ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቅድስት ድንግል እናቱ እና የቅዱሳኑ ወዳጅ ውድ አባቴ ባሕታዊ ቅዱስ አባታችን እውነተኛ መናኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ትምህርቷን ከጉባኤ ቤት ተምረው የተማሩትን በትክክል የኖሩ ከሥውራኑ እና ከግሑሳኑ ጋር አብረው የኖሩ እርሶም እንደእነርሱ የሆኑ ርህሩህ ከሰዉ ሸሽተው ተደብቀው የኖሩ እጅግ ጸሎተኛ ርኩሳን መናፍስት እርሶን ሲያዩ ደንግጠው እንደ አመድ እንደ ጉም የሚበተኑ። በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በውጪ አገር ያሉ በዋሻ የሚኖሩ ቅዱሳን ባሕታውያን የእርሶን ማንነት ቅድስና አውቀው ያላቸውን አስኬማ እና የጸሎት መቍጠሪያቸውን ልከው "አባታችን በጸሎት ያስቡን" የሚሎት። በጸሎቶ ብዙዎችን ከችግራቸው ያዳኑ የታመሙትን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የሚፈውሱ ታላቅ የትንቢት ጸጋ ያሎት። ለኔ ለኃጥያተኛ ልጅዎ ደግሞ ከወላጅ አባት በላይ ቅርብ ለሆኑት ችግሬን ይሁን ምንም ዓይነት ንግግሬን ሳይሰለቹ ለሚያዳምጡኝ መጥፎ ሆኜ ሳላ እንደ ተወዳጅ ልጅ አጠገቦ አስቀምጠው በፈገግታ ለሚያዩኝ 😢😢😢 ታላቁ አባቴ ባሕታዊ አባ ኃይለ ኢየሱስ በሥጋ ስለተለዩን እጅግ ልቤ ተሰብሯል የልጆቾ ልብ ተሰብሯል ነገር ግን በነፍስ በጌታችን መንበር ፊት ኢትዮጵያን እና መላውን ዓለም እኛን ልጆቾን እንደማይረሱን አምናለሁ።ይህ የተጻፈው ከልብ ስብራት የተነሳ ቃላት አንሶኝ ነው ከዚህ በላይ ምንም መጻፍ አልችልም ከቅዱስ አባታችን ጋር ያየሁ እጅግ ብዙ ነገሮች ራሱን የቻለ ጊዜ ተመድቦ እንደ ጌታችን ፍቃድ የምንጽፍላችሁ ሲሆን ነገር ግን በአንድ መንፈሳዊ ወዳጄ ጥያቄ እንዲሁም ግፊት ምክንያት ይህችን ጽሑፍ ለበረከት እንዲሆን ጽፌላችኋለሁ።ዋናው ነገር በኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ እምነት እንዲያጸናን እና እንደነዚህ ያሉ ቅዱሳን አባቶችን እና ቅዱሳት እናቶችን እንዲያሳየን አሳይቶንም በእምነታቸው መስለናቸው በእነርሱ መንገድ ሄደን ወደ መንግሰተ ሰማይ እንድንገባ ነው።የቅዱሱ አባት የባሕታዊ የአባ ኃይለ ኢየሱስ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።
1 day ago | [YT] | 1,261
ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቅድስት ድንግል እናቱ እና የቅዱሳኑ ወዳጅ ውድ አባቴ ባሕታዊ ቅዱስ አባታችን እውነተኛ መናኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ትምህርቷን ከጉባኤ ቤት ተምረው የተማሩትን በትክክል የኖሩ ከሥውራኑ እና ከግሑሳኑ ጋር አብረው የኖሩ እርሶም እንደእነርሱ የሆኑ ርህሩህ ከሰዉ ሸሽተው ተደብቀው የኖሩ እጅግ ጸሎተኛ ርኩሳን መናፍስት እርሶን ሲያዩ ደንግጠው እንደ አመድ እንደ ጉም የሚበተኑ።
በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በውጪ አገር ያሉ በዋሻ የሚኖሩ ቅዱሳን ባሕታውያን የእርሶን ማንነት ቅድስና አውቀው ያላቸውን አስኬማ እና የጸሎት መቍጠሪያቸውን ልከው "አባታችን በጸሎት ያስቡን" የሚሎት።
በጸሎቶ ብዙዎችን ከችግራቸው ያዳኑ የታመሙትን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የሚፈውሱ ታላቅ የትንቢት ጸጋ ያሎት።
ለኔ ለኃጥያተኛ ልጅዎ ደግሞ ከወላጅ አባት በላይ ቅርብ ለሆኑት ችግሬን ይሁን ምንም ዓይነት ንግግሬን ሳይሰለቹ ለሚያዳምጡኝ መጥፎ ሆኜ ሳላ እንደ ተወዳጅ ልጅ አጠገቦ አስቀምጠው በፈገግታ ለሚያዩኝ 😢😢😢
ታላቁ አባቴ ባሕታዊ አባ ኃይለ ኢየሱስ በሥጋ ስለተለዩን እጅግ ልቤ ተሰብሯል የልጆቾ ልብ ተሰብሯል ነገር ግን በነፍስ በጌታችን መንበር ፊት ኢትዮጵያን እና መላውን ዓለም እኛን ልጆቾን እንደማይረሱን አምናለሁ።
ይህ የተጻፈው ከልብ ስብራት የተነሳ ቃላት አንሶኝ ነው ከዚህ በላይ ምንም መጻፍ አልችልም ከቅዱስ አባታችን ጋር ያየሁ እጅግ ብዙ ነገሮች ራሱን የቻለ ጊዜ ተመድቦ እንደ ጌታችን ፍቃድ የምንጽፍላችሁ ሲሆን ነገር ግን በአንድ መንፈሳዊ ወዳጄ ጥያቄ እንዲሁም ግፊት ምክንያት ይህችን ጽሑፍ ለበረከት እንዲሆን ጽፌላችኋለሁ።
ዋናው ነገር በኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ እምነት እንዲያጸናን እና እንደነዚህ ያሉ ቅዱሳን አባቶችን እና ቅዱሳት እናቶችን እንዲያሳየን አሳይቶንም በእምነታቸው መስለናቸው በእነርሱ መንገድ ሄደን ወደ መንግሰተ ሰማይ እንድንገባ ነው።
የቅዱሱ አባት የባሕታዊ የአባ ኃይለ ኢየሱስ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።
1 day ago | [YT] | 1,261