ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

ይህ 'ቻናል' የእግዚአብሄርን ቃል በማስተላለፍ፡ ተስፋ ለመስጠት፥ እምነትን ለማጠናከር እና መንፈሳዊ መነቃቃትን ለመፍጠር ያለመ ነው።

This channel aims to inspire, give hope, strengthen faith by spreading God's Word.


ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

01 ___ የአምላክ እናት ልደት ( #ልደታ_ለማርያም )
https://youtu.be/UBAY7p4iBCA 👈👈👈
ይኽቺ እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ እንደ ጨረቃ የተዋበች፤ እንደ ፀሓይም የጠራች ዐላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሰራዊት የምታስፈራ ማን ናት?
___ ጠቢቡ ሰሎሞን
___ ሙሸራዬ ሆይ ከሊባኖስ ነዪ ከሊባኖስ ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም
ጠቢቡ ሰሎሞን በለሶች (ኢያቄምና ሐና) ቡቃያ አንቺን ባስገኙሸ ጊዜ ምድር ደስ አላት ሰማይም ደስ አለው፤
ጓደኛ (ምሳሌ) የሌለሽ የድኅነት ምልክት ማርያም፤
መልአከ ሞት እስከ ፈራና ሰይጣንም እስከ ደነገጠ ድረስ
የመወለድሽ ዜና እስከ ሲኦል ድረስ (በሲኦል) ተሰማ)
___ አባ ጽጌ ድንግል አባ ገብረ ማርያም

1 day ago (edited) | [YT] | 1,116

ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

30 _ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ #ዮሐንስ 👇
https://youtu.be/56rwfottIww

ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፣ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን፥ ድንግል፥ ሰማዕት፣ ነብይና አገልጋይ፣ ምስጉን፥ ቅዱስና ንፁህ፣ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ።

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኖ ቅዱሳን ላይ።

2 days ago | [YT] | 882

ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

27 _____ ‎“ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ‎ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢያትን ‎ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት በሚፈርደው ‎በርሱ ፈረዱበት ______ ፡፡
_____ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://youtu.be/jldRr2qDsBw👈👈👈
‎በሐዋርያት ሥራና በመልእክታት ላይ ቅዱስና ‎ጻድቅ፣ የሕያዋንና የሙታን ፈራጅ፣ ጌታ፣ መድኀኒት፣ ‎የእግዚአብሔር ኀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ፣ በግዐ ‎ፋሲካ፣ ኋለኛው አዳም፣ የቤተ ክርስቲያን ራስ፣ ሕያው ‎አምላክ፣ በኲር፣ ታላቅ ሊቀ ካህናት፣ የእምነታችን ‎ራስና ፈጻሚ፣ የነፍስ እረኛና ጠባቂ፣ የእረኞች አለቃ፣ ‎የሕይወት ቃል፣ የአብ ልጅ፣ የእግዚአብሔር አንድ ልጅ ‎የተባልኽ መድኃኔ ዓለም ሆይ እወድኻለኹ::

5 days ago | [YT] | 1,246

ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

26_ የአባታችን የ #አቡነ_ሀብተ_ማርያም በረከታቸው
ይደርብን አሜን።
https://youtu.be/3ERM53hopLY👈👈👈
_ በተከበረች በኅዳር 26 ቀን ንዑድ ክቡር ንጹሕ መነኰስ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም
የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

በዓለም የተበተኑ በጎች የተባሉ ልጆችህ የሚጠበቅበት የእምነት ዘንግን ለጨበጠ መሀል እጅህ ሰላምታ ይገባል። ጻድቁ አባታችን ሀብተ ማርያም ሆይ የዚች ዓለም ጸጥታዋና ሰላሟ አንተ ነህ እኮ እኛ ለመዉደቅ የተፍገመገምነዉን እንደ ብረት ዘንግ የሆነ ጸሎትህ ከወደቅንበት መሬት ያንሳን ይደግፈን ሁለተኛም የጎሰቆለች ነፍሳችን ቃልኪዳንህ አይለያት።

_ መልክአ አቡነ ሀብተ ማርያም

6 days ago (edited) | [YT] | 358

ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

ኅዳር 25 የ#ቅዱስመርቆሬዎስ ሰማዕትነት
በተወለደ በ25 ዓመቱ በኅዳር 25 ቀን ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት በክርስቶስ ስም የሰማዕትነትን የክብር የሕይወት አክሊል ተቀዳጀ፤ የሰማዕታት ዘመን ካለፈም በኋላ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታንጸዋል።
ግሩም ሮማዊ በመንፈስ ቅዱስ የታተምክ፤ እንደ ምድረበዳ አበባ የምስጋናህ መዐዛ የጣፈጠ መርቆሬዎስ በበዓልህ ዛሬ ትባርከን ዘንድ ና ና በመካከላችንም ቁም።
_ሊቁ አርከ ሥሉስ

_የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት
መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል።
_ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ

1 week ago | [YT] | 1,050

ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

24 #ተክለ_ሐይማኖት
ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው
ጣዖትን አዋርዶ የተሸለመዉ
https://youtu.be/67rVJ9UmTBA👈👈👈
የተዋሕዶ ኮከብ ተክለ ሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት ዘኢትዮጵያ

1 week ago | [YT] | 1,371

ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

23 #ቅዱስ_ጊዮርጊስ
ሰማይ ነው ሀገሩ ፥ ልዳ መቃብሩ
ጊዮርጊስ ሰማእት ፥ ፍጡነ ረድኤት
https://youtu.be/ATrLv5qQenc👈👈👈
... የደካሞች ረዳት ... የምስኪኖች አባት
ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለ
ታላቅና ክቡር የሆነ ሰማእት
+++ በረከቱ ይደርብን!

1 week ago | [YT] | 990

ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

💚💛❤️ዑራኤል ሆይ ከመልኮች ሁሉ ይልቅ የአንተን መልክአ ጸሎት እወዳለሁ።
https://youtu.be/L56yGujhOsk👈👈👈
የመልክህ ሥነ ጸዳል በደመ ወልደ እግዚአብሔር የታተመ ነውና።
ዑራኤል ሆይ እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጽበት መልአከ ብርሃናት አንተ ነህ።
በዕለተ ስቅለት በደመ ወልድ ዓለምን ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ አንተ ተሰይመሃልና።
ስለክብርህ የሰማይ መላእክት አደነቁ።
💚💛❤️መልክአ ዑራኤል

1 week ago (edited) | [YT] | 628

ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

#ጽዮን ማርያም
እንኳን አደረሳችሁ ! አደረሰን !
https://youtu.be/J3_SRCwfd9k👈👈👈
"እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።” (መዝ. ፻፴፩ ፥ ፲፫ - ፲፬) እንዲል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በመዝሙሩ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማናዊት የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችውን የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዓመታዊ በዓል ኅዳር ፳፩ ቀን በድምቀት ታከብራለች።

“ጽዮን” ማለት“ አምባ፣ መጠጊያ” ማለት ነው።
“ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፤ በውስጥዋም ሰው ተወለደ” (መዝ. ፹፮፥፭) በማለት መዝሙረኛው ዳዊት እንደተናገረ አዳምና ልጆቹ በበደል ምክንያት ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ከተፈረደባቸው የሲኦል እሥራት ነጻ ይወጡ ዘንድ እግዚአብሔር ወልድ ከዳዊት ዘር በተገኘችው ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ፡፡
ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ማኅፀኗን ዙፋን አድርጎ ተወለደ። እኛም ኦርቶዶክሳውያን የእግዚአብሔር ማደሪያ፣ አምባ መጠጊያ የሆነችውን ድንግል ማርያምን የድኅነታችን መሠረት ናትና እናከብራታለን፣ እናመሰግናታለን፣ ከፍ ከፍም እናደርጋታለን፣ በዓሏንም እናከብራለን።

_ታቦተ ጽዮን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ትመሰላለች። ኅዳር ፳፩ ቀን የእመቤታችን የቅድስት
ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በተለየ መልኩ
የምናከብርበት ምክንያት በርካታ ቢሆኑም በዋነኛነት
ታቦተ ጽዮን በፍልስጤማውያን ተማርካ በነበረበት ወቅት
ዳጎን የተባለውን ጣኦት የሰባበረችበትና ልዩ ልዩ ተአምራት
የፈጸመችበትን መሠረት አድርገን ነው።

1 week ago (edited) | [YT] | 184

ቅዱስ ሐሳብ | Kidus Hasab

ለጣኦት ሳንሰግድ እኛ ሳንረታ
የምናምነው አምላክ ሊያድነን ወደደ
ገብርኤል መጣና እሳቱ በረደ
https://youtu.be/-rmRz8YK620👈👈👈
ፍላጻና ሰይፉን አጠፋው መልአኩ
ሰላም ይዞ መጣ በዓለም ሊታወኩ
አትጠራጠሩ ምልጃው ያስምረናል
የሚነደው እሳት ሳይነካን ወጥተናል
https://youtu.be/vF2-ioYZ-Ww👈👈👈

1 week ago (edited) | [YT] | 1,496