ሄመን ዘተዋህዶ ቲዮብ

መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን የምሕረትና የመዳኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 12፥1 በማለት በነቢዩ ዳንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ ቦታ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 10፥13 በማለት ያስረዳል፡፡ በዚህ ቃል ላይ ከዋንኞቹ አለቆች አንዱ የሚለውን በመያዝ ሚካኤል ብቻ የመላእክት አለቃ አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን የሌሎች አለቅነት የተወሰነ ወይም ዝቅተኛ ሲሆን በአንድ ነገድ ላይ በአንድ የመላእክት ከተማ ላይ ነው፡፡የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት ግን በመላእክት ሁሉ ላይ ከሆነ ከሌሎቹ ይለያል፡፡ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ እንደተገለጸው ሰባት ሊቃነ መላእክት ቢኖሩም አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ቅዱስ ሚካኤል አርምሞ ትዕግሥትን የሚወድ መልአክ ነው፡፡የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር በተሰጠው ኃይል ዲያብሎስን ድል የነሣ መልአክ ነው፡፡በሰማይ ጦርነት ተነሣ ሚካኤልና እርሱ መላእክት ከዘንዶው ከመላእክቱም ጋር ተዋጉ ራእይ ዮሀንስ ምዕራፍ 12፥7 ይላል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሀገራችንን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን፣ እኛን ልጆችህንም አንተ በያለንበት ሁሉ ጠብቀን አማላጅነትህ ረድኤትህና በረከትህ አይለየን፡፡🌹💒🌹
በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፡፡ በዚች ቀን በዚህ ወር እግዚአብሔር ወደባቢሎን አገር ላከው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሦስቱን ልጆች አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ በጣላቸው ጊዜ አራተኛ ገጽ ሁኖ ታየ። የእሳቱም ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ወላይ ከፍ ከፍ አለ የጨመሩአቸውን ሰዎችና እሳት የሚያንዱትን አቃጠላቸው ይህም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የእሳቱን ነበልባል በበትሩ መትቶ ከሠለስቱ ደቂቅ ላይ አጥፍቶ አዳናቸው ምንም አልነካቸውም እንደ ቀዘቀዘ እንደ ጧት ጤዛ አድርጎታልና።በዚያንም ጊዜ የአባቶቻችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ይክበርይመስገን እያሉ ስድስት ቃላትን ተናገሩ በዚህም ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ ትንቢት ተናገሩ። ከዚህም በኋላ የጌታ እግዚአብሔር ሥራዎቹ ሁሉ ያመሰግኑታል እርሱ ለዘላለሙ ምስጉን ልዑልም ነው እያሉ ሠላሳ ሦስት ጊዜ አመሰገኑት በዚህም በምድር ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ክርስቶስ እንደሚኖር አመለከቱ ስለዚህም አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያን መምህራን የመላእክት አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ እንድናደርግ ሥዓትን ሠሩ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።🌹💒🌹

11 hours ago | [YT] | 217