የዕለቱ መዝሙር
#ኢየሱስ የጊዜ አለቃ አንዲት መበለት ተስፋዋ የሆነው ልጇ በመሞቱ በሃዘን እየተንገበገበች ነው፡፡ ዓይን የጣሉበት፣ ተስፋ ያረጉት ሲሞት መኖር ራሱ ትርጉም ያጣል። አንዳንድ ሃይማኖት ነገር እስካለ ነው የሚሠራው – የሚጠቅመውም። አንዳንድ ምርጥ ባሕሎች ሕይወት ያለው ነገር እስካላችሁ ነው የሚያግዙት። ባልጀራም ቢሆን ነገር ሲያልቅ መደብዘዝ ይጀምራል። በናይን ከተማ ትኖር የነበረችዋ መበለት ተስፋዋ ሲሞት የሚቀጥልላት፣ ልጇን በሞት ስታጣው ወደ ሕይወት የሚመልሳላት ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ዘመድና አዝማድ የለም። ተስፋዋ ሞተ - አበቃ። የቀብር ሰዎች ትላንት ሕያው የነበረንና ዛሬ ሬሳ የሆነባቸውን ሊቀብሩ ሲወጡ፣ ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ወደ ከተማው ሲገቡ ተገጣጠሙ። ባለሬሳዎቹ ያበቃውን ሊቀብሩ፣ የሕይወት ራስ ደግሞ ከደቀ መዛሙርቱ ወደ ከተማ ሲገቡ በሩ ላይ ተገጣጠሙ። ያ'በቃው ነገር ቀን መጣበት። የተቆረጠ ተስፋ ሊቀጠል ሰዐት ደረሠ። 'ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና - 'አይዞሽ፤ አታልቅሺ' አላት። ቀረብ ብሎም ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙትም ሰዎች ቀጥ ብለው ቆሙ፤ ኢየሱስም፣ 'አንተ ጎበዝ፤ ተነሥ እልሃለሁ' አለው፡፡ ሉቃ. 7:13-14 እንግዲህ በቃ በተባለው ላይ ጌታ መጣና ቀጠለ። ስብራትን ይጠግናል፤ የተቀደደን ልብ ይሰፋል ጌታዬ፤ የወደቀን ያነሣል ኢየሱስ፤ የሞተን ያስነሣል አዳኜ። በቃ በቃ በተባለው ላይ አበቃ በቃ በተባለው ላይ ....
5 months ago | [YT] | 2
የዕለቱ መዝሙር
#ኢየሱስ የጊዜ አለቃ
አንዲት መበለት ተስፋዋ የሆነው ልጇ በመሞቱ በሃዘን እየተንገበገበች ነው፡፡ ዓይን የጣሉበት፣ ተስፋ ያረጉት ሲሞት መኖር ራሱ ትርጉም ያጣል። አንዳንድ ሃይማኖት ነገር እስካለ ነው የሚሠራው – የሚጠቅመውም። አንዳንድ ምርጥ ባሕሎች ሕይወት ያለው ነገር እስካላችሁ ነው የሚያግዙት። ባልጀራም ቢሆን ነገር ሲያልቅ መደብዘዝ ይጀምራል።
በናይን ከተማ ትኖር የነበረችዋ መበለት ተስፋዋ ሲሞት የሚቀጥልላት፣ ልጇን በሞት ስታጣው ወደ ሕይወት የሚመልሳላት ሃይማኖት፣ ባሕል፣ ዘመድና አዝማድ የለም። ተስፋዋ ሞተ - አበቃ።
የቀብር ሰዎች ትላንት ሕያው የነበረንና ዛሬ ሬሳ የሆነባቸውን ሊቀብሩ ሲወጡ፣ ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ወደ ከተማው ሲገቡ ተገጣጠሙ። ባለሬሳዎቹ ያበቃውን ሊቀብሩ፣ የሕይወት ራስ ደግሞ ከደቀ መዛሙርቱ ወደ ከተማ ሲገቡ በሩ ላይ ተገጣጠሙ። ያ'በቃው ነገር ቀን መጣበት። የተቆረጠ ተስፋ ሊቀጠል ሰዐት ደረሠ።
'ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና - 'አይዞሽ፤ አታልቅሺ' አላት። ቀረብ ብሎም ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙትም ሰዎች ቀጥ ብለው ቆሙ፤ ኢየሱስም፣ 'አንተ ጎበዝ፤ ተነሥ እልሃለሁ' አለው፡፡ ሉቃ.
7:13-14
እንግዲህ በቃ በተባለው ላይ ጌታ መጣና ቀጠለ። ስብራትን ይጠግናል፤ የተቀደደን ልብ ይሰፋል ጌታዬ፤ የወደቀን ያነሣል ኢየሱስ፤ የሞተን ያስነሣል አዳኜ።
በቃ በቃ በተባለው ላይ አበቃ በቃ በተባለው ላይ ....
5 months ago | [YT] | 2