EBC
አዋሽ ወንዝ ከስጋት ምንጭነት ወደ ልማት መሳሪያነት የተቀየረበት ተንዳሆ የመስኖ ግድብ ************* የአዋሽ ወንዝ በአፋር ምድር ከ1 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ይጓዛል። በዚህ ጉዞው ወንዙ በተለይ ባለፉት ዓመታት በሚያስከትለው የጎርፍ አደጋ ለአካባቢው ስጋት ሆኖ ኖሯል። ይህን መነሻ በማድረግ ከ15 ዓመታት በፊት የተጀመረው የተንዳሆ የመስኖ ልማት ግድብ ተስፋን ፈንጥቆ የነበረ ቢሆንም፤ በገጠሙት የግንባታ እክሎች ሳቢያ ውጤታማ ሳይሆን ቆይቷል። የተጓተቱትን ማፋጠን፣ የተበላሹትን ማቃናት በሚል መርህ የሚሰራው የመደመር መንግሥት በግድቡ ላይ ያጋጠሙ እክሎችን በራስ አቅም በመጠገን የማሻሻያ ሥራው ከመጠናቀቁ በፊት ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንዲያለማ አስችሎታል። በጥገና ሥራው፥ በውሃ መቆጣጠሪያ ግድቡ አካባቢ ያላለቁ ተግባራትን ማጠናቀቅ ቀዳሚው ተልዕኮ ሲሆን፤ ከዚህ ጎን ለጎን የግድቡን ውሃ ለመስኖ ልማት እና ለማህበረሰቡ ፍጆታ ማዋል ሌላው ዓላማ ነበር። ይህን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ በተለይም የማሻሻያ ሥራው በኢትዮጵያውያን ኮንትራክተሮች መሠራቱ “የራስ አቅም ምን ድረስ ነው?” የሚለውን እንድንፈትሽ ያደረገ ነው ሲሉ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ፕሮጀክት ፕሮግራም ጽ/ቤት ኃላፊ አሸናፊ ሊካሳ ገልጸዋል። በተጨማሪም ማሻሻያው ወጣት አርሶ አደሮች እንዲፈጠሩ እና የቀደሙትም እንዲነቃቁ ያስቻለ ስለመሆኑ ነው የተናገሩት። የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ሀብታሙ ብርሃን፥ በማሻሻያው ውሃ ፓምፕ በማድረግ ለጥቅም ይውል የነበረበትን መንገድ በመቀየር የፀሃይ ታዳሽ ኃይል ጥቅም ላይ እንዲውል እየተሠራ ስለመሆኑ ተናግረዋል። ይህም ውሃ ፓምብ ለማድረግ ሲባል ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ነዳጅ ወጪን እንደሚቀንስ አስረድተዋል። ስለ ፕሮጀክት ማሻሻያው አስተያየታቸውን ለኢቲቪ የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፥ ፕሮጀክቱ ከፈጠረላቸው የሥራ ዕድል በትግበራው ሂደት ያለፉበት የሥራ ባህል ትልቅ ትምህርት እንደሆናቸው ተናግረዋል። ያለማቋረጥ 24/7 እየተከናወነ ያለው የማሻሻያ ሥራው ግድቡ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲገነባ የቅርብ ክትትል የሚደረግበት መሆኑን ኢቲቪ በቦታው ተገኝቶ ታዝቧልል። በአፎሚያ ክበበው #EBC #ebcdotstream #Afar #tendahodam
19 hours ago | [YT] | 186
EBC
አዋሽ ወንዝ ከስጋት ምንጭነት ወደ ልማት መሳሪያነት የተቀየረበት ተንዳሆ የመስኖ ግድብ
*************
የአዋሽ ወንዝ በአፋር ምድር ከ1 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ይጓዛል።
በዚህ ጉዞው ወንዙ በተለይ ባለፉት ዓመታት በሚያስከትለው የጎርፍ አደጋ ለአካባቢው ስጋት ሆኖ ኖሯል።
ይህን መነሻ በማድረግ ከ15 ዓመታት በፊት የተጀመረው የተንዳሆ የመስኖ ልማት ግድብ ተስፋን ፈንጥቆ የነበረ ቢሆንም፤ በገጠሙት የግንባታ እክሎች ሳቢያ ውጤታማ ሳይሆን ቆይቷል።
የተጓተቱትን ማፋጠን፣ የተበላሹትን ማቃናት በሚል መርህ የሚሰራው የመደመር መንግሥት በግድቡ ላይ ያጋጠሙ እክሎችን በራስ አቅም በመጠገን የማሻሻያ ሥራው ከመጠናቀቁ በፊት ከ60 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንዲያለማ አስችሎታል።
በጥገና ሥራው፥ በውሃ መቆጣጠሪያ ግድቡ አካባቢ ያላለቁ ተግባራትን ማጠናቀቅ ቀዳሚው ተልዕኮ ሲሆን፤ ከዚህ ጎን ለጎን የግድቡን ውሃ ለመስኖ ልማት እና ለማህበረሰቡ ፍጆታ ማዋል ሌላው ዓላማ ነበር።
ይህን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ በተለይም የማሻሻያ ሥራው በኢትዮጵያውያን ኮንትራክተሮች መሠራቱ “የራስ አቅም ምን ድረስ ነው?” የሚለውን እንድንፈትሽ ያደረገ ነው ሲሉ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ፕሮጀክት ፕሮግራም ጽ/ቤት ኃላፊ አሸናፊ ሊካሳ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ማሻሻያው ወጣት አርሶ አደሮች እንዲፈጠሩ እና የቀደሙትም እንዲነቃቁ ያስቻለ ስለመሆኑ ነው የተናገሩት።
የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ሀብታሙ ብርሃን፥ በማሻሻያው ውሃ ፓምፕ በማድረግ ለጥቅም ይውል የነበረበትን መንገድ በመቀየር የፀሃይ ታዳሽ ኃይል ጥቅም ላይ እንዲውል እየተሠራ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ይህም ውሃ ፓምብ ለማድረግ ሲባል ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ነዳጅ ወጪን እንደሚቀንስ አስረድተዋል።
ስለ ፕሮጀክት ማሻሻያው አስተያየታቸውን ለኢቲቪ የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፥ ፕሮጀክቱ ከፈጠረላቸው የሥራ ዕድል በትግበራው ሂደት ያለፉበት የሥራ ባህል ትልቅ ትምህርት እንደሆናቸው ተናግረዋል።
ያለማቋረጥ 24/7 እየተከናወነ ያለው የማሻሻያ ሥራው ግድቡ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲገነባ የቅርብ ክትትል የሚደረግበት መሆኑን ኢቲቪ በቦታው ተገኝቶ ታዝቧልል።
በአፎሚያ ክበበው
#EBC #ebcdotstream #Afar #tendahodam
19 hours ago | [YT] | 186