EBC

"የበደልነውን ህዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን" - የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች
*****************
የበደሉትን ህዝብ ለመካስ ዝግጁ መሆናቸውን በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች ተናገሩ፡፡
በምዕራብ ጎንደር ዞን የሰላም ጥሪ ከተቀበሉ ኃይሎች ጋር በገንዳ ውኃ ከተማ ዛሬ ውይይት ተደርጓል።
የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መንግስት ሁለንተናዊ ሠላምን ለማስፈን ከባለድረሻ ድርሻ አካላት ጋር ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚስችሉ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የታጠቁ አካላት የሰላም አማራጭን ተቀብሎ የመመለሱ ሂደቱ መጠናከሩን ገልፀጸው፤ ለሰላም ወደ ምህረት የመጡ አካላትን ዞኑ በተለያዩ የሥራ እድሎች በዘላቂነት ለማቋቋም እንደሚደግፍ አንስተዋል።
የሰላምን አማራጭ ያልመረጡ ሌሎች የታጠቁ ኃይሎችም ለሀገር እና ለህዝብ ሰላም ሲሉ የሰላም ጥሪውን እንዲቀበሉ ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።
በሰሜን ምዕራብ ዕዝ የ504ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ቾምቤ ወርቁ በበኩላቸው፤ አሁን ላይ እንደ ክልልም ሆነ እንደ አካባቢ ሰላምን ለማፅናት በርካታ ሥራዎች በመሰራታቸው ሰራዊቱ አበረታች ድል እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
ወደ ሰላም የመጡ አካላት ከህዝቡና ከፀጥታ አካላቱ ጎን በመሆን የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ለማምጣት የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ህዝቡ ለሰላም የሚደረገውን ርብርብ በማጠናከር የታጠቁ ሀይሎች መንግስት ሁልጊዜም ለሰላም በሩ ክፍት መሆኑን ተረድተው ሌሎችም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት ለሰላም እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሰላምን ተቀብለው በምህረት የገቡ አካላት፤ መንግሥት የሕዝቡን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እንደሚፈታ መገንዘባቸውን ገልፀው፤ ከመንግሥት እና ከሕዝብ ጎን በመሰለፍ ሌሎች ጫካ የሚኖሩ የታጠቁ ሃይሎች ወደ ሰላም ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡
በድርጊታቸው በመፀፀት ቀጣይ ከመንግስት ጎን በመሆን አብረው እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመልክቷል፡፡

1 day ago | [YT] | 296