ቅድስት ቲዩብ

ነሐሴ 27/2017 #የአለም_መድኃኒት_መድኃኔዓለም

በሞቱ ሞታችንን ለሻረልን #ለመድኃኔዓለም
ምስጋናና ክብር ይሁንልን

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር #ኢየሱስ_ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው ምን ዓይነት ፍቅር ነው ስለኛ የሰዉ ልጆች ሲል በመስቀል ላይ ዋለ

👉ራቁትን መሰቀል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ #ራቁቱን_ተሰቀለ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተናቀ ተተፋበት

👉እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር #ክርስቶስ እኛን ልጆቹን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር

👉አይሁድ በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት ጌታችን ሲሰቀል በመሰቀሉ የተገኙት እናታችን #ማርያምና ሐዋርያው አባታችን #ቅዱስ_ዮሐንስ ነበሩ አኛም #በመስቀሉ ስር ለመገኘት ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ ወንበዴ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባከዉ በኃጢአት የወደቅን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚታሠቡት አባታችን አቡነ #መብአ_ፅዮን በፀሎታቸዉ ከኛ ጋር ይሁኑ "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ነሐሴ 27/2017 ዓ/ም

3 months ago | [YT] | 37