በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
❗️#በመጀመሪያ ❗️
🚶♂️🚶♂️
☞አዳም ማለት በአራማይክ አፈር ማለት ሲኾን በግእዝ እንደ ረዓይት ሳይረዝም እንደ ድንክ ሳያጥር ይህ ቀረህ የማይባል እንደ ብርጨቆ የጠራ እንደ ፀሓይ የሚያበራ እንደ ጽጌያት ያሸበረቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ መልከ መልካም ማለት ነው፡፡
☞እግዚአብሔር አዳምን ከመሬት አፈር ፈጥሮ በፊቱ የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ባለአእምሮ ሰው ኾነ፡፡
☞ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን አቅንቶ የፈጠረው ስለምን ነው ቢሉ ሌላው ፍጥረት(እንስሳት አዕዋፋት ሙተው ፈርሰው በስብሰው ይቀራሉ፡፡ እሱ ግን ትንሣኤ አለው ሲል ነው፡፡
☞በማይታወቅ ምሥጢር በእግዚአብሔር አምሳል ለተፈጠረና የፍጥረት 'መጀመሪያ''' ለሆነ አዳም አባታችን ሰላምታ ይገባል፡፡
ለእናተ ''መጀመሪያ'' እንድንሆን ይህንን ቻናል ሰብስክራይብ አድርጉልን ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። Please Subscribers #Subscribe🙏🙏🙏🙏🙏
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
ታህሳስ 12/2018 #መልአኩ_ቅዱስ_ሚካኤል
በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት #በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር ለምስጋናና ለፀሎት ለሚቆመዉ ለመልአኩ #ለቅዱስ_ሚካኤል ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
መልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል የአርምሞና የትሕትና መልአክ ነው ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈፅሙ ድረስ የሚያፀናቸውና የሚያስታግሣቸው እርሱ ነው ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ ወር በገባ በ12 ቀን ለመታሰቢያው በዓል እናደርጋለን
እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲያወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲሆንልን ወደ #እግዚአብሔር በፀሎት ይማልድልናልና
መልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል በክንፈ ረድኤቱ ጋርዶ ችግራችንን አስወግዶ ከፈጣሪው እንደሚያስታርቀን ሊቁ #ቅዱስ_ያሬድ በዜማው ሲያመሰጥር #ሚካኤል የኃይል መልአክ ነውና እርሱ ታላቅ ነው ሥልጣኑም ታላቅ ነው በችግራችን ጊዜ ይለምንልን ዘንድ ረዳትም ይሆነን ዘንድ ክንፎቹንም ዘርግቶ በላይ ይጋርዳል በማለት ዘምሯል
#ቅዱስ_ሚካኤል የነፍስም የሥጋም መጋቢ በመሆኑ በቃል ኪዳኑ ታምነው አማላጅነቱን ደጅ ጸንተው ስሙን የጠሩ ሁሉ በነፍስም በሥጋም የሚጠቀሙ ሆነዋል
እስራኤል ዘሥጋን ከግብፅ የባርነት ኑሮ #በእግዚአብሔር ቸርነት ነፃ አውጥቶ መና አውርዶ ደመና ጋርዶ አለት ሰንጥቆ ውኃ አፍልቆ ጠላት ገድሎ ባሕር ከፍሎ እየመራ ምድረ ርስት ያስገባቸው #ቅዱስ_ሚካኤል ነው
በዚህም መጋቤ ብሉይ የሚል ቅፅል ተሰጥቶታል ቅዱስ #ያሬድ ስለዚህ ገናና መልአክ ሲመሰክር #ቅዱስ_ሚካኤል ቀን በደመና ሌሊት በብርሃነ እሳት መራቸው ሕዝበ እስራኤል በጎዳናቸው ፊት ፊት እየሔደ ሕዝቡን በደስታ አወጣቸው መልአኩን ላከ አዳናቸው በማለት ታዳጊነቱን ዘምሯል
ዳግመኛም #በእግዚአብሔር ቸርነት #ቅዱስ_ሚካኤል እስራኤል ሲበድሉ እያማለደ ሲራቡ እየመገበ ሲደክሙ እያበረታ ልብሳቸውና ጫማቸው እንዳያልቅ አድርጎ ዐርባ ዓመት ሙሉ ተንከባክቦ እንደ ጠበቃቸው ቅዱስ ያሬድ በድጓው እንዲህ ይገልጠዋል
መስፈርት የሌለው አምላክ አስፈሪ ባሕርን ግድግዳ አደረገ በውስጧም መንገድን አሳየ #በመልአኩ እጅ ጠበቃቸው አርባ ዓመት ሙሉ በዱር ኅብስተ መናን መገባቸው በማለት ተናግሯል
#ነቢዩ_ዳንኤልም ስለወገኖቹ ስለ እስራኤል ነፃነት ሲል ከፋርስ ንጉሥ በሚያደርገው ትግል #ቅዱስ_ሚካኤል ሊረዳው እንደመጣ መስክሯል ነቢዩ ዳንኤል የተናገረውን የምስክርነት ቃል ሊቁ እንዲህ ሲል በዜማ ገልጦታል
ቀደምት ከሆኑ ቅዱሳን መላእክት አንዱ #ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ አለ አፀናኝ አትፍራም አለኝ #ዳንኤል ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን ፅና ታገሥ ብሎ ሲናገረኝ ፀናሁ #መልአኩ_ሚካኤል ሆይ አፅንተኸኛል አልኩት በማለት ዘምሯል
የመልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል ጥበቃና ተራዳኢነት አይለየን ሀገራችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን የቅዱሳን #አበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁንልን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👉 ታህሳስ 12/2018 ዓ/ም
8 hours ago | [YT] | 7
View 1 reply
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
https://youtu.be/PKG6bRFpOcQ?si=bxqwc...
9 hours ago | [YT] | 1
View 0 replies
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
የአእላፋት ዝማሬ ስብስቦች ክፍል 2 👇👇
https://youtu.be/efPLNc4dcEk?si=VTcSc...
4 days ago | [YT] | 2
View 0 replies
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
https://youtu.be/ORsR5fu-7vg?si=biyy8...
5 days ago | [YT] | 6
View 0 replies
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
ታህሳስ 6
ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ)
✝እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው።
✝መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና።"(ማቴ. ፭፥፲፩) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት። ቅድስት አርሴማ ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት። ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት። ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት፦ ፩.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት ፪.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት ፫.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት። ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት።
✝መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር። ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስን ጻድቃን የምንላቸው። በኋላ ግን ማኅደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ። በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ። በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም። ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው። ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት። ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ፤ አይሆንም።" አለችው። ሊያስፈራራት ሞከረ። ዓይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው። አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው። እጅግ ስላፈረ አስገረፋት፣ አሰቃያት፣ ዓይኗንም አወጣ። በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት። ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው።
✝የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ። የንጉሡ እኅት ስታለቅስ በራእይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም።" አላቸው። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት። ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም። ለአሥራ አምስት ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው። ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው። የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በአሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮጵያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል። ለዚህም ነው ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ፍቅር ያላት።
✝በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ ስባ ውስጥ የሚገኝ ነው።) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና። ነገር ግን ወንድሞቼና እኅቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ። የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን። አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና።" (መዝ. ፸፭፥፭) በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል። ይህች እናት እመ ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት፣ ታጸናት፣ ከጐኗም ትቆምላት ነበር።
✝ረሃቧን፣ ጥሟን፣ ስደቷን፣ መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች። በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች። ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍልሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
6 days ago (edited) | [YT] | 28
View 0 replies
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
https://youtu.be/XtkMnGcejk8?si=xnCZk...
1 week ago | [YT] | 6
View 0 replies
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
" ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ " ( መዝ 45:4)
⛪⛪ ⛪ ታህሳስ 3( ፫)ባዕታ ለማርያም 🔔🔔🔔
እንኳን ለእናታችን እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ💕🙏
🌹 ባዕታ ለማርያም 🌹
" ባዕታ" ማለት ባዕት ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን መግባት ማለት ነው! ባዕታ ለማርያም ስንል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታኅሣሥ 3, ቀን ወደ ቤተመቅደስ የገባችበት እለት በመሆኑ ወር በገባ በ3ኛው ቀን የምናከብረው ታላቅ ቀን ነው!!!
በጸሎት እና በሱባዔ እግዚአብሔርን ደጅ ጸንተውና ስእለት የበረከት ፍሬ የሆነችውን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆች የሆኑት ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና በተባረከችና በተቀደሰች በታህሳስ 3 ቀን የዓለሙ ሁሉ ጌታ ክብርና መድኃኒት የሆነውን ጌታን ያስገኘችውን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምን ለቤተእግዚአብሔር ያስገቡበት ዕለት ነው፡፡
❗️ መቅደሲቷ ወደ መቅደስ ገባች
❗️ቅድስቲቱ ወደ ቅድስት ገባች
❗️ክብርቲቱ ወደ ክብርት ቤቷ ገባች
❗️ልዩ የሆነችው ወደ ልዩ ሥፍራ ገባች
❗️ቅድስተ ቅዱሳኗ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገባች
❗️ ንጽሕተ ንጹሐኗ ወደ ንጽሕና አዳራሽ ገባች💕
❗️ቤተ መቅደሷ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች
እንኳን አደረሰን ❤️ ጣዕሟ በከንፈራችን ፍቅሯ በልባችን ይኑር ። ከክፉ ሰው እና ከኃጢያት ሞት ባዕታ ማርያም በምልጃዋ ትጠብቀን።
የእመቤታችን ፍቅር ፣ በረከት ፣ ምልጃ አይለየን።
ስለ ታህሣሥ 3 ታሪኩን ሊንኩን ይጫኑ።👇👇
https://youtu.be/LqvP9YFJwP4?si=TQiav...
1 week ago (edited) | [YT] | 7
View 0 replies
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
ታህሳስ 3/2018 #እናታችን_ቅድስት_ባዕታ_ማርያም
#ፆመ_ነብያት_19ኛ_ቀን
በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በእናታችን ስም ለምናመሰግንበት ለእናታችን #ቅድስት_ባዕታ_ማርያም አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ።
ታኅሣሥ ፫ #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን ነው ይህንን ቀን ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች
እመቤታችን ከአባቷ ከቅዱስ #ኢያቄም ከእናቷ ከቅድስት #ሐና ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች ግንቦት 1 ቀን ሊባኖስ በምትባል አካባቢ ተወለደች፡፡
እመቤታችን በፆም በፀሎትም የተገኘች የስዕለት ልጅ ናት ንጽሕት በመሆኗም #የእግዚአብሔር_ማደሪያ ሆናለች ከዚህ በኋላ እመቤታችን በእናት በአባቷ ቤት 3 ዓመት ተቀመጠች
ኢያቄምና ሐናም ልጃቸውን ሲያሳድጉ ስላደረገላቸውም ሁሉ #እግዚአብሔርን ፈፅመው እያመሰገኑት 3 ዓመት ኖሩ በፆም እና በፀሎት ተወስነው ለድሆችና ለጦም አደሮች ምጽዋት እየሰጡ በጐ ሥራን አበዙ፡፡
ልጃቸውንም #ድንግል_ማርያምን በንጽሕና ሲያሳድጉ ሦስት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ #ሐና ባሏን #ኢያቄምን ወንድሜ ሆይ ልጃችንን ለቤተ #እግዚአብሔር ብፅዐት አድርገን እንስጥ ልጃችን ቤተ #እግዚአብሔርን ልታገለግል እንጂ በዚህ ዓለም እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን አስብ አለችው ኢያቄምም ይህን ነገር ከሚስቱ በሰማ ጊዜ ደስ አለው።
ነቢየ #እግዚአብሔር ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ክርስቶስ ውበትሽን ንጽሐ ባሕርይሽን ወድዷልና መዝ.44፥10-11 ብሎ እንደተናገረ #ለወላጆቿ_የብፅአት_ልጅ የሆነችው ድንግል ማርያም ከእናት ከአባቷ ተለይታ ታህሣሥ 3 ቀን በ 3 ዓመቷ ወደ መቅደሰ ኦሪት ገብታለች
#ባዕታ _ለማርያም ማለትም የድንግል #ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ማለት ነው #ካህኑ_ዘካሪያስም ስለምትመገበው ምግብ በተጨነቀ ጊዜ መልአኩ ቅዱስ #ፋኑኤል ከሰማያት ወርዶ አንድ ክንፉን ጋርዶ አንድ ክንፉን አጐናፅፎ ኅብስቱን አብልቷት ወይኑን አጠጥቷት የብርሃን ፅዋ እና የብርሃን መሶብ ይዞ ወደ ሰማይ ተመልሷል
እመቤታችንም ከዚህ በኋላ ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላአክት ጋር እየዘመረች ፈጣሪዋን እያመሰገነች 12 ዓመት #በቤተ_መቅደስ ተቀመጠች
የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ እያልን ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ኤፍሬም ለቅዱስ ያሬድ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለፀች #እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ለበላኤ ሰብዕ የተለመች #እመ_አምላክ ለኛም ትለመነን ከልጅዋ ከወዳጅዋ #ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን የቅዱሳን #አበዉ_ነብያት ምልጃና ፀሎት ከኛ ጋር ይሁን "አሜን"
አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሀገራችንን ኢትዮጲያን በምህረት አይኑ ይጎብኝልን የእናታችን ቅድስት #ባዕታ_ማርያም በረከት ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ታህሳስ 3/2018 ዓ/ም
1 week ago | [YT] | 12
View 0 replies
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
#በስመአብ _ወወልድ _ወመንፈስ_ቅዱስ_አሃዱ_አምላክ_አሜን
[ኅዳር 8 የእግዚአብሔርን ዙፋን የሚሸከሙ የኪሩቤልና የሱራፌል ዓመታዊ በዓል፤ ክብራቸውና ስማቸው]
ክብራቸው ታላቅ የኾኑት የኪሩቤልን ነገር ሊቁ ኤጲፋንዮስ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ ኪሩቤል ካህናተ ቅዳሴ ወውዳሴ እምታሕተ ሐቌሆሙ አሐዱ ወእምላዕለ ሐቌሆሙ አርባዕቱ እለ ግሉፋን በአዕይንት” ብሎ እንደገለጸው ኹለተኞቹ አመስጋኞች የኾኑት ዐሥሩን ነገድ ስማቸው ኪሩቤል ሲባሉ ከወገባቸው በታች አንድ ከወገባቸው በላይ አራት አድርጎ ሲፈጥራቸው ዐይናቸው ብዙ ነው፤ አለቃቸውም ኪሩብ ሲኾን የሰው መልክና የአንበሳ መልክ ያለው ነው፡፡
❖ ሦስተኛውን ዐሥሩን ነገድ ስማቸው ሱራፌል ሲባል የእነዚኽ አለቃቸው የንስር መልክና የእንስሳ መልክ ያለው ነው፤ አለቃቸውም ሱራፊ ሲባል ሲፈጥራቸውም ስድስት ስድስት ክንፍ አድርጎ ፈጥሯቸዋል፨
❖ ልዑል እግዚአብሔር ከነገደ ኪሩቤል ኹለት ገጸ ሰብእ እና ገጸ አንበሳን፤ ከሱራፌል ኹለት ገጸ ንስርና ገጸ እንስሳን አንሥቶ ከኢየሩሳሌም ሰማያዊት በላይ ከሰማይ ውዱድ በታች አቁሞ በነርሱ ላይ ሰማይ ውዱድን እንደ መረሻት ጫነባቸው፤ በላይም ሕብሩ በረድ የመሰለውን ዙፋን እንደ ሠረገላ ጭኖባቸዋል፤ እነዚኽንም በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን፣ በደቡብ በአራቱ መኣዝን ዠርባቸውን ወደ ውስጥ ፊታቸውን ወደ ውጪ እያደረገ አቁሟቸዋል።
❖ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለዚኽ ነገር በምዕ ፩፥፲፪ ላይ “እያንዳንዱም ወደ ፊት ቀጥ ብሎ ይኼድ ነበር መንፈስም ወደሚኼድበት ኹሉ ይኼዱ ነበር ሲኼዱም አይገላመጡም ነበር” በማለት እንደተናገረ ገጽ ለገጽ ሳይተያዩ ሥላሴ በፈቀዱት ፍኖት አንዱ በኼደበት ሦስቱ እየተከታተሉ ይኼዳሉ፡፡
❖ እነዚኽንም እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል ገለጻ ፲፮ ሲኾኑ የቀሩት ከውስጥ ስለኾኑ ስለማይታዩ አራቱ ግን ብቅ ብቅ ብለው ስለሚታዩ ዮሐንስ አራት ብሏቸዋል እንጂ እንደ ሕዝቅኤል ገጻቸው ፲፮ ነው ይላሉ መተርጉማን፡፡
❖ ሊቁ “እምርእሶሙ እስከ ሐቌሆሙ አርባዕቱ ወእምሐቌሆሙ እስከ እግሮሙ አሐዱ ከመ ርእየተ እለ ቄጥሩ ዘውእቱ ዖፍ ዘይነብር በሀገረ ፋርስ” እንዲላቸው፤ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም “ከመ ርእየተ እለቄጥሩ ገጸ በገጽ ኢይትናጸሩ” ብሎ እንደገለጻቸው በፋርስ ሀገር የሚኖረው እለቄጥሩ የተባለውን ዎፍ ከወገቡ በታች አንድ ከወገቡ በላይ አራት እንደኾነ እነዚኽንም ከወገባቸው በታች አንድ ከወገባቸው በላይ አራት አድርጎ ፈጥሯቸዋል ፡፡
❖ ኪሩቤልን “እለ ብዙኃት አዕይንቲሆሙ” አላቸው፤ ከላይ እስከ ታች ድረስ ዐይንን የተመሉ ናቸውና፤ ይኽስ አይደለም እንደ ብርሌ እንደ ብርጭቆ እያብለጨለጨ ለዐይን ባልተመቸም ነበር ብሎ ዐልፎ ዐይን ዐልፎ ዐይን ነው፤ እንደ አልጋ መለበሚያ እንደ ሱቲ መጠብር እንደ ቀሽመሪ መታጠቂያ፣ እንደ ነብር ለምድ፣ እንደ ዐይነ በጎ፣ እንደ ማር ሰፈፍ ይላሉ፤ ይኽስ አይደለም ብሎ ዐይናቸው ከአንገታቸው በላይ ሰድ ነው፤ ይኽም እንደ መስታዮት እያወለወለ እንደ ብርጭቆ እያንጸበረቀ አይደለም ብሎ ኀላፍያትን መጻእያትን የሚያውቁ ስለኾነ እንዲኽ አለ እንጂ ዐይናቸውስ ኹለት ነው ይላሉ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት መተርጉማን ፡፡
❖ በኢሳ ፮፥፩-፫ ላይ፡- “ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየኹት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን መልቶት ነበር፤ ሱራፌልም ከርሱ በላይ ቆመው ነበር ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው በኹለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር በኹለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር በኹለቱም ክንፍ ይበር ነበር፤ አንዱም ለአንዱ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ኹሉ ከክብሩ ተመልታለች እያለ ይጮኽ ነበር” ይላል ይኽ መሸፈናቸው ያድናቸዋል ቢሉ? ትእምርተ ፍርሀት ነው፤ ዛሬ በዚኽ ዓለም ሴቶችን ሕፃናትን እንመታችኋለን ባሏቸው ጊዜ እጃቸውን መጋረዳቸው የሚያድናቸው ኾኖ ሳይኾን ትእምርተ ፍርሀት እንደኾነ ኹሉ፡፡
አንድም በኹለት ክንፋቸው ፊታቸውን መሸፈናቸው ፊትኽን ማየት አይቻለንም ሲሉ በኹለት ክንፋቸው እግራቸውን መሸፈናቸው ከፊትኽ መቆም አይቻለንም ሲሉ፤ ኹለት ክንፋቸውን ወዲያና ወዲኽ ያደርጋሉ አለ ትእምርተ ተልእኮ ነው፡፡
አንድም በኹለት ክንፋቸው ፊታቸውን መሸፈናቸው ባሕርይኽን መመርመር አይቻለንም ሲሉ፤ በኹለት ክንፋቸው እግራቸውን መሸፈናቸው ባሕርይኽን መረማመድ መተላለፍ አይቻለንም ሲሉ፤ ኹለት ክንፋቸውን ወዲያ ወዲኽ ያደርጋሉ ከእእምሮ ወደ አእምሮ ለመፋለሳቸው፡፡
አንድም ኹለት ክንፋቸውን ወደ ላይ አድርገው ይታያሉ አለ ወደላይ ቢወጡ ቢወጡ አትገኝም ሲሉ፤ ኹለት ክንፋቸውን ወደታች አድርገው ይታያሉ ወደታች ቢወርዱ ቢወርዱ አትገኝም ሲሉ፤ ክንፋቸውን ወዲያና ወዲኽ ያደርጋሉ ወዲያና ወዲኽ ቢሉ አትገኝም ሲሉ፤
አንድም ወደላይ መዘርጋት በሰማይ ምሉእ ነኽ ሲሉ ወደታች መዘርጋቸው በምድርም ምሉእ ነኽ ሲሉ፤ ወዲያና ወዲኽ መዘርጋታቸው በኹሉ ምሉእ ነኽ ማለታቸው ነው፤
አንድም ወደላይ መዘርጋት ትእምርተ ተመስጦ ወደታች መዘርጋት ትእምርተ ትሕትና፤ ወዲያና ወዲኽ ረብቦ መታየት ትእምርተ ተልእኮ ነው
❖ በአጠቃላይ ኹለት ክንፋቸውን ወደላይ ኹለት ክንፋቸውን ወደታች ኹለት ክንፋቸውን ወዲያና ወዲኽ አድርገው ትእምርተ መስቀል መሥራታቸው በብሉይ ኪዳን ከኾነ እንዲኽ ባለ መስቀል ተሰቅለኽ ዓለምን ታድነዋለኽ ሲሉ በዘመነ ሐዲስ የኾነ እንደኾነ እንዲኽ ባለ ትእምርተ መስቀል ተሰቅለኽ ዓለምን አድነኸዋል ሲሉ ነው፡፡
❖ የእነዚኽ አርባዕቱ እንስሳ መላእክት ፊታቸው በርካታ ምስጢራትን ሲያመለክቱ ገጸ ሰብእ በማቴዎስ፤ ገጸ አንበሳ በማርቆስ፤ ገጸ ላሕም በሉቃስ፤ ገጸ ንስር በዮሐንስ ተመስሏል።
❖ በሌላ ምስጢር የሰው ገጽ ያለው የጌታን ሰው የመኾንን ነገር፤ የላም መልክ ያለው በቀራንዮ ላይ ደሙን ማፍሰሱ፤ የአንበሳው መልክ ያለው የጌታችንን ትንሣኤ፤ የንስር መልክ ያለው የጌታን ዕርገት እንደሚያመለክቱ ቀደምት መተርጒማን ይተነትኑታል።
❖ዐምደ ሃይማኖት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም እጅግ ምጡቅ በኾነው ዕውቀቱ ዕጓለ አንበሳ የተባለው የወልድ የባሕርይ አባቱን አብን በአንበሳ ይመስለዋል።
❖ሥጋን ተውሕዶ ፍጹም ሰው የኾነው ወልድን የሰው መልክ ባለው መስሎ ገልጾታል፡፡
❖ በአምሳለ ርግብ ወርዶ በወልድ ራስ ላይ ተቀምጦ የታየው መንፈስ ቅዱስን የንስር መልክ ባለው መስሎ አብራርቶ ጽፎታል።
❖በቀንዱ የማይበራታ ላሕም ተብሎ የተመሰገነው የወልደ እግዚአብሔር ቅዱስ ሥጋው የሚፈትትባት፤ ክቡር ደሙ የሚቀዳባት በአራቱ ኪሩቤል አምሳል አራት መአዝን ያላት ቤተ ክርስቲያንን በገጸ ላሕም አምሳል ገልጦ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ ስማቸውን በመጥቀስ ሲያወድሳቸው፦
[“ሰላም ለ፬ እንስሳሁ ለአብ እለ ይጸውሩ መንበሮ እለ ስሞሙ አግርሜስ ገጸ አንበሳ፡፡ አግርሜጥር ገጸ ሰብእ፡፡ ባርቲና ገጸ ላሕም፡፡ አርጣን ገጸ ንስር፡፡ ለቀዳማዊ ገጹ ከመ አንበሳ፤ በአምሳለ ፈጣሪሁ ዘውእቱ አብ፡፡ ለካልዕ ገጹ ከመ ሰብእ በአምሳለ ወልድ፤ ዘውእቱ ነሥአ ፍጹመ ስባኤ፡፡ ለሣልስ ገጹ ከመ ንስር በአምሳለ መንፈስ ቅዱስ ዘውእቱ አስተርአየ በርእየተ ርግብ በሥጋ፡፡ ወለራብእ ገጹ ከመ ላሕም በአምሳለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ እስመ ፬ቱ መኣዝኒሃ”፡፡]
(የአብ ዙፋኑን ለሚሸከሙና ስማቸውም የአንበሳ መልክ ያለው አግርሜስ፤ የሰው መልክ ያለው አግርሜጥር፤ የላም መልክ ያለው ባርቲና፤ የንስር መልክ ያለው አርጣን ለተባሉ ለአራቱ እንስሳ ሰላምታ ይገባል፤😍😍
አርባእቱ እንስሳ #ሱራፌልና_ኪሩቤል በምልጃ ፀሎታቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቁልን ይሁንልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️
1 month ago | [YT] | 11
View 0 replies
Adam Media / አዳም-ሚዲያ
ህዳር 7 ቅዳሴ ቤቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ
በዚህች ቀን የፋርስና የልዳ ፀሐይ የተርሴስና የቤሩት ኮከብ የባህርና የየብሰ ብርሃን የጌታችን የመድሐኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ምስክር የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ቀን ነው።
ይህንንም ቀን በመላ ኢትዮጰያ በተለይም የቅዱስ ጊዮርጊስ የቃል ኪዳኑ ታቦት ከያለበት ቤተመቅደስ ወጥቶ ህዝበ ምዕመናኑን ይባርካል ታሪኩ በአጭሩ እንዲህ ነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሚያዚያ 23 ቀን በሰማዕትነት ከሞተ በኃላ አጋልጋዮቹ እጅግ የከበሩ ልብሶችና ያማሩ ሽቶዎች አዘጋጁ በከበረ አገናነዝም ገነዙት በመርከብም ጭነው ወደ ትውልድ አገሩ ልዳ አመጡት ነገር ግን ቤተሰቦቹ በሙሉ ማለትም አባቱ ዘሮንቶስ እናቱ ቴዎብስታ እህቶቹ ማርታና እስያ እንዲሁም አጭተውለት የነበረች እጮኛው ሁሉም ሞተው አገኙዋቸው፤ እንድርያስ የሚባል አጎት ነበረው ስጋውን ተቀበላቸው አገሬው ተሰበሰበ የእየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎድሮስ ተጠርቶ መጣ ቤተክርስቲያኑን አነጹለት ስጋውንም በዚያ በክብር አኖሩት፤ በዚህች ቀን እጅግ ብዙ የሆነ ድንቅ ታአምራትና ታላላቅ ኃይላት ተደረጉ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ይህንን ቀን ታከብረዋለች።
ልበ ብልሁ ንጉሳችን እምዬ ምኒሊክ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን ሲሰሩ ከዚሁ ከልዳ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ካለበት አፈሩን በመርከብ ከዚያም በበቅሎ አስጭነው አምጥተው ለቤተክርስቲያኑ መሰረት አድርገውታል ቅጥሩን ዙርያውንም ነስንሰውታል ይላል። ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚከበርባቸው ሚያዚያ 23 እረፍቱ ህዳር 7 ቅዳሴ ቤቱ ጥር 23 ዝርዎተ አጽሙ ናቸው፤ በረከቱን ያድለን።
እስኪ ሁላችንንም ባለንበት የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በረከት በሀገር ውስጥም. በውጭም ያላችሁ እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጲያ የተከሰተውን የፍቅር እና የሰላም እርሀብ እግዚሐብሔር አምላክ ለእኛ ለተራብነው ምህረትን. ከማይጎልበት ሀብቱ በረከትን ይላክልን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥኖ ይድረስልን።
ምንጭ ገድለ ጊዮርጊስ ምዕራፍ 9 ላይ ይገኛል
1 month ago | [YT] | 16
View 0 replies
Load more