Bagaa Nagan dhuftaan Obbolleewaan kenyaa garan chanel kenyatii. Inis like share subscribers gochuu hin dagatinaa. Chanel kanara Barnotaa Amantaa Orthodox fi Faaruuwwan Garagaraa qabatee kan sini dhiyatuudhaa. Orthodox Tewahidoon Baraa baraan ni jiratii. Waqayoo jirtaa baraa baraatii❤
ቅድስት ቲዩብ
ነሐሴ 27/2017 #የአለም_መድኃኒት_መድኃኔዓለም
በሞቱ ሞታችንን ለሻረልን #ለመድኃኔዓለም
ምስጋናና ክብር ይሁንልን
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር #ኢየሱስ_ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው ምን ዓይነት ፍቅር ነው ስለኛ የሰዉ ልጆች ሲል በመስቀል ላይ ዋለ
👉ራቁትን መሰቀል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ #ራቁቱን_ተሰቀለ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተናቀ ተተፋበት
👉እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር #ክርስቶስ እኛን ልጆቹን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር
👉አይሁድ በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት ጌታችን ሲሰቀል በመሰቀሉ የተገኙት እናታችን #ማርያምና ሐዋርያው አባታችን #ቅዱስ_ዮሐንስ ነበሩ አኛም #በመስቀሉ ስር ለመገኘት ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ ወንበዴ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባከዉ በኃጢአት የወደቅን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚታሠቡት አባታችን አቡነ #መብአ_ፅዮን በፀሎታቸዉ ከኛ ጋር ይሁኑ "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👉ነሐሴ 27/2017 ዓ/ም
3 months ago | [YT] | 37
View 2 replies
ቅድስት ቲዩብ
ነሐሴ 21/2017 #እናታችን_ቅድስት_ማርያም
በወርቅ ልብስ ተጎናፅፋና ተሸፋፍና ንግስቲቱ
#በቀኝህ_ትቆማለች መዝ.44፥9
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በእናታችን ስም ለምናመሰግንበት #ለወላዲተ_አምላክ_ማርያም ወርሐዊ ለእረፍት መታሠቢያ በዐል እንኳን አደረሰን የእናታችን ማርያም ትንሣኤና እርገት በረከት ለሁላችንም ይድረሰን አሜን
👉እናታችን #ማርያም ከመሬት ወደ ሰማይ ላረገዉ ስጋሽ ሠላምታ ይገባል የምድር ስፋት በሠሌዳ መልክ ቢዘጋጅ እያደር አዲስና እንግዳ የሚሆን ምስጋናሽን ፍጡር ፅፎት ሊጨርሰዉ አይችልምና ምስጋና ይገባሻል
👉በሁሉ እንደበት መመስገን የተገባሽ ስለሆነ በሰማይ ካሉ #መላእክት በምድር ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም ሁል ጊዜ ምስጋና ይቀርብልሻልና ሠላምታ ይገባሻል
👉 #እግዚአብሔር በብሩህ ደመና ተጭኖ መጥቶ በማኅፀንሽ ያደረ እመቤታችን ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ
👉በቅዱሳን ነቢያት በቅዱሳን መላእክት አድሮ የሚኖር ካንች ተወልዶ የተገለፀልን #እመቤታችን_ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ።
👉ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ የምንሰግድለት ቃል የሚባል እግዚአብሔር ባንች ባሕርይ ካንች ይወለድ ዘንድ የወደደሽ #እመቤታችን_ማርያም ደስ ይበልሽ
👉ከወለድሽው በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ እንዳይለወጥ አድርጎ የጠበቀሽን #አማኑኤልን የወለድሽው እመቤታችን ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ
👉ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ #ንጉሥ_ክርስቶስን የወለድሽ #እመቤታችን_ማርያም ሆይ ሰላምታ ይገባሻል
👉ልዩ መድኃኒታችንን በመውለድሽ እናትና አገልጋይ ተብለሻልና #እግዚአብሔር ባሕርይሽን ባሕርይ አድርጎ ባለሟልነትን አግኝተሻልና #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ ሰላምታ ይገባሻል
👉እኛ ከምንወደው እሱም ከሚወደን #ልጅሽ ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ ለምኝልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👉ነሐሴ 21/2017 ዓ/ም
3 months ago | [YT] | 57
View 0 replies
ቅድስት ቲዩብ
🌹 27 🌹መድኃኔዓለም እንኳን አደረሳችሁ ።
🌿 ከሰው ወገን ማንም እንደኔ ኃጢአት የሰራ የለም ።
እንዳንተም ያለ መሓሪ ይቅር ባይ አምላክ አይኖርም ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ ዓለማትን ሁሉ የፈጠርክ ፈጣሪ እንደመሆንህ መጠን በኋለኛው ዘመን በዓለም ላይ ለመፍረድ
በመጥመጣበት ጊዜ ከጎንህ በፈሰሰው ደሞ ኃጢአቴን
እጠብልኝ ።
4 months ago | [YT] | 49
View 4 replies
ቅድስት ቲዩብ
❤️☦️🥰
4 months ago | [YT] | 4
View 0 replies
ቅድስት ቲዩብ
❤☦️🕊️
4 months ago | [YT] | 5
View 1 reply
ቅድስት ቲዩብ
አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል?!
👉"እናትህ እነኋት" ዮሐ. 19፣27
4 months ago | [YT] | 47
View 2 replies
ቅድስት ቲዩብ
#ቅዱስገብርኤል #ሊቀመላእክት #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ #Orthodox #ገብርኤል
“ #እኔ_በእግዚአብሔር_ፊት_የምቆመው_ገብርኤል ነኝ “ (ሉቃ 1:19)
#ቅዱስ_ገብርኤል_ማን_ነው ???
ሐሙሌ 19/11/017 ዓ.ም
👉 #ገብርኤል:- ማለት የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና ከሊቀ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ ስልጣን የተሰጠው ታላቅ መልአክ ነው።
👉 #ለእመቤታችን ለቅስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም የዓለም ድኅነትን የሚሆን ልጅ እንደ ምትወልድ በታላቅ ምስጋና ያበሠረ! የነቢያትንም ትንቢት የፈጸመ ድንቅ መልአክ ነው።
👉 #ለካህኑ ዘጋርያስ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስን መወለድን ያበሰረ አብሳሪ መልአክ ነው።
👉 #ሐምሌ 19 ቀን ህጻኑን ቅዱስ ቂርቆስን እና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳነበት ታላቅ ቀን ነው።
👉 #ታህሳስ 19 ቀን ሃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሠልስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነበት ታላቅ ቀን ነው።
👉 #ዳንኤልን ከአናብስት አፍ ያዳነም ሃያል መልአክ ነው ሰብአ ሠገልን በኮከብ ምልክት የመራ መልአክም ነው በጨለማ በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃንን የገለጸ ሃያል መልአክ ነውና ክብር እና ምስጋና ይገባዋል።
የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት፣ ፍቅር፣ ምልጃ አይለየን ሀገራችንን ሠላም ያድርግልን።
እንኳን በሰላም በጤና ለሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን 💕🙏💕
4 months ago | [YT] | 44
View 1 reply
ቅድስት ቲዩብ
ኪዳነ ምህረት እመቤቴ እመቤቴ💖
ነይልን ነይልን ካልንበት(2) ዛሬ አኮ 1️⃣6️⃣
እናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ናት ወርኃዊ መታሰቢያ ከክፉ ሁሉ ትጠብቀን💖🙏💖💒💒💒
4 months ago | [YT] | 42
View 0 replies
ቅድስት ቲዩብ
#አይኑ ዘርግብ
ልብሱ ዘመብረቅ
#ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ ➊➋💚💛❤️✝️
5 months ago | [YT] | 31
View 1 reply
ቅድስት ቲዩብ
ወር በገባ በ8 የጻድቁ አባታችን ‹‹አቡነ ኪሮስ›› የመታሰቢያ በዓል ነው።
አባ ኪሮስ አባቱ ንጉስ ዮናስ እናቱ አንስራ ይባላሉ፡፡
አባ ኪሮስ በታህሣሥ ፰ ቀን በሀገረ ሮም እግዚአብሔርን ከሚያከብሩ ወላጆች ተወለዱ።
አባ ኪሮስ ከልጅነታቸው ጀምረው የቤተክርስቲያን ትምህርትን እየተማሩ በክርስቲያናዊ ምግባር አደጉ
በእግዚአብሔር ፈቃድም ወደ ገዳም በመሄድ ገዳማዊ ሕይወትን መኖር በበዓታቸው በጾም በጸሎት መትጋትን ጀመሩ።
ለቅድስና የተመረጡ በመንፈስ ቅዱስ የተባረኩ ነበሩና በምንኩስና ሕይወታቸው የበረቱ ሆኑ።
እግዚአብሔር አምላክ "ለብዙዎች አባት ትሆናለህ፤ በቃልህ ክርዳድ ይነቀላል" አላቸው።
አባ ኪሮስ በምንኩስና ሕይወት እየተጉ ለብዙዎች መነኮሳት አባት ሆነው በቅድስና ኖሩ።
የጻድቁ አባታችን አባ ኪሮስ በረከትና ምልጃ ይደርብን🙏
👉ባሎ ቢላና ሰኔ 07/10/2017!
5 months ago | [YT] | 52
View 0 replies
Load more