የዕለቱ መዝሙር

በረከት ተስፋዬ

🎼ከሚጠፉት እንዳሎን

በዓለም ፍቅር እንዳልነደፍ
ከሚጠፉት ጋር እንዳልሰለፍ
አረማመዴን አቅናውና
የራስህ አድርገኝ ቀይረኝና

ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

አንተ የሌለህበት
የዓለም ዝና የዓለም ዕውቀት
ኢሄ ሁሉ ከንቱ ነዉ
ንፋስን እንደመከተል ነው

ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

በአንደበቴ እንዳልረክስ
ወንድሜንም እንዳልተነኩስ
አቤቱ ማስተዋልን ስጠኝ
መንፈስ ቅዱስ ና አስተምረኝ

ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

ዓይኔን ወደ አንተ እንዳቀና
መንፈስ ቅዱስ ናልኝና
ፈውሰኝ ቀድሰኝ
መጠቀሚያ ገንዘብህ አድርገኝ

ከሚጠፉት እንዳልሆን ጠብቀኝ
ጌታ ሆይ ምህረትህን አብዛልኝ (፪x)

🎼ከሚጠፉት እንዳሎን

6 months ago | [YT] | 3