ብሶቴን በግጥም
ክፋት ሆይ እባክህ ቀስ በል አትቸኩል የትም አያደርስም የክፋት ቀንድ ማብቀልበሰፊው ተንጠራራህ እጅህ ተዘረጋለምን ፈለክ ከአምላክህ ልትዋጋ❓በጣም ቸኮልክ አበዛህ ጥድፊያበኋላ አይጠቅምህም አማክር በለሙያያመጣብሀልና ስብራት ከቤት መዋያሮጠህ አታመልጥም ከቁጣው እሳት ፊትስለጥፋትህ እዘን ተጸጸት በቁጭትአይጠቅምህም መሆን ለጥፋት ታታሪአገልጋይ ሁን እንጂ በቅጥሩ አዳሪእልህ አትጋባ አትግጠም ውጊያ ከፈጣሪትግልህ ይሁን እንደ ያዕቆብ ትግልመባረክ አለእና በጨለማው መሀከል አውልቀህ ጣለው የተንኮልን ዝናርአድመኝነትና ቁጣን ትተህ እንደቃሉ እደር
10 months ago | [YT] | 3
ብሶቴን በግጥም
ክፋት ሆይ እባክህ ቀስ በል አትቸኩል
የትም አያደርስም የክፋት ቀንድ ማብቀል
በሰፊው ተንጠራራህ እጅህ ተዘረጋ
ለምን ፈለክ ከአምላክህ ልትዋጋ❓
በጣም ቸኮልክ አበዛህ ጥድፊያ
በኋላ አይጠቅምህም አማክር በለሙያ
ያመጣብሀልና ስብራት ከቤት መዋያ
ሮጠህ አታመልጥም ከቁጣው እሳት ፊት
ስለጥፋትህ እዘን ተጸጸት በቁጭት
አይጠቅምህም መሆን ለጥፋት ታታሪ
አገልጋይ ሁን እንጂ በቅጥሩ አዳሪ
እልህ አትጋባ አትግጠም ውጊያ ከፈጣሪ
ትግልህ ይሁን እንደ ያዕቆብ ትግል
መባረክ አለእና በጨለማው መሀከል
አውልቀህ ጣለው የተንኮልን ዝናር
አድመኝነትና ቁጣን ትተህ እንደቃሉ እደር
10 months ago | [YT] | 3