ብሶቴን በግጥም

ክፋትን ከሚያስፋፉ በበለጠ በጎነትን በሚዲያችን እናውጅ ቅንነትን እንያዝ


ብሶቴን በግጥም

ጥሬ ቆርጥመው ያደሩት ገዳማውያኑ
ፈለግህን ተከትለው የመነኑት ሰማዕት ሆኑ
ተሰው ልጆችህ ታረዱ ካህኑ
ጸሎተኛው ቅዱስ አቡዬ ጻድቁ
ልጆችህ ጸንተው በጽድቅህ በቁ

5 months ago | [YT] | 3

ብሶቴን በግጥም

እንደ አበባ ነው።
ክብሬ

6 months ago | [YT] | 2

ብሶቴን በግጥም

ርእሰ ሊቃዉንት ድርሰትህ የተራቀቀ
የሱራፌል አምሳያ አእምሮህ የመጠቀ
ልዑለ ስብከት የቤተክርስቲያን ጌጧ
ዜማን የወጠንክላት ከብሯ ነህ ዉበቷ

7 months ago | [YT] | 4

ብሶቴን በግጥም

ስም-አልባ ጥያቄ ተሳተፉበት

ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ እስኪዝል ድረስም ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ሞትን ፈለገና። ከሕይወት ሞት ይሻለኛል አለ። እግዚአብሔርም ን። በወኑ ስለዚች ቅል ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለው። እርሱም። እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል አለ።


ሀ. ሙሴ

ለ. ዮናስ

ሐ. ኤልያስ

መ. ዳዊት
ሠ. ሁሉም መልስ ናቸው።

10 months ago | [YT] | 2

ብሶቴን በግጥም

ቀዝቃዛ በሆነ ምሽት አንድ ሃብታም ሰውየ ከቤቱ ውጭ አንድ ድሃ ሽማግሌ አገኘ። ‹በዚ ቅዝቃዜ ውጪ ላይ ኮት እንኳን አለበስክም አይበርድህም እንዴ› ብሎ ጠየቀው። አዛውንቱም "ኮት የለኝም ነገር ግን ለምጄዋለሁ ሲል መለሰለት። ባለ ሃብቱም "ቆይ ጠብቀኝ ወደ ቤቴ ሄጄ ኮት አመጣልሀለው" ብሎት ሄደ።

ድሃው ሰውም በጣም ተደስቶ እጠብቅሀለው አለው። ባለ ሃብቱም ወደ ቤቱ ደረሰ ግን በስራ ተጠምዶ ስለ ምስኪኑ ሰው ረሳ። በማግስቱ ጠዋት ድነገት ምስኪኑን አዛውንት አስታወሰና ሊፈልገው ወጣ ነገር ግን ምስኪኑን አዛውንት በቅዝቃዜው ሞቶ አገኘው።

ምስኪኑ አዛውንትም እንዲህ የሚል ደብዳቤ አስቀምጦለት ነበር "ሞቅ ያለ ልብስ ሳላገኝ ቅዝቃዜውን ለመቋቋም የሚያስችል የአእምሮ ጥንካሬ ነበረኝ, ነገር ግን እንደምትረዳኝ ቃል ስትገባ, ቃልህ የአእምሮ ኃይሌን ገደለው"

ቃል መፈጸም ካልቻልን ምንም ቃል አንግባ። ለእርስዎ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል, ነገር ግን ለሌላ ሰው ሁሉም ነገር ሊሆን ይችላል...🤔

10 months ago | [YT] | 3

ብሶቴን በግጥም

ክፋት ሆይ እባክህ ቀስ በል አትቸኩል
የትም አያደርስም የክፋት ቀንድ ማብቀል
በሰፊው ተንጠራራህ እጅህ ተዘረጋ
ለምን ፈለክ ከአምላክህ ልትዋጋ❓
በጣም ቸኮልክ አበዛህ ጥድፊያ
በኋላ አይጠቅምህም አማክር በለሙያ
ያመጣብሀልና ስብራት ከቤት መዋያ
ሮጠህ አታመልጥም ከቁጣው እሳት ፊት
ስለጥፋትህ እዘን ተጸጸት በቁጭት
አይጠቅምህም መሆን ለጥፋት ታታሪ
አገልጋይ ሁን እንጂ በቅጥሩ አዳሪ
እልህ አትጋባ አትግጠም ውጊያ ከፈጣሪ
ትግልህ ይሁን እንደ ያዕቆብ ትግል
መባረክ አለእና በጨለማው መሀከል
አውልቀህ ጣለው የተንኮልን ዝናር
አድመኝነትና ቁጣን ትተህ እንደቃሉ እደር

10 months ago | [YT] | 3

ብሶቴን በግጥም

የቅኔውን መቀነት ደርቦ አስታጥቆ
በክብር ሸልሞ በሞገስ ጠብቆ
በፍቅሩ ከቦ በምህረት ጎዳና
እንኳን አደረሳችሁ በሰላም በጤና

10 months ago | [YT] | 3

ብሶቴን በግጥም

የሚያስጨንቀኝን ለአምላኬ ጥዬ
ልቤ ይረፍ በወንጌል ከለላዬ
ነፍሴ ትታመን በቃለ ወንጌሉ
ሥጋይ ይብቃህ ለኃጢአት መማለሉ

1 year ago | [YT] | 3

ብሶቴን በግጥም

አንተ ሃይሌ ነህ
እኔ ምርኮኛህ
ስበድል በንስሐ ልብስ ትሽፍነኛልህ

1 year ago | [YT] | 4