Simegn Sisay Tube


አንተ ሐሳብህን ልትመራዉ እንጂ፤ ሐሳብህ አንተን ሊመራ ቦታ አትስጠዉ፥ እዉነተኛ ክርስቲያን ስሜቱ የሚመራዉ ሳይሆን ስሜቱን የሚወመራ ነዉ።


ወንድሜ አንተ በመከራ ውስጥ ካለህ የዩናስን ዓሣ ነባሪ አስታውስ። ከፍራቻ ትገላገላለህ። መከራው እግዚአብሔር ጸጋውን ሊያበዛልህ ስለፈለገ ያዘጋጀው ዓሣ ነባሪ እንደሆነ የምታውቅበት ጊዜ ይመጣል። የዚህ ዓለም የባሕር ዓሣዎች ብዙ ስለሆኑ ስትዋጥ እንዳይከፋህ መጠንቀቅ ይኖርብሃል። የመጀመሪያው ባህታዊ ጻድቁ አባ ጳውሊ የተናገረውን መዘንጋት የለብህም "ከመከራ መራቅ የሚወድ ከእግዚአብሔር ይርቃል" ብሏል። በእውነት መከራ የጸሎት ትምህርት ቤት ነው። "በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ጮኽሁ እርሱም ሰማኝ። በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ። ቃሌንም አደመጠ" ዮናስ 2፥3




Simegn Sisay Tube

"እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ። ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።"
(ሉቃ ፪፥፲-፲፩)

2 years ago | [YT] | 0

Simegn Sisay Tube

እንኳን ለፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለሀይማኖት አመታዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችው አደረሰን አሜን (3)

2 years ago | [YT] | 0

Simegn Sisay Tube

እንደምን አደራችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን በዕለቱ ታስበውና ተከብረው ለሚውሉ አመታዊ እና ወርሀዊ የቅዱሳን በዓል እንዲሁም ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን መልካም ቀን ይሁንልን 🕊🕊🕊🕊🕊🥀💐🥀

2 years ago | [YT] | 0

Simegn Sisay Tube

"ገብርኤል ሆይ! ከጭንቅና ከመከራ ለማውጣት የተላክህ መልአክ ነህና ሠለስቱ ደቂቅ በእሳት ጉድጓድ በተጣሉ ጊዜ ሁለቱ ክንፎችህን ጋርደህ ከመቃጠል እንዳዳንሃቸው እኔንም አገልጋይህን በረድኤትህ ኃይል አድነኝ።"
(መልክአ ገብርኤል)

2 years ago | [YT] | 1

Simegn Sisay Tube

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
*****************

በፊልም ሥራዎቹ ብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና ዝናን ያተረፈው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ወጣቱ የፊልም ባለሙያ ባደረበት ሕመም ለሳምንታት በሕክምና ሲረዳ ቢቆይም ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነው አርቲስት ታሪኩ በሕመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ኢፕድ ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ማረጋገጡን ዘግቧል።

አርቲስቱ ወጣት በ97፣ ወንድሜ ያዕቆብ፣ ላውንድሪ ቦይ፣ ማርትሬዛ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣ አንድ ሁለት፣ ብር ርርር፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ እንደ ቀልድ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

3 years ago | [YT] | 0

Simegn Sisay Tube

እንኳን እንደ እ

3 years ago | [YT] | 1

Simegn Sisay Tube

❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

❤ ኅዳር ፲፪ (12) ቀን።

❤ እንኳን ለሰው ወገን ለሚያዝንና ለሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረት ሁሉ ለሚማልድ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ከግብፅ ባርነት ሲወጡ ከሊቀ ነቢያት ሙሴ ጋር በሆነ ሕዝብ በመንዳቸው ሁሉ እየመራ የኤርትራ ባሕር ለከፈለበት፣ ለነዌ ልጅ ለነቢዩ ለቅዱስ ኢያሱ፡ለተገለጠለት፣ ዱራታዎስና ሚስቱን ቴዎብስታ ለረዳበት ዓመታዊ በዓልና ለኢትዮያዊው ንጉሥ ለጻድቁ በእደ ማርያም ለዕረፍቱ መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በደብረ ማህው ከታየችበት፣ ከእስክድርያ ስልሳ ሦስተኛ ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ አባት ከአባ ፊላታዎስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።



+ + +
❤ "ሰላም ለሚካኤል መልአከ ኃይል" ትርጉም፦ የኃይል መልአክ ለኾነ ለቅዱስ ሚካኤል ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።

+ + +
❤ በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

❤ ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው "ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?" አለው። "እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ" አለው። ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና "በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል?" አለው። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን "የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ። እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው "በውስጧ ያለውን ንጉሷን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ"።

❤ ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጽናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው። ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባልክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና።

+ + +
❤ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፦ እንዲህም ሆነ እግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢ ያደርጉ ነበር ከዚህም በኋላ በአገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ ለዚህም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉት አጡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሔደ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኰንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት ወደ ባለ በጎች ሒዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሒዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ ግን መልአኩ ወደ ቤቱ ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ ወደ ባለ ሥንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ። ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው። እጅግም አደነቀ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደ አደረገ። የተራቡ ድኆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደየቤታቸው አሰናበታቸው።

❤ ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ሁለተኛ ተገለጠላቸው። ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሠነጥቅ አዘዘው። በሠነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ተገኘ። ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው "ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሣውና ለባለ ሥንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ። በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል" አላቸው።

❤ እነርሱም ሲሰሙ ስለዚህ ነገር ደነገጡ እርሱም "ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም" አላቸው። ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ። እነርሱም ሰገዱለት ተአምራቱም የማይቈጠር ብዙ ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል ጸሎትና አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

+ + +
❤ አባ ፊላታዎስ፦ በእስክንድርያ ከተሾሙ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ ሦስተኛ ነው። በሹመቱ ወራት የኢትዮጵያ ንጉሥ ወደ ኖባ ንጉሥ ወደ ጊዮርጊስ እንዲህ ብሎ የመልክት ደብዳቤ ጻፈ "ወንድሜ ሆይ ከሊቀ ጳጳሳት ቆዝሞስ ጊዜ ጀምሮ ለረጅም ጊዜ ጳጳስ ስለ ሌለን እኛ በታላቅ ችግር ውስጥ እንዳለን ዕወቅ። ይህም የሆነው ተንኰለኛው ሚናስ በተንኰልና በሐሰት ነገር የከበረ ጳጳሳችንን ጴጥሮስን ከሹመቱ ወንበር እንዲሰደድ ስለ አደረገው ነው። ስለዚህ አምስት ጳጳሳት እስቲአልፉ ለአገራችን ጳጳስ አልተላከም። አሁንም ስለ እግዚአብሔር ብለህ ስለ ቀናች ሃይማኖትም በድካም ከእኛ ጋር አንድ በመሆን ስለእኛ ወደ ግብጽ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቅዱስ ፊላታዎስ ጳጳስ ይልክልን ዘንድ ከራስህ ደብዳቤ እንድትጽፍለት እለምንሃለሁ" የሚል ነበር።

❤ በዚያንም ጊዜ የኖባ ንጉሥ ጊዮርጊስ ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስን ይሾምላቸው ዘንድ የልመና ደብዳቤ ወደ አባ ፊላታዎስ ጻፈ ይህ ቅዱስ ፊላታዎስም ልመናውን ተቀብሎ ከአስቄጥስ ገዳም ስሙ ዳንኤል የሚባል አንድ ጻድቅ መነኰስ አስመጣ እርሱን ጵጵስና ሹሞ ወደ ኢትዮጵያ አገር ላከው ወደ እነርሱም በደረሰ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰዎች በታላቅ ደስታ ተቀበሉት። በዚህም አባት ፊላታዎስ ዘመን ብዙ ተአምራት ተገልጠዋል ኅዳር 12 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ፊላታዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 12 ስንክሳር።



+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ። ወብዙኀ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ። ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ"። መዝ 20፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ19፥11-28።

+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ዘነፈቃ ለባሕረ ኤርትራ ወከፈላ። እስመ ለዓለም ምሕረቱ። ወአውፆኦሙ ለእስራኤል እንተ ማዕከላ"። መዝ 135፥14-15 ወይም መዝ 33፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 9፥17-24 ይሁ 1፥9-14 እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥15-21 ። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል በዓል ለሁላችንም ይሁን

3 years ago | [YT] | 1

Simegn Sisay Tube

እንኳን ማርያም ማረችሽ መስኪዬ🕊🕊💦🥰

3 years ago | [YT] | 1

Simegn Sisay Tube

https://youtu.be/EyyjuQgnzTY እልልልልልልልል👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼👏🏼 ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን አሜን አሜን አሜን

3 years ago | [YT] | 1