት ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ በጾምና በስግደት በመቆም ተጋደለ፤ ከዚያም ወደ ሌላ በርሃ ሄዶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ምንም ምን ሳይቀምስ በጾም ኖረ፡፡ በአንዲት ዕለትም በጐዳና ሲጓዝ ተከዜ በደረሰበት ወቅት የተከዜ ወንዝ መልቶ የማያሻግረው ሲሆን በትእምርተ መስቀል ባርኮ በአንድ እጁ መጽሐፍ በሌላ እጁ መብራት እሳት ይዞ ገብቶ መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉ ሳይበሰብስ ተሻግሮ ዋልድባ ገብቷል የዋልድባ ገዳም መሥራች በመሆኑም አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህም ገዳም ገድሞ ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማረ በጾም በጸሎት ጸንቶ ሰውነቱን በመግረፍ መዝሙረ ዳዊትን በቀን 5 ጊዜ በማድረስ ከእመቤታችን ፍቅር የተነሣ ውዳሴ ማርያምን እና ቅዳሴ ማርያምን በቀን 64 ጊዜ በዕድሜዋ ልክ ይጸልየው ነበር፡፡ዋልድባን በእጁ እንደ መሶብ ይዞ አስባርኳታል፤ ከሰማይም የወርቅ መስቀል ወርዶለታል፡፡ በተጋድሎው ጽኑዕ ስለነበር ሰይጣን በሚያስፈሩ አራዊት እየተመሰለ ይፈታተነው ነበር፡፡ብዙ አናብስት እየተከተሉ ግማሾቹ ለመጽሐፍት መያዣ፣ ግማሾቹ ለዕቃ መያዣ ሆነው የአባ ሳሙኤልን የእግራቸውን አቧራ እንደ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብስት እየላሱ ይኖሩ ነበር፡፡🌹
በቅዳሴ ጊዜ ቅዳሴ ማርያምን ሲቀድሱ ከመሬት ሦስት ክንድ ከፍ ይላሉ፤ በዚህም በውኃ ላይ ቅዳሴ ማርያምን ደግመው ቢባርኩት ኅብስት ሆኖላቸዋል፤ ይህንንም"ሶበ ዐተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ ረስዮ ኅብስተ ጽጌ ሃይማኖት ሳሙኤል ዘሐቅለ ወዐሊ" ብሎ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲው አባ ጽጌ ድንግል ገልጾታል፡፡ለዚህም መታሰቢያ እመቤታችን
ለአባ ሳሙኤል የሚያበራ ዕንቁ እና ንጹሕ ዕጣን ሰጠችው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአርያም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ያጥን ነበር፡፡ የብቃት ደረጃ ላይ ስለደረሱ አባ ሳሙኤል በዋልድባ ፣ አባ ብንያም በግብጽ ፣ አባ አንበስ በሐዘሎ ሆነው ይተያዩ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስቱ ቅዱሳን ተቀጣጥረው ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ወደ ምድረ ከብድ በሔዱበት ጊዜ የተጫኑባቸውን አናብስት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብስት ሰባብረው በሏቸው፤አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ፈጣሪ ያላዘዘላችሁን ለምን በላችሁ ብሎ እንዲተፏቸው አዝዞ ሕያዋን አድርጎላቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቡራኬ ተቀብለው መንፈሳዊ ጨዋታ ተጨዋውተው በአናብስታቸው ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል፡፡የአባ ሳሙኤል ዕረፍታቸው በተቃረበ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል በክንፉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ወስዶ ከእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አቀረባቸው፡፡🌹
እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶላቸው ከሰማይ ተመልሰው በታኅሣሥ 12 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ ፍልሰተ ዐጽማቸው ከብዙ ጊዜ በኋላ ከዋልድባ ወደ ደብር ዐባይ መስከረም 6 ቀን ተደርጓል የጻድቁ አባታችን አባ ሣሙኤል ዘዋልድባ ረድኤት በረከት አይለየን
🌹🌹🌹🌹🌹ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🌹🌹🌹🌹🌹ወለወላዲቱ ድንግል
🌹🌹🌹🌹🌹🌹ወለመስቀሉ ክቡር

7 hours ago | [YT] | 254

ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው🎤
ለጶርዓ ሰው ለማኑሄ እንደነገረው
በመሰዊያው ነበልባል ዉስጥ ዐረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/🙏💖
† † †
ከዳን ወገን የሆነ በእግዚአብሔር ያመነ
ማኑሄ የሚባል ሰው የጌታ መልአክ ታየው
ሚስቱ መካን ነበረች ልጅንም ያልወለደች
ሚካኤል ተገልጦላት በዘር ፍሬ ባረካት
‹‹የእግዚአብሔር መልአክ››

8 hours ago | [YT] | 261

ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን የምሕረትና የመዳኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 12፥1 በማለት በነቢዩ ዳንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ ቦታ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 10፥13 በማለት ያስረዳል፡፡ በዚህ ቃል ላይ ከዋንኞቹ አለቆች አንዱ የሚለውን በመያዝ ሚካኤል ብቻ የመላእክት አለቃ አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን የሌሎች አለቅነት የተወሰነ ወይም ዝቅተኛ ሲሆን በአንድ ነገድ ላይ በአንድ የመላእክት ከተማ ላይ ነው፡፡የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት ግን በመላእክት ሁሉ ላይ ከሆነ ከሌሎቹ ይለያል፡፡ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ እንደተገለጸው ሰባት ሊቃነ መላእክት ቢኖሩም አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ቅዱስ ሚካኤል አርምሞ ትዕግሥትን የሚወድ መልአክ ነው፡፡የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር በተሰጠው ኃይል ዲያብሎስን ድል የነሣ መልአክ ነው፡፡በሰማይ ጦርነት ተነሣ ሚካኤልና እርሱ መላእክት ከዘንዶው ከመላእክቱም ጋር ተዋጉ ራእይ ዮሀንስ ምዕራፍ 12፥7 ይላል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሀገራችንን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን፣ እኛን ልጆችህንም አንተ በያለንበት ሁሉ ጠብቀን አማላጅነትህ ረድኤትህና በረከትህ አይለየን፡፡🌹💒🌹
በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፡፡ በዚች ቀን በዚህ ወር እግዚአብሔር ወደባቢሎን አገር ላከው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሦስቱን ልጆች አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ በጣላቸው ጊዜ አራተኛ ገጽ ሁኖ ታየ። የእሳቱም ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ወላይ ከፍ ከፍ አለ የጨመሩአቸውን ሰዎችና እሳት የሚያንዱትን አቃጠላቸው ይህም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሠለስቱ ደቂቅ ላይ አጥፍቶ አዳናቸው ምንም አልነካቸውም እንደ ቀዘቀዘ እንደ ጧት ጤዛ አድርጎታልና።በዚያንም ጊዜ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበርይመስገን እያሉ ስድስት ቃላትን ተናገሩ በዚህም ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ ትንቢት ተናገሩ። ከዚህም በኋላ የጌታ እግዚአብሔር ሥራዎቹ ሁሉ ያመሰግኑታል እርሱ ለዘላለሙ ምስጉን ልዑልም ነው እያሉ ሠላሳ ሦስት ጊዜ አመሰገኑት በዚህም በምድር ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ክርስቶስ እንደሚኖር አመለከቱ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ እንድናደርግ ሥዓትን ሠሩ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።🌹💒🌹

9 hours ago | [YT] | 183

ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

የሠራዊት ጌታ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋይ መላዕክት” 🙏

የስሙ ትርጓሜ “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነውከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ማታ ይለምናሉ። የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስፅህ አለው እንጂ የስድብን ቃል አልተናገረውም ሲባል ሰምተናል፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበርና ከነዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ ሲወጣ 2 መላዕክት በአረጋውያን ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ ቢያይ ላግዛቹ ብሎ መቆፈሪያውን ተቀበላቸው፡፡

በመጨረሻ “ሰውየው በአንተ ልክ ነውና እስቲ ገብተህ ለካልን” አሉት፡፡ እሱም በየዋህነቱ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ እንደተኛ እንደ እንቅልፍ አሸልቦት በዚያው ዐረፈ፤ መላዕክቱም ቀበሩት። እስራኤላዊያን ሙሴን እጅግ ስለሚወዱት የሙሴን መቃብር እንደ ጣዖት እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ሰወረው፤ ነገር ግን ጠላት ዲያቢሎስ ሊያሳያቸው በመነሳቱ ቅዱስ ሚካኤል ተቃወመው፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን እግዚአብሔር ይገስጽህ ብሎ ከእርሱም ሰወረበት። በሐዋርያው ይሁዳ መልዕክት ቁጥር 8 የሚገኘው ቃል የቅዱስ ሚካኤልን ትዕግስት ያሳያል፡፡ ዳግመኛም አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በአይሁድ ስራ አዝኖ፣ ፈጣሪን ፍጡራን ሲሰቀሉት የትዕግስቱንና የፍቅሩን ብዛት እያየ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ።

መላዕክቱ በክንፋቸው የእግዚአብሔር ስም ስለተፃፈበት ህዝቡን ይጠብቃሉ፤ የመላዕክቱን ስም የመጨረሻውን ፊደል ስናይ ኤል ብሎ ይጨርሳል፡፡ ሚካ-ኤል ገብር-ኤል ኡራ-ኤል፡፡ ይህም “ስሜ በሱ ላይ ነውና” እንደሚል የእግዚአብሔር የምህረት ስም ስለሆነና በክንፎቻቸው ስለተፃፉ መላዕክቱ ይጠብቁናል። “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል” ተብሎም በመዝሙር 90÷11 ተጽፋልና አህዛብን ጭምር ያለጊዜያቸው እንዳይሞቱ መላዕክት ይጠብቋቸዋል!!! ቅዱስ ሚካኤል ሰኔ 12 ቀን ዲያቢሎስን ጥሎ በምትኩ ሊቀ መላዕክት ሆኖ የተሾመበትና አፎምያንም የረዳበት ቀን ስለሆነ በታላቅ ሥርዓት ይከበራል። ህዳር 12 ሕዝበ እስራኤልን በክንፎቹ ጥላ ከበረሃው ፀሐይ ከልሎ ከግብጽ ምድር እየመራና እየጠበቀ ከንዓን ያገባቸው እለት ነው።

በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለትረ በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡

20 hours ago | [YT] | 1,166

ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

† ስንክሳር ዘወርኀ ታኅሣሥ ፲፩ †

=>አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ አንድ በዚች ቀን የግብጽ ደቡብ ከሆነ ከመጺል አውራጃ ከሬስ ከተማ ሰዎች ወገን የሆነ ቅዱስ አባት አባ በኪሞስ አረፈ።

እርሱም የአባቱን በጎች የሚጠብቅ ነበር ዕድሜውም ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲሆነው ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ በጐልማሳ አምሳል ተገለጠለትና በአንድነት ሒደን እንመነኵስ ዘንድ ትሻለህ አለው እርሱም አዎን አለ ሁለቱም ተስማምተው ወደ አስቄጥስ ገዳም በአንድነት ተጓዙ ሦስት አረጋውያን መነኰሳትንም አገኙ አባ በኪሞስም ከእነርሱ ጋር ሃያ አራት ዓመታትን ኖረ።

ከዚህም በኋላ አባ በኪሞስ ከዚያ ተነሥቶ የሦስት ቀን ጐዳና ያህል ተጓዘና ሩቅ ወደ ሆነ በረሀ ውስጥ ገባ ሰይጣናትም በእሪያዎችና በዘንዶዎች አምሳል ሁነው መጡበት ሊነክሱትም አፋቸውን ከፍተው ከበቡት እርሱ ግን የአጋንንትን ሐሳብ አወቀ በእግዚአብሔርም ኃይል እፍ አለባቸው በዚያንም ጊዜ ተበተኑ።

እርሱም ወንዝ አገኘ ሰባት ሰባት ቀን እየጾመ በዚያ ሦስት ዓመት ኖረ በሱባዔውም መጨረሻ በመሀል እጁ ተምር መልቶ ያንን ይመገባል ውኃም በጥቂቱ ይጠጣል ሁለት ሽህ አራት መቶ ጊዜ በሌሊት እንዲሁም በቀን ሁለት ሽህ አራት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ይጸልያል።

ከዚህም በኋላ አርባ አርባ ቀን እየጾመ ሃያ አራት ዓመታት ያህል ኖረ አርባውም ቀን ሲፈጸም አንድ ጊዜ ይበላል ከዚህም በኋላ አንድ ጊዜ ቆዳው ከዐጥንቶቹ ጋር እስቲጣበቅ ሰማንያ ቀን ጾመ በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ይበላና ይጠጣ ዘንድ እንጀራና ውኃን አመጣለት ያም ውኃና እንጀራ ሳያልቅ እስከ አረፈ ድረስ ብዙ ዓመታትን ኖረ።

ፈጣሪ እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ ተገልጦ ወደ አገሩ እንዲመለስ አዘዘው በዚያንም ጊዜ ተነሥቶ ሔደ ወደ አገሩም ደርሶ በዚያ ታናሽ ማደሪያ ጎጆ ሠርቶ በውስጡ ብቻውን የሚኖር ሆነ ወደርሱም ለሚመጣ ሁሉ መጠጊያና ወደብ በጎ አለኝታም ሆነ ሰዎችም ሁሉ በትምህርቱ እየተጽናኑ ኖሩ ንጹሕ በሆነ አምልኮቱ በትሩፋቱና በተጋድሎው መንፈሳዊ ቅናትን ይቀኑበት ነበር።

በአንዲት ዕለትም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተሸክሞ ወደ ኤፍራጥስ ምድር አደረሰው የዚያ አገር ሰዎች በመተላለፍ ከእውነተኛ ሃይማኖት ወጥተው ነበርና ሁሉንም ወደ ቀናች ሃይማኖትና ወደ በጎ ምግባር መለሳቸው ከዚያም ወደ ቦታው ተመለሰ።

አንድ ጊዜም ሽጦ ምግቡን ያገኝ ዘንድ አገልግሎችን ተሸክሞ ወደ ከተማ ሲሔድ በጎዳና ላይ ደክሞት አገልግሎቹን አስቀምጦ ጥቂት ያርፍ ዘንድ ተቀመጠ በዚያንም ጊዜ ከአገልግሎቹ ጋር የእግዚአብሔር ኃይል ተሸክሞ ወደሚሻው ቦታ አደረሰው።

በዚያንም ወቅት አባ ሲኖዳ ከፍተኛ የዕንቈ ባሕርይ ምሰሶ በራእይ አየና ይህ ታላቅ ምሰሶ ምንድን ነው ብሎ ደነገጠ የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦ ይህ አባ በኪሞስ ነው አለው። አባ ሲኖዳም ወዲያውኑ ተነሥቶ ወደ አባ በኪሞስ አገር እስቲደርስ በእግሩ ተጓዘ ከዚያችም ቀን በፊት ከቶ አላየውም ነበር በተገናኙም ጊዜ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ።

አባ በኪሞስም ወጥ ሊአበስል ወደደ አባ ሲኖዳንም ይቺን እንስራ ያዛትና ሔደህ ውኃ ቀድተህ መልተህ አምጣልኝ አለው በዚያንም ጊዜ አባ ሲኖዳ ተነሣና ያቺን እንስራ ተሸከማት ውኃውንም ቀድቶ መልቶ አመጣለት ወጡንም ፈልቶና በስሎ አገኘው በዚያንም ጊዜ አባ በኪሞስ መሆኑን አወቀ ከእርሱም ጋር ሰላምታን ደገመ እጅ በመነሣሣትም ሰላምታ ተለዋወጡ።

ከዚህም በኋላ አባ ሲኖዳ ስለርሱ ያየውን ራእይ ነገረው በእርሱም ዘንድ ጥቂት ቀኖች ኖረ።

ዳግመኛም በአንዲት ቀን በአንድነት ሲጓዝ የሞተ ሰው ራስ አገኙ አባ ሲኖዳም በበትሩ ነቅነቅ አደረገውና ምውት ሆይ ያየኸውን ትነግረንና ታስረዳን ዘንድ ተነሣ አለው በዚያን ጊዜ ነፍሱ ወደ ዐፅሙ ተመልሳ ሥጋ ለብሶ ተነሣና ሰገደላቸው በሲኦል የሚሠራውንም ሁሉ በየወገናቸውም በውስጧ የሚሠቃዩትን እርሱም አረማዊ እንደሆነ ነገራቸው። እንዲህም አለ ክብር ይግባውና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያመኑ ትእዛዙን ግን ያልጠበቁ በአሕዛብ ሥራና በአረማውያን ርኵስት የኖሩ ከእኛ በታች የሚኖሩ ክርስቲያኖች አሉ አለ ቅዱሳንም ተመልሰህ ተኛ አሉት ወዲያውኑ እንደ ቀድሞው ሆነ።

ከዚህም በኋላ አባ ሲኖዳ ቅዱስ በኪሞስን ተሰናብቶ ወደ ቦታው ተመለሰ። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ቅዱስ አባ በኪሞስ አገልጋዩን ጠርቶ በኖረበት ቦታ ሥጋውን እንዲቀብር አዘዘው። ከዚህም በኋላ በሆድ ዝማ ሕመም ጥቂት ታመመ። ቅዱሳንን በአንድነት ወደርሱ ሲመጡ አያቸው በዚያንም ጊዜ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። መላእክትም ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እስከአደረሷት እያመሰገኑና እየዘመሩ አሳረጓት።

መላ ዕድሜውም ሰባ ዓመት ሆነ ዐሥራ ሁለት ዓመት በዓለም ውስጥ ሃምሳ ስምንት ዓመት በምንኵስና ሥራ ኖረ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለከ ፀዋሬ ክቡድ አስፈሬዳ። ወመንሥኤ ምውት በምድረ በዳ። ዐስበ ፃማከ በኪሞስ ወዘተቀንዮትከ ፍዳ። መንበረ ብርሃናዌ ወአክሊለ ክብር ፀዓዳ። እግዚአብሔር አርአዩ ለአባ ሲኖዳ።
፨፨፨

=>በዚችም ቀን የኤጲስቆጶሱ በርተሎሜዎስና የሰማዕቱ በጥላን መታሰቢያቸው ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
፨፨፨
አርኬ
ሰላም ለከ በርተሎሜዎስ አቡነ። ዘደለወከ በርትዕ ኤጲስቆጶሰ ከዊነ። እምጽድቅ ኲሉ ዘይጸንሐነ። ኃይለ ጸሎትከ ይዕቀብ ኪያነ። በአምሳለ ብንት ዘየዓቅብ ዐይነ።
ሰላም ለልደትከ ቴዎድሮስ ፍሡሐ ገጽ። አምሳለ ፍሬ ሥርናይ ወፍሬ ሠናይ ዕፅ። ውስተ ፍኖትከ ሚጠኒ እምነ ፍኖትየ ዘዳኅጽ። በእንተ ሥጋከ በዝብጠተ በትር ቅሩጽ። ወበእንተ ዐፅምከ ካዕበ በማኅረፅ ኅሩፅ።
፨፨፨

=>ታሕሳስ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ታላቁ አባ በኪሞስ
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ
3.ቅዱስ ቴዎድሮስ
4.ቅዱስ በጥላን

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
5.ቅድስት ሐና ቡርክት

=>+"+ በእሸቅድምድም ሥፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ: ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ:: የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል:: እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው:: እኛ ግን የማይጠፋውን:: +"+ (1ቆሮ. 9፥24)

፨፨፨

ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውክፈ እምእለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሂቅ እምንኡስ ሕፃን።
ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶ።
( ጌታ ሆይ ከብልፅግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

1 day ago | [YT] | 674

ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

ፑቲን ከእግዚአብሔር የተሰጠን ስጦታ ነዉ

የሩሲያ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ፑቲን “ከላይ የመጣ ስጦታ” ሲሉ መናገራቸው ተሰማ ።

የሩሲያ ከፍተኛ ጳጳስ ለፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በአሁኑ ጊዜ ሩሲያን መምራታቸዉ እንደ መለኮታዊ ሞገስ እና ስጦታ አድርገው አቅርበዋል። “ፑቲን በእርግጥ ከላይ የተሰጠ ስጦታ ነው።” ሲሉ ተናግረዋል ።

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኃላፊ ፓትሪያርክ ኪሪል ይህንን ያሉት በሞስኮ ክሪላትስኮዬ አውራጃ በሚገኘው የቅዱስ ቭላድሚር ታላቁ ቤተክርስቲያን በስብከት ወቅት ለምዕመናን ሲሆን ሩሲያውያን “በጣም በበለጸገ ዘመን” ውስጥ እየኖሩ ነው ምክንያቱም ፑቲን “ከዛሪስት ዘመን ጀምሮ የመጀመሪያው የኦርቶዶክስ ፕሬዝዳንት” በመሆናቸው ብለዋል

ፓትርያርኩ የፑቲንን የግል እምነት ደጋግመው አወድሰው ፣ “የጥሩ ክርስቲያን ምሳሌ” ብለው ጠርተውታል፣ ፕሬዚዳንቱንም ቤተክርስቲያን ለመገኘት ወይም ቁርባን ለመቀበል የማያፍር “ቅን አማኝ” ሲሉ ገልጸውታል።

አክለዉም ኪሪል ሩሲያውያን ቤተክርስቲያኗንም ሆነ መንግሥቱን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፣ አገሪቱን ከመንገዷ ለማዞር እየሞከሩ ነው በማለት የውጭ ተጽዕኖዎች አስጠንቅቀዋል።
ሩሲያውያን ለፕሬዚዳንቱ እንዲጸልዩ አሳስበዋል።

ለአገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለአመራሯም ምስጋና ያቀረቡት ጳጳሱ ። “ስለዚህ፣ ለምንኖርባት ሀገር እግዚአብሔርን እና በግልጽ ለመንግስት… እና ሩሲያ ዛሬ ላለችበት ጥንካሬ ሁሉ ምስጋናችንን ማቅረብ አለብን” ብለዋል ሲል moscow times ዘግቧል ።

በሌላም በኩል የሩሲያን ጠንካራ አቋም ከምዕራቡ ዓለም ውድቀት ጋር አነጻጽሯል። ‘በማንም አንፈርድም፣ ነገር ግን የዚያ ማህበረሰብ መንፈሳዊ እና ሥነ ምግባራዊ ቀውስ ሙሉ በሙሉ ግልጽ ነው’ ብለዋል፣ ማህበረሰቦች ሰዎችን ለማስደሰት በ‘ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ካፒታል’ ላይ ብቻ የተገነቡ መሆናቸውን አክለዋል ሲል digi24.ro ዘግቧል።

በጠንካራ ኦርቶዶክሳዊ እምነታቸው የሚታወቁት የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከዩክሬንና ሀይማኖትና ማንነትን ለማጥፋት ዙርያዉን ካሰፈሰፉ ጋር ግጭት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በክሪምሊን እና በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መካከል ያለውን የጠበቀ ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል ።

1 day ago | [YT] | 49

ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቅድስት ድንግል እናቱ እና የቅዱሳኑ ወዳጅ ውድ አባቴ ባሕታዊ ቅዱስ አባታችን እውነተኛ መናኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ትምህርቷን ከጉባኤ ቤት ተምረው የተማሩትን በትክክል የኖሩ ከሥውራኑ እና ከግሑሳኑ ጋር አብረው የኖሩ እርሶም እንደእነርሱ የሆኑ ርህሩህ ከሰዉ ሸሽተው ተደብቀው የኖሩ እጅግ ጸሎተኛ ርኩሳን መናፍስት እርሶን ሲያዩ ደንግጠው እንደ አመድ እንደ ጉም የሚበተኑ።

በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በውጪ አገር ያሉ በዋሻ የሚኖሩ ቅዱሳን ባሕታውያን የእርሶን ማንነት ቅድስና አውቀው ያላቸውን አስኬማ እና የጸሎት መቍጠሪያቸውን ልከው "አባታችን በጸሎት ያስቡን" የሚሎት።

በጸሎቶ ብዙዎችን ከችግራቸው ያዳኑ የታመሙትን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የሚፈውሱ ታላቅ የትንቢት ጸጋ ያሎት።

ለኔ ለኃጥያተኛ ልጅዎ ደግሞ ከወላጅ አባት በላይ ቅርብ ለሆኑት ችግሬን ይሁን ምንም ዓይነት ንግግሬን ሳይሰለቹ ለሚያዳምጡኝ መጥፎ ሆኜ ሳላ እንደ ተወዳጅ ልጅ አጠገቦ አስቀምጠው በፈገግታ ለሚያዩኝ 😢😢😢

ታላቁ አባቴ ባሕታዊ አባ ኃይለ ኢየሱስ በሥጋ ስለተለዩን እጅግ ልቤ ተሰብሯል የልጆቾ ልብ ተሰብሯል ነገር ግን በነፍስ በጌታችን መንበር ፊት ኢትዮጵያን እና መላውን ዓለም እኛን ልጆቾን እንደማይረሱን አምናለሁ።

ይህ የተጻፈው ከልብ ስብራት የተነሳ ቃላት አንሶኝ ነው ከዚህ በላይ ምንም መጻፍ አልችልም ከቅዱስ አባታችን ጋር ያየሁ እጅግ ብዙ ነገሮች ራሱን የቻለ ጊዜ ተመድቦ እንደ ጌታችን ፍቃድ የምንጽፍላችሁ ሲሆን ነገር ግን በአንድ መንፈሳዊ ወዳጄ ጥያቄ እንዲሁም ግፊት ምክንያት ይህችን ጽሑፍ ለበረከት እንዲሆን ጽፌላችኋለሁ።

ዋናው ነገር በኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ እምነት እንዲያጸናን እና እንደነዚህ ያሉ ቅዱሳን አባቶችን እና ቅዱሳት እናቶችን እንዲያሳየን አሳይቶንም በእምነታቸው መስለናቸው በእነርሱ መንገድ ሄደን ወደ መንግሰተ ሰማይ እንድንገባ ነው።

የቅዱሱ አባት የባሕታዊ የአባ ኃይለ ኢየሱስ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

1 day ago | [YT] | 1,256

ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

❤🙏ፃድቁ አባታችን አቡነ ኪሮስ በምልጃ ፀሎታቸው ሀገራችንን ህዝባችንን ያስቡልን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸው አይለየን
አሜን...🙏!!!

4 days ago | [YT] | 2,076

ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

ታህሳስ 8/2018 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ኪሮስ
#ፆመ_ነብያት_24ኛ_ቀን

የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ የልደት መታሠቢያ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #አቡነ_ኪሮስ አባታቸው ንጉስ ዮናስ እናታቸው እንስራ
ይባላሉ እሊህም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው ሀገራቸው ሮም ሲሆን በታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ የመጀመሪያ ስማቸው ዲላሶር ይባል ነበር

👉በኋላ አባታቸዉ ከሞቱ በኋላ ሀብት ንብረታቸዉን ተካፍለዉ ለድሆች ከመፀወቱ በሑዋላ ከአባ #በቡነዳ_ገዳም ገቡ

👉በ17 አመታቸው ስርአተ ምንኩስናን ተምረው ከአባ በቡነዳ እጅ ስርአተ #ምንኩስናን ተቀበሉ ከዚህ በሁዋላ በፆምና በፀሎት ተወስነው ኖሩ

👉ስለ አለም መከራ ለ 40 ዘመን ተኝተው ሲፀልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ #መላዕክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡርን ቃል ሰምቶ ወድቋልና ጌታም ድምፁን ያሰማኝ አሏቸው በኋላም #ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይቷቸው በመጨረሻም ጌታችን ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል

👉ቃል ኪዳናቸውም መካኖችን ልጅ የሌላቸው #ገድላቸውን
አቅፈው ቢያለቅሱ #ፀበሉን ቢጠጡ ስምሕን ቢጠሩ የመካኒቱን ማሕፀን እከፍታለሁ

👉ህፃናት የሚሞትባቸው #እንዳይሞትባቸው አደርጋለሁ በንፁህ ገንዘቡ ቂም እና በቀልን ሳይዝ በሕግ በስጋ ወደሙ ለፀና ሰው በስምህ በተሰራው #ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ እሰጠዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል

👉ከዚህም በኋላ በተወለዱ በ 270 አመታቸው ሐምሌ 8 ቀን አርፈዋል #የፃድቁ_አቡነ_ኪሮስ ረድኤት በረከታቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን የቅዱሳን #አበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ታህሣሥ 8/2018

4 days ago | [YT] | 2,289

ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

በረኸትን ጸሎትን ናይ ቅዱስ ሙሴ ምስ ኩላትና ይኩን፡ ፫ ኣሜን።
፰ ታሕሳስ ፳፻፲ወ፰ - 8 Tahsas 2018.
Bereketn Tselotn Nay Kidus Mussie Mis Kulatna Yekun, 3 Amen.

4 days ago | [YT] | 843