ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

ፑቲን ከእግዚአብሔር የተሰጠን ስጦታ ነዉ

የሩሲያ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ፑቲን “ከላይ የመጣ ስጦታ” ሲሉ መናገራቸው ተሰማ ።

የሩሲያ ከፍተኛ ጳጳስ ለፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በአሁኑ ጊዜ ሩሲያን መምራታቸዉ እንደ መለኮታዊ ሞገስ እና ስጦታ አድርገው አቅርበዋል። “ፑቲን በእርግጥ ከላይ የተሰጠ ስጦታ ነው።” ሲሉ ተናግረዋል ።

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኃላፊ ፓትሪያርክ ኪሪል ይህንን ያሉት በሞስኮ ክሪላትስኮዬ አውራጃ በሚገኘው የቅዱስ ቭላድሚር ታላቁ ቤተክርስቲያን በስብከት ወቅት ለምዕመናን ሲሆን ሩሲያውያን “በጣም በበለጸገ ዘመን” ውስጥ እየኖሩ ነው ምክንያቱም ፑቲን “ከዛሪስት ዘመን ጀምሮ የመጀመሪያው የኦርቶዶክስ ፕሬዝዳንት” በመሆናቸው ብለዋል

ፓትርያርኩ የፑቲንን የግል እምነት ደጋግመው አወድሰው ፣ “የጥሩ ክርስቲያን ምሳሌ” ብለው ጠርተውታል፣ ፕሬዚዳንቱንም ቤተክርስቲያን ለመገኘት ወይም ቁርባን ለመቀበል የማያፍር “ቅን አማኝ” ሲሉ ገልጸውታል።

አክለዉም ኪሪል ሩሲያውያን ቤተክርስቲያኗንም ሆነ መንግሥቱን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፣ አገሪቱን ከመንገዷ ለማዞር እየሞከሩ ነው በማለት የውጭ ተጽዕኖዎች አስጠንቅቀዋል።
ሩሲያውያን ለፕሬዚዳንቱ እንዲጸልዩ አሳስበዋል።

ለአገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለአመራሯም ምስጋና ያቀረቡት ጳጳሱ ። “ስለዚህ፣ ለምንኖርባት ሀገር እግዚአብሔርን እና በግልጽ ለመንግስት… እና ሩሲያ ዛሬ ላለችበት ጥንካሬ ሁሉ ምስጋናችንን ማቅረብ አለብን” ብለዋል ሲል moscow times ዘግቧል ።

በሌላም በኩል የሩሲያን ጠንካራ አቋም ከምዕራቡ ዓለም ውድቀት ጋር አነጻጽሯል። ‘በማንም አንፈርድም፣ ነገር ግን የዚያ ማህበረሰብ መንፈሳዊ እና ሥነ ምግባራዊ ቀውስ ሙሉ በሙሉ ግልጽ ነው’ ብለዋል፣ ማህበረሰቦች ሰዎችን ለማስደሰት በ‘ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ካፒታል’ ላይ ብቻ የተገነቡ መሆናቸውን አክለዋል ሲል digi24.ro ዘግቧል።

በጠንካራ ኦርቶዶክሳዊ እምነታቸው የሚታወቁት የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከዩክሬንና ሀይማኖትና ማንነትን ለማጥፋት ዙርያዉን ካሰፈሰፉ ጋር ግጭት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በክሪምሊን እና በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መካከል ያለውን የጠበቀ ትስስር ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል ።

1 day ago | [YT] | 50