እንኳን ወደ Daily Mezmur ቻናል በደህና መጡ! 🙏
በዚህ ቻናል የእለቱ አማርኛ መዝሙሮችን በቀጥታ እና በፍጥነት እናቀርባለን። ቪዲዮዎቻችን ሁሉ የእምነት እና የመንፈሳዊ ግንኙነት እንዲያጠናክሩ ተዘጋጅተዋል።
✨ **ምን ማግኘት ይችላሉ?**
- አጫጭር ዕለታዊ መዝሙሮች
- የአማርኛ መዝሙር ቪዲዮዎች
- ስብከት እና መንፈሳዊ ትምህርት ያገኛሉ
🔔 እባኮትን ቻናልን ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ “Subscribe” በተን ይጫኑ ።
📌 ተከታይ ለመሆን: [Subscribe ቁልፍ ይጫኑ]
#DailyMezmur #መዝሙር #AmharicMezmur #PraiseSongs
የዕለቱ መዝሙር
በአንድነት አስሮ በፍቅር ባርኮ
ይስብስብልህ ምርኮ በምርኮ
ብዛ ተባዛ የአባቴ መንጋ
የሚነሳብህ ወገብ ይወጋ
አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
የጽድቅን ኑሮ የቅድስናን
እያበዛልህ ጸሎት ጽሞናን
የካህኑን ረሃብ የአምልኮን ጥማት
ያትረፍርፍልህ ቅባት በቅባት
አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
ሽማግሌዎች ከአደባባይ
ህጽናት ልጆች ከሜዳው ላይ
የአዝመራው መዓዛ የአምልኮ መድረክ
ሁሉም ይለምልም ሁሉም ይባረክ
አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
የግብጽ ቁስል ደዌ ቸነፈር
ጭንገፋና ሞት አንተን አይድፈር
ቀሳፊው መልአክ ቤትህ አይግባ
ጉበን መቃንህ በደሙ ይቀባ
አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
ተምች አይውረር ደግሞም ኩብኩባ
የአየር ንብረትህ እንዳይዛባ
ወንዝ አፈርህ ጌታ ይባርክልህ
ቁርባን መስዋዕትህን ያለምልምልህ
አዝ:- እግዚአብሔር ይባርክህ ይጠብቅህ
ፊቱን ደግሞ ያብራልህ ይራራልህ
እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ
ሰላሙን ደግሞ ይስጥህ ይጨምርልህ
ፓስተር ታምራት ሀይሌ
5 days ago | [YT] | 1
View 0 replies
የዕለቱ መዝሙር
👉አይበለውና በህይወት ዘመንሽ ሙሉ አንድ መዝሙር ብቻ ነው መስማት የሚፈቀድልሽ የሚል ቅጣት ቢጣልብኝ ሁለቴ እንኳ ሳላስብ የመርጠው አንድ መዝሙር አለ የምህረት ኢተፋ (ክበር ንገስ🥹🤎 )
#ወደ ልጅነቴ የሚመልሰኝ ያንን ወርቃማውን ዘመን የሚያስናፍቀኝ ቆየት ያለ የምህረት ዝማሬ ነው ትዝ ይለኛል በጣም ልጅ ነበርኩ ያን ግዜ የጴንጤ መዝሙር ጫት ቤት ሳይቀር ይከፈት ነበር
አሁን ትልቅ ሰው ሆኜ ሆድ ሲብሰኝ .....አንድ አንድ "አገልጋዮች " አገልግሎትን ንግድ ሲያረጉት ሳይ ልቤ እንዳይወርድብኝ ስሰጋ ሄጄ የድሮ መዝሙሮች ውስጥ እደበቃለሁ 🥹
እኔም ልቤ ሲያብጥ ጥጋብ ጥጋብ ሲለኝ ውስጤ ድርቅ ሲል "ክበር ንገስ" የሚለውን መዝሙር ለራሴ ጋብዤ ገና ኢንትሮውን ስሰማ እንባዬ በጉንጮቼ አልፎ አንገቴን ያጥበኛል ...እታከማለው ..እፈወሳለሁ እንደገና በፍቅር እሞላለሁ እንደገና ሰማይን ናፍቃለሁ እንደገና አለም እና ኮተተቶቿን እንቃለሁ "ክበር ንገስ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ 🥹)
ከተወዳጇ ዘማሪት ምህረት ኢተፋ መዝሙሮች የምትወዱትን እስኪ ጋብዙኝ 🤎
1 month ago | [YT] | 10
View 1 reply
የዕለቱ መዝሙር
"ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" 1ኛ ቆሮ. 3÷11
#መሠረተ_ክርስቶስ_ቤተ_ክርስቲያን
#ራእይ
👉 በመንፈስ ቅዱስ ኀይል የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች የእግዚአብሔርን መንግሥት የምታስፋፋ ሚስዮናዊት ቤተ ክርስቲያን መኾን ነው፡፡
#ተልእኮ
👉 ለሰዎች ሁሉ ወንጌል በማድረስ ያመኑትን በማስተማር የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንዲኾኑ ማድረግ ነው፡፡
#ዐላማዎች
📌 ወንጌልን ማሰራጨት
📌 ያመኑትን ደቀ መዛሙርት ማድረግ
📌 አገልጋዮችን ማፍራትና ማብቃት
📌 ሰላምን መገንባት
📌 ኹለንተናዊ አገልግሎት መስጠት
#እሴቶች
📢 ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ሕይወትና አገልግሎት
📢 ርስ በርስ መዋደድ
📢 ሎሌነት
📢 ኹለንተናዊ ሰላም
📢 ባለዐደራነት
📢 ተሳታፊነትና አሳታፊነት
መረጃዎቻችንን ከዚህ በታች በተቀመጡት አማራጮች ይከታተሉ 👇
በቴሌግራም: https://t.me/MKC_Official
በዩቱብ: youtube.com/@mkcmedia2023
በፌስቡክ: https://www.facebook.com/mkcpresidentoffice
1 month ago | [YT] | 5
View 1 reply
የዕለቱ መዝሙር
1 month ago | [YT] | 4
View 0 replies
የዕለቱ መዝሙር
#ነብይ ጥሌ እና ቤተሰቡ 👨👩👦
3 months ago | [YT] | 7
View 0 replies
የዕለቱ መዝሙር
#ዳዊት ይኖርበት በነበረ በዚያ ዘመን ብዙ "ትልቅ" የሚባሉ ነገሮች ነብሩ:: ከእነዚህም መካከል አንዱ #ጎልያድ ነበር:: ነገር ግን ዳዊት በዘመኑ የነበሩ "#ትልልቅ" ነገሮች አይተልቁበትም ነበር:: ለዳዊት ትልቅ እግዚአብሔር ብቻ ነው:: ለዚህም ነው እስራኤላውያን እና ፍልስቴማውያን "ትልቅ" ላሉት ጎልያድ ጠጠር ይዞ የሄደው::
እግዚአብሔርን ብቻ ታላቅ ስናደርግ ሁሉም ትንሽ ይሆንብናል🙏
5 months ago | [YT] | 1
View 0 replies
የዕለቱ መዝሙር
#ኢየሱስ የጊዜ አለቃ
አንዲት መበለት ተስፋዋ የሆነው ልጇ በመሞቱ በሃዘን እየተንገበገበች ነው፡፡ ዓይን የጣሉበት፣ ተስፋ ያረጉት ሲሞት መኖር ራሱ ትርጉም ያጣል። አንዳንድ ሃይማኖት ነገር እስካለ ነው የሚሠራው – የሚጠቅመውም። አንዳንድ ምርጥ ባሕሎች ሕይወት ያለው ነገር እስካላችሁ ነው የሚያግዙት። ባልጀራም ቢሆን ነገር ሲያልቅ መደብዘዝ ይጀምራል።
በናይን ከተማ ትኖር የነበረችዋ መበለት ተስፋዋ ሲሞት የሚቀጥልላት፣ ልጇን በሞት ስታጣው ወደ ሕይወት የሚመልሳላት ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ዘመድና አዝማድ የለም። ተስፋዋ ሞተ - አበቃ።
የቀብር ሰዎች ትላንት ሕያው የነበረንና ዛሬ ሬሳ የሆነባቸውን ሊቀብሩ ሲወጡ፣ ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ወደ ከተማው ሲገቡ ተገጣጠሙ። ባለሬሳዎቹ ያበቃውን ሊቀብሩ፣ የሕይወት ራስ ደግሞ ከደቀ መዛሙርቱ ወደ ከተማ ሲገቡ በሩ ላይ ተገጣጠሙ። ያ'በቃው ነገር ቀን መጣበት። የተቆረጠ ተስፋ ሊቀጠል ሰዐት ደረሠ።
'ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና - 'አይዞሽ፤ አታልቅሺ' አላት። ቀረብ ብሎም ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙትም ሰዎች ቀጥ ብለው ቆሙ፤ ኢየሱስም፣ 'አንተ ጎበዝ፤ ተነሥ እልሃለሁ' አለው፡፡ ሉቃ.
7:13-14
እንግዲህ በቃ በተባለው ላይ ጌታ መጣና ቀጠለ። ስብራትን ይጠግናል፤ የተቀደደን ልብ ይሰፋል ጌታዬ፤ የወደቀን ያነሣል ኢየሱስ፤ የሞተን ያስነሣል አዳኜ።
በቃ በቃ በተባለው ላይ አበቃ በቃ በተባለው ላይ ....
5 months ago | [YT] | 2
View 0 replies
የዕለቱ መዝሙር
🛳 .መርከብ ላይ ተረጋግተህ ትጓዛለህ
ካፒቴኑን ግን አታውቀውም.....
✈ . አውሮፕላን ላይ ተረጋግተህ ትበራለህ
አብራሪውን ግን አታውቀውም......
🚖 . ታክሲ ላይ ተረጋግተህ ትሳፈራለህ
ሹፌሩን ግን አታውቀውም.....
🎯 . በሕይወትህ ጉዞ ውስጥም በፍጹም አትናወጥ ይልቁንም ታምነህና ተረጋግተህ ተቀመጥ
መንገድ ያስጀመረህ ሳታውቀው ያወቀህ ፣
ሳትወደው የወደደህ አምላክህ እርሱ ነውና።
“በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።”
መዝሙር 37፥3 See less
5 months ago | [YT] | 2
View 0 replies
የዕለቱ መዝሙር
“በምትሄድበት ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋራ ነውና አይዞህ፤ በርታ፤ ጽና፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?””
ኢያሱ 1:9
“Have not I commanded you? Be strong, vigorous, and very courageous. Be not afraid, neither be dismayed, for the Lord your God is with you wherever you go.”
Joshua 1:9
5 months ago | [YT] | 9
View 0 replies
የዕለቱ መዝሙር
በረከት ተስፋዬ
🎼ከሚጠፉት እንዳሎን
በዓለም ፍቅር እንዳልነደፍ
ከሚጠፉት ጋር እንዳልሰለፍ
አረማመዴን አቅናውና
የራስህ አድርገኝ ቀይረኝና
ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)
አንተ የሌለህበት
የዓለም ዝና የዓለም ዕውቀት
ኢሄ ሁሉ ከንቱ ነዉ
ንፋስን እንደመከተል ነው
ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)
በአንደበቴ እንዳልረክስ
ወንድሜንም እንዳልተነኩስ
አቤቱ ማስተዋልን ስጠኝ
መንፈስ ቅዱስ ና አስተምረኝ
ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)
ዓይኔን ወደ አንተ እንዳቀና
መንፈስ ቅዱስ ናልኝና
ፈውሰኝ ቀድሰኝ
መጠቀሚያ ገንዘብህ አድርገኝ
ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)
🎼ከሚጠፉት እንዳሎን
6 months ago | [YT] | 3
View 0 replies
Load more