EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) is a 24 hour working public media.
Ethiopian Broadcasting Corporation is a national media which disseminates its news and programs world wide via Television, Radio and Internet.


EBC

24 ሰዓት ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው የመገጭ መስኖ ፕሮጀክት
*******
መገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ያረፈበት ቦታ 870 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን፣ ግድቡ ሲጠናቀቅ 17 ሺህ ሔክታር መሬት በመስኖ የማልማት አቅም ይኖረዋል።
ከተጀመረ 15 ዓመታት ያስቆጠረው ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች እየተጓተተ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ አልቻለም።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ግንባታውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተጠቅሷል።
ፕሮጀክቱን በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ ግንባታው በፍጥነትና በጥራት እየተከናወነ መሆኑን፣ ግንባታውን ካለፈው ዓመት ጀምሮ እያከናወነ የሚገኘው ሀገር በቀሉ ኮንትራክተር ቤአኤካ አስታውቋል።
በተለይም ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚረዱ መሰረታዊ የግንባታ ምዕራፎችን በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉ ነው የተመላከተው።
አሁን ላይ የፕሮጀክቱ ግንባታ 77 በመቶ መድረሱም ተጠቅሷል። ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅም ለ24 ሰዓት የግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ለጎንደር እና በጎንደር ዙሪያ ለሚገኙ ከተሞች የንጹህ መጠጥ ውኃ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑም ተጠቅሷል።
በአባዲ ወይናይ
#ebcdotstream #EBC #irrigationdam

4 hours ago | [YT] | 447

EBC

የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቻይናን ከአውሮፓ ጋር በማገናኘት ዕውቅና አገኘ
*******
የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በቻይና እና አውሮፓ መካከል በሚደረገው የሎጂስቲክስ ግንኙነት ግንባታ ቁልፍ የሎጂስቲክስ አጋር በመባል ሽልማትን አገኘ።
አየር መንገዱ የቤልጂየም መንግሥት ከቻይና ሎጅስቲክስ ማኅበር ጋር በመሆን በቻይና ጓንዡ ባዘጋጀው ሥነ-ስርዓት ላይ ሽልማቱን ተቀብሏል።
አየር መንገዱ ዕውቅናውን ያገኘው፤ የተለያዩ ዕቃዎችን ከቻይና ወደ አውሮፓ በቤልጂየም በኩል በማጓጓዝ እንደ አገናኝ ድልድይ ሆኖ እየሰጠ ላለው ጠንካራ የካርጎ አገልግሎት ነው ተብሏል፡፡
በላሉ ኢታላ ነው
#ebcdotstream #EBC #ethiopianairlines

4 hours ago | [YT] | 50

EBC

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የነበረው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ችግር ተፈቷል፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
*************
የተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ሥራ መግባትን ተከትሎ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያ አድርጋለች።
ይህ ማሻሻያ ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት በብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ይደረግበት የነበረው የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን ማስቻሉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ተናግረዋል።
ከውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያው ዋነኛ ግቦች አንዱ የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ዋጋ እንዲኖራቸው ማድረግ መሆኑን ያነሱት የብሔራዊ ባንክ ገዥው፣ ይህም የወጭ ንግድ ገቢን በከፍተኛ መጠን ማሳደጉን ገልፀዋል።
ማሻሻያው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግና የሐዋላ ገንዘብ ግኝትን መጨመሩንም ነው የገለፁት።
ባለፉት 5 ወራት ብቻ እንኳን ኢትዮጵያ ካወጣችው የበለጠ የውጭ ምንዛሪ ማግኘቷን አስታውቀዋል።
አሁን ያለው የኢትዮጵያ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት በተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መጨረሻ ለማሳካት የታቀደውን ቀድሞ መድረስ የተቻለበት መሆኑንም ነው ያመላከቱት።
በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንደሌለም ተናግረዋል።
የውጭ ምንዛሪ ተደራሽነትን ለማሳደግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንኮች በጨረታ የሚገዙበትን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ ለደንበኞቻቸው እንዲያቀርቡ ማስቻሉንም ገልፀዋል።
በሐዋላ ከሚላክ የውጭ ምንዛሪ ጋር በተገናኘም ሕገወጥ ሐዋላ ገንዘብ ዝውውር ላይ የሚሳተፉትን ወደ ሕጋዊ መንገድ የሚመጡበት ሥራ እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
ከዚህ ተግባራቸው የማይታቀቡትን በሕግ አግባብ ተጠያቂ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ አጠቃላይ ሥርዓቱን እንዲስተካከል ይደረጋልም ብለዋል።
በቀጣይም የውጭ ምንዛሪ ግብይቱ የበለጠ ተገማችና ግልፅ አሰራር የሰፈነበት እንዲሆን የተጀመሩ የማሻሻያ ሥራዎችን ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።
በጌታቸው ባልቻ
#ebcdotstream #EBC #foreignexchange #Ethiopian #economy

4 hours ago | [YT] | 42

EBC

ግብርና ሚኒስቴር 258 መኪኖች እና 1 ሺህ 830 የሞተር ብስክሌቶችን ለክልሎች አበረከተ
***************
ግብርና ሚኒስቴር ለምግብ ሥርዓት ማጠናከርያ ፕሮግራም የሚሆኑ 258 መኪናዎችን እና 1 ሺህ 830 የሞተር ብስክሌቶችን ዛሬ ለክልሎች አስረክቧል።
‎ተሽከርካሪዎቹ በተለይም በገጠሩ አካባቢ ዝቅተኛ አቅም ያላቸው ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አርሶ እና አርብቶ አደሮች የምግብ ሥርዓት እንዲሻሻል የሚሰሩ ባለሙያዎችን እና የላቦራቶሪ ቁሶችን ለማጓጓዝ እንደሚውሉ በርክክቡ ወቅት ተገልጿል።
‎ሚኒስቴሩ ከዚህ በተጨማሪ የአየር ንብረትን ለሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ፕሮግራም 9 መኪኖች፣ 24 የሞተር ብስክሌቶች፣ የውኃ መሳቢያ ሞተር እንዲሁም 100 የመለዋወጫ ዕቃዎችን የያዙ ሳጥኖችን ለክልሎች አስረክቧል።
‎ይህም በኢትዮጵያ የተጀመረውን የበጋ መስኖ ልማትን ይበልጥ ለማስፋፋት እንደሚያግዙ ነው የተገለፀው።
‎የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፤ ለሁለቱም ፕሮግራሞች ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው ድጋፍ ለክልሎች ተደርጓል።
‌‎ተሽከርካሪዎቹ ኢትዮጵያ የያዘችውን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ለማሳካት አጋዥ መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ድጋፉ ከልማት አጋሮች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንደቀረበ ጠቁመዋል።‎
በባዬ ሙላት
#ebcdotstream #EBC #Ethiopia

8 hours ago | [YT] | 283

EBC

አዋሽ ወንዝ ከስጋት ምንጭነት ወደ ልማት መሳሪያነት የተቀየረበት ተንዳሆ የመስኖ ግድብ
*************
የአዋሽ ወንዝ በአፋር ምድር ከ1 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ይጓዛል።
በዚህ ጉዞው ወንዙ በተለይ ባለፉት ዓመታት በሚያስከትለው የጎርፍ አደጋ ለአካባቢው ስጋት ሆኖ ኖሯል።
ይህን መነሻ በማድረግ ከ15 ዓመታት በፊት የተጀመረው የተንዳሆ የመስኖ ልማት ግድብ ተስፋን ፈንጥቆ የነበረ ቢሆንም፤ በገጠሙት የግንባታ እክሎች ሳቢያ ውጤታማ ሳይሆን ቆይቷል።
የተጓተቱትን ማፋጠን፣ የተበላሹትን ማቃናት በሚል መርህ የሚሰራው የመደመር መንግሥት በግድቡ ላይ ያጋጠሙ እክሎችን በራስ አቅም በመጠገን የማሻሻያ ሥራው ከመጠናቀቁ በፊት ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንዲያለማ አስችሎታል።
በጥገና ሥራው፥ በውሃ መቆጣጠሪያ ግድቡ አካባቢ ያላለቁ ተግባራትን ማጠናቀቅ ቀዳሚው ተልዕኮ ሲሆን፤ ከዚህ ጎን ለጎን የግድቡን ውሃ ለመስኖ ልማት እና ለማህበረሰቡ ፍጆታ ማዋል ሌላው ዓላማ ነበር።
ይህን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ በተለይም የማሻሻያ ሥራው በኢትዮጵያውያን ኮንትራክተሮች መሠራቱ “የራስ አቅም ምን ድረስ ነው?” የሚለውን እንድንፈትሽ ያደረገ ነው ሲሉ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ፕሮጀክት ፕሮግራም ጽ/ቤት ኃላፊ አሸናፊ ሊካሳ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ማሻሻያው ወጣት አርሶ አደሮች እንዲፈጠሩ እና የቀደሙትም እንዲነቃቁ ያስቻለ ስለመሆኑ ነው የተናገሩት።
የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ሀብታሙ ብርሃን፥ በማሻሻያው ውሃ ፓምፕ በማድረግ ለጥቅም ይውል የነበረበትን መንገድ በመቀየር የፀሃይ ታዳሽ ኃይል ጥቅም ላይ እንዲውል እየተሠራ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ይህም ውሃ ፓምብ ለማድረግ ሲባል ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ነዳጅ ወጪን እንደሚቀንስ አስረድተዋል።
ስለ ፕሮጀክት ማሻሻያው አስተያየታቸውን ለኢቲቪ የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፥ ፕሮጀክቱ ከፈጠረላቸው የሥራ ዕድል በትግበራው ሂደት ያለፉበት የሥራ ባህል ትልቅ ትምህርት እንደሆናቸው ተናግረዋል።
ያለማቋረጥ 24/7 እየተከናወነ ያለው የማሻሻያ ሥራው ግድቡ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲገነባ የቅርብ ክትትል የሚደረግበት መሆኑን ኢቲቪ በቦታው ተገኝቶ ታዝቧልል።
በአፎሚያ ክበበው
#EBC #ebcdotstream #Afar #tendahodam

10 hours ago | [YT] | 131

EBC

#የመደመር_ጥቅስ


"...እንደ ዛሬው በብዙኃኑ ጉልበት የሚታረስ መሬትና ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ምርታማነት ያለው አይሆንም፡፡ በዘመኑ ቴከኖሎጂ እየታገዘ፣ በጥቂት የሰው ኃይል ከፍተኛ ምርት ያስገኛል። የገበሬውን ፍላጎት ከማሟላትና የሀገር ውስጥ ፍጆታን ከመሸፈን ያልፋል። በመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት ካፒታልን ለማሰባሰብ በምናደርገው ጥረት ውስጥ የውጭ ንግድ ወሳኝ ተዋናይም ይሆናል። ግብርናው ብቻም ሳይሆን የገጠር ሽግግሩም በተሠናሰለ መልኩ እየተመራ ይሄዳል፡፡ ሽግግሩ ለሰው ልጅ ምቹ ተደርገው የተገነቡ፣ መሠረተ ልማት የተሟላላቸው፣ ትናንሽ የገጠር ከተሞች እንዲፈጠሩ ያስችለናል፡፡
የተሻገረ ገጠርን መገንባት የተሻገረ ግብርናን የሚጠይቅ ነው። ስለዚህም ግብርናችንን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለውን ዐቅም ማላበስ አለብን፡፡ ይህ ደግሞ አሁን ካለበት እጅግ ኋላ ቀር ደረጃ ወደ ዘመናዊ የግብርና ደረጃ በፍጥነት ማሸጋገርን ይጠይቃል። ግብርናን በፍጥነት ማሸጋገር ዘርፉን በብዙ ወሳኝና አሻጋሪ ፈጠራዎች ማነቃቃት ነው። ግብርናችንን በሜካናይዜሽን የሚመራ፣ ግብአቶቹን ያለመቆራረጥ የሚያገኝ፣ ውጤታማነቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚያሣልጥ፣ የወደፊቱን ቴከኖሎጂ ባለቤት ለመሆን በምርምር የሚደገፍ ማድረግ ነው።
በአጠቃላይ ግብርናችን በከፍተኛ ትኩረት ዘመናዊነትን እንዲላበስ መሥራት የግድ ነው። የተሻገረ ግብርና ገጠሩን ለማሻገር መሠረት ነው ብለናል፡፡ ቢሆንም ግን የገጠሩን ሽግግርለማፋጠን ሊሟሉ የሚገባቸው ሌሎች መሥፈርቶችም አሉ። እነዚህን ከወዲሁ በቅንጅት መምራት፣ የገጠሩ ሽግግር ከግብርናው ሽግግር ጎን ለጎን መከናወን እንዲችል ዕድል ይሰጣል።
የግብርና ሽግግርም ሆነ አጠቃላይ የገጠር ሽግግር በመንግሥት ዐቅም ብቻ የሚሳካ አይደለም፡፡ የግል ዘርፉን ከፍተኛ ተሳትፎና የሌሎች የልማት አጋሮችን ቅንጅት ይጠይቃል፡፡ መንግሥት ቀዳሚ ኢንቨስተር ሆኖ መሥራት በሚገቡት ሁኔታዎች ሁሉ በከፍተኛ ፈጠራና ፍጥነት ታጅቦ ሚናውን ይወጣል። ለዚህም ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታዩት ግብርናውን የማሻገር የፈጠራና የፍጥነት መንገዶች ምስክር ናቸው። በቀጣይም ከልማት አጋሮች ጋር በተለየ ትኩረትና ቅንጅት ሽግግሩን ለማሳካት የሚታትር ይሆናል። የግል ዘርፉም አሁን ካለው የተሳታፊነት ደረጃ በላይ ግብርናውን የማሻገር ከፍ ሲልም ገጠሩን የማሻገር ትልምን ለማሳካት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል። ይሄንን በመገንዘብ በሙሉ ዐቅምና በተባበረ ክንድ የሽግግሩ አካል እንዲሆን ይጠበቃል፡፡
የተረጋጋና የጸና የገጠር ሽግግር ግንባታ የማይበገር ግብርናን (Resilient Agriculture) መገንባትን ይጠይቃል፡፡ ይህም ማለት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ተግዳሮቶችን የሚቋቋም ግብርና ማለት ነው።"


(#የመደመር_መንግሥት_ገጽ_166)

11 hours ago | [YT] | 553

EBC

ማንችስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ ከአርሰናል ያለውን ልዩነት ወደ ሁለት አጥብቧል
*************
በ16ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጭ ከፓላስ የተጫወተው ማንችስተር ሲቲ 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በሸልህረስት ፓርክ በተደረገው ጨዋታ ሃላንድ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ ፊል ፎደን ደግሞ ቀሪዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በውድድር ዓመቱ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ከአርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት አጥብቧል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች አስቶን ቪላ ከመመራት ተነስቶ ዌስትሀም ዩናየትድን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡
ቶተንሀም ሆትስፐር በኖቲንግሀም ፎረስት 3 ለ 0 ሲሸነፍ በተጠባቂው ደርቢ ሰንደርላንድ ኒውካስትል ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

22 hours ago | [YT] | 99

EBC

ኢትዮጵያ በቀዳሚነት ያጠናቀቀችበት የብስክሌት ስፖርት

22 hours ago | [YT] | 598

EBC

የወልድያ ከተማን መልክ እየቀየረ ያለው የኮሪደር ልማት
********************
በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማዋን መልክ በአጭር ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየረ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልፃሉ።
በከተማዋ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ የመንገድ ማሻሻያ፣ የእግረኞች መንገድ፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች እና የመብራት ስራዎችን ያካተተ ሲሆን፤ የከተማዋ ነዋሪዎች በልማቱ ምክንያት የትራፊክ አደጋ መቀነሱን፣ የከተማዋ ውበት መጨመሩን እና የንግድ እንቅስቃሴ መነቃቃቱን ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት ጠባብና የደቀቁ ሰፈሮቿ ዛሬ ዘመናዊ መልክ በመያዝ የከተማዋን ገጽታ ቀይረዋል ለዚህ ምስክሩ ደግሞ አዳጎ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ያነሳሉ።
በከተማዋ ከዚህ ቀደም አቧራ ያስቸግር እንደነበርና በጨለማም ሰዓታት ለመንቀሳቀስ አደጋች እንደነበር የሚያነሱት ነዋሪዎቹ፤ አሁን ላይ በከተማዋ መንገዶች ላይ የተሰራው ኮሪደርና በተዘረጋው የመብራት ምክንያት ደህንነነታቸው መረጋገጡን ገልፀዋል።
የኮሪደር ልማቱ የተዋቡ ህንፃዎች፣ የእግረኛ መንገዶች፣ የህፃናት መዝናኛዎች እንዲገነቡ በማስቻሉ በከተማዋ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠራቸውን ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ የንፅህና ባህሪን በመፍጠር ህይወታቸውን መሻሻሉን ገልጸው፤ ከዚህ በፊት መንገዶቻችን ጨለማ ነበሩ ዛሬ ግን በሀሴት እንቀሳቀሳለን ከተማችንም ፅዱ ሆናለች ብለዋል።
ልማቱ በአካባቢው የነበረውን የፀጥታ ችግር ተቋቋሞ መሰራቱ ለሰላም እና ለመረጋጋት ተግባራዊ ምላሽ መስጠቱን ያሳያል ይህም በከተማዋ ውስጥ ልማት እና ሰላም እጅ ለእጅ ተያይዘው መሄዳቸውን በእጀጉ አስፈላጊ መሆኑን ይመስክራል ነው ያሉት።
በወልድያ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ የከተማዋን የኑሮ ጥራት በማሻሻል ለዘላቂ ሰላምና ልማት መሠረት እየጣለ መሆኑም ተመላክቷል።
በሜሮን ንብረት
#EBC #EBCdotstream #Weldiya #corridordevelopment

22 hours ago | [YT] | 110

EBC

"የበደልነውን ህዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን" - የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች
*****************
የበደሉትን ህዝብ ለመካስ ዝግጁ መሆናቸውን በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች ተናገሩ፡፡
በምዕራብ ጎንደር ዞን የሰላም ጥሪ ከተቀበሉ ኃይሎች ጋር በገንዳ ውኃ ከተማ ዛሬ ውይይት ተደርጓል።
የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መንግስት ሁለንተናዊ ሠላምን ለማስፈን ከባለድረሻ ድርሻ አካላት ጋር ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚስችሉ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የታጠቁ አካላት የሰላም አማራጭን ተቀብሎ የመመለሱ ሂደቱ መጠናከሩን ገልፀጸው፤ ለሰላም ወደ ምህረት የመጡ አካላትን ዞኑ በተለያዩ የሥራ እድሎች በዘላቂነት ለማቋቋም እንደሚደግፍ አንስተዋል።
የሰላምን አማራጭ ያልመረጡ ሌሎች የታጠቁ ኃይሎችም ለሀገር እና ለህዝብ ሰላም ሲሉ የሰላም ጥሪውን እንዲቀበሉ ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።
በሰሜን ምዕራብ ዕዝ የ504ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ቾምቤ ወርቁ በበኩላቸው፤ አሁን ላይ እንደ ክልልም ሆነ እንደ አካባቢ ሰላምን ለማፅናት በርካታ ሥራዎች በመሰራታቸው ሰራዊቱ አበረታች ድል እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
ወደ ሰላም የመጡ አካላት ከህዝቡና ከፀጥታ አካላቱ ጎን በመሆን የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ለማምጣት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ህዝቡ ለሰላም የሚደረገውን ርብርብ በማጠናከር የታጠቁ ሀይሎች መንግስት ሁልጊዜም ለሰላም በሩ ክፍት መሆኑን ተረድተው ሌሎችም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ለሰላም እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሰላምን ተቀብለው በምህረት የገቡ አካላት፤ መንግሥት የሕዝቡን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እንደሚፈታ መገንዘባቸውን ገልፀው፤ ከመንግሥት እና ከሕዝብ ጎን በመሰለፍ ሌሎች ጫካ የሚኖሩ የታጠቁ ሃይሎች ወደ ሰላም ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡
በድርጊታቸው በመፀፀት ቀጣይ ከመንግስት ጎን በመሆን አብረው እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመልክቷል፡፡

22 hours ago | [YT] | 256