ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና ማዕከል በሁለት ውጤታማ የስነ ምግብ ሕክምና ባለሙያዎች (Dietitians) የተመሰረተ ነው። ባለሙያዎቻችን በሙያው የሰለጠኑ እንዲሁም ከሚመለከተው የመንግስት አካል (የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ) የሙያ ፈቃድ ያላቸው ናቸው!
ወደ ቢሮአችን ሲመጡ ማንኛውንም ከአመጋገብ እና ጤና ጋር ተያያዥ የሆኑ ምክሮችን እና አገልግሎቶችን በብቃት ያገኙበታል።
• ክብደትን በጤናማ መንገድ ብቻ ለማስተካከል
• የተለያዩ ሥር ሰደድ ሕመሞችን በአመጋገብዎ ለመከላከል እና ለምምቆጣጠር (የደም ግፊት ፣ የስኳር ሕመም ፣ የኮሌስትሮል መዛባት ፣ የአንጀት ችግሮች ፣ የመገጣጠሚያ ሕመሞች እና ሌሎችም)
• የጨቅላ ሕፃናት እድገት ክትትል እና ተጨማሪ ምግቦችን ስለማስጀመር
• የቁስል መዳንን ለማገዝ
• የአመጋገብ ልዩ ፍላጎት ላላቸው እገዛ
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሚያዘወትሩ ተገቢ አመጋገብ (Sport nutrition)
• ልዩ ልዩ ትምህርት እና ስልጠናዎች አገልግሎቶቻችን ናቸው።
ይደውሉልን!
0903832121
0922144948
መጥተው ይጎብኙን!
ብሥራተ ገብርዔል የሚገኘው ላፍቶ ሞል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 112.
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና ፤ የጤናማ ሕይወት ዘይቤ አጋርዎ!
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ አክል ፤ የጤናማ ሕይወት ዘይቤ አጋርዎ!
1 year ago | [YT] | 1
View 0 replies
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
1 year ago | [YT] | 4
View 0 replies
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
በኢቢኤስ ቴሌቭዥን ቅዳሜን ከሰዓት የነበረን አጭር ቆይታ #ኑትሪዮጵያ #ጤናማአመጋገብ #ቅዳሜንከሰዓት #ስነምግብ #ጤና #ebs #ebstv
1 year ago | [YT] | 0
View 0 replies
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
ኢድ ሙባረክ 🎉🎉🎉 Eid Mubarak 🎉🎉🎉
1 year ago | [YT] | 3
View 0 replies
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
ኮሌስትሮልን ለመቀነስ እንዴት እንመገብ?
በቅድሚያ ስለኮሌስትሮል ምንነት ጥቂት ማለት ይጠቅማል።
ኮሌስትሮልን በቀላሉ ለመረዳት በደም / በደም ስሮች ውስጥ የሚገኝ ቅባት ነው ልንል እንችላለን። ይህም ከደም ስር እና ልብ ጤና ጋር ከፍተኛ ተያያዥነት አለው።
ኮሌስትሮል በአብዛኛው በሰውነታችን ውስጥ በተለይ በጉበት ውስጥ የሚመረት ሲሆን አነስተኛ መጠን ደግሞ ከምንመገበው ምግብ (በተለይ ከእንስሣት ተዋጽዖዎች) ጋር ተያይዞ በሰውነታችን ውስጥ ይገኛል ፤ ይህም ቢሆን ግን አመጋገባችንን በመቆጣጠር በሰውነታችን ውስጥ ሊገኝ የሚችል አላስፈላጊ ኮሌስትሮልን ልንቆጣጠረው እንችላለን።
ኮሌስትሮል በሁለት አይነት ሁኔታ በሰውነታችን ውስጥ ሊገኝ ይችላል፤ ይህም ጥሩ ኮሌስትሮል (Good cholesterol) እና መጥፎ ኮሌስትሮል (Bad cholesterol) በመባል የሚገለጽ ነው።
በሕክምና ወቅት ኮሌስትሮልን ለመቀነስ ስናስብ እንድንቀንስ የሚፈለገው መጥፎውን ኮሌስትሮል (LDL) ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ጥሩ የሚባለውን የኮሌስትሮል አይነት (HDL) መጨመር እንፈልጋለን።
አመጋገባችንን ውስጥ ምን ብናካትት መጥፎ የሚባለውን የኮሌስትሮል አይነት መቀነስ እንችላለን?
እንደ አጠቃላይ አመጋገባችን አትክልት እና ፍራፍሬ ተዋጽዖዎች እና ጤናማ ቅባቶች ላይ ዋነኛ ትኩረት ማድረግ ይኖርብናል። ስለዚህ እለት እለት በእያንዳንዱ ምግባችን ውስጥ በቂ አትክልት ማካተት እና በቀን ውስጥ በቂ ፍራፍሬ መመገባችንን እርግጠኛ መሆን ይኖርብናል።
በተጨማሪም በልዩ ትኩረት እነዚህን የምግብ አይነቶች ብንዘወትር ይጠቅማል።
1. ያልተፈተጉ እህሎች በተለይ አጃ
2. ጥራጥሬዎች (ድፍን ምስር፣ ባቄላ፣ አተር፣ ቦሎቄ ወዘተ)
3. አትክልቶች በተለይ ደበርጃን (Egg plant) እና ባሚያ (Okra)
4. የቅባት እህሎች (ተልባ፣ ለውዝ እና የለውዝ ዝርያዎች
5. ፍራፍሬዎች (ፖም፣ እንጆሪ፣ ወይን፣ አቮካዶ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ እና ተመሳሳይ ዝርያዎች)
6. የወይራ ዘይት
በተቃራኒው ማስወገድ ያለብን የምግብ አይነቶች ደግሞ
1. በጥልቅ ዘይት / ቅባት የተጠበሱ ምግቦች
2. ከፍተኛ የስብ መጠን / ጮማ
3. ከፍተኛ የጨው መጠን
4. በፋብሪካ የተቀነባበሩ እና የታሸጉ ምግቦች
5. ስኳር እና ልዩ ልዪ ተፈጠሮአዊ ያልሆኑ ማጣፈጫዎች ናቸው።
በተጨማሪም
• መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
• ልከኛ የሰውነት ክብደት እና የሰውነት ስብ መጠን መያዝ
• እንዲሁም የአልኮል መጠጥ እና ሲጋራን ማስወገድ
ይህን የጤና እክል ለመከላከልም ሆነ ለመቆጣጠር ይረዳል።
መልካም እና ጤናማ ጊዜን ተመኘሁ!
ኬብሮን ሠናይ (ዳይቲሺያን)
ለተጨማሪ ንባብ
የኑትሪዮጵያ የቴሌግራም ገፅ t.me/nutriopia
2 years ago | [YT] | 4
View 0 replies
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
የልጆች አመጋገብ እና ሁለንተናዊ እድገት (ክፍል 2)
ጥናቶች እንደሚያሳዩት እድሜ ከገፋ በኋላ የሚመጡ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች (ደም ግፊት፣ የስኳር ህመም፣ የልብ ህመም የመሳሰሉት) ብዙውን ጊዜ በልጅነታችን ከነበረን የአመጋገብ ስርዓት ጋር ከፍተኛ የሆነ ግንኙነት አላቸው። በተመሳሳይ ህፃናትን ከአቅም በላይ መመገብ (overfeed ማድረግ) ለአላስፈላጊ የሰውነት ክብደት መጨመር ሊያጋልጥ ይችላል። ይህ ደግሞ ለስኳር ህመምና ደም ግፊት ሊያጋልጥ ይችላል።
ልጆች ከምግብ የሚያገኟቸውን ንጥረ ነገሮች ሙሉ እንደሆኑ ለማረጋገጥ የሚመገቧቸው ምግቦች የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላታቸውን ማየት ይጠቅማል
• ጊዜያቸውን የጠበቁ ማለትም በተገቢው የእድሜ ክልል ከጡት ወተት በተጨማሪ ተጨማሪ ምግብን መጀመራቸውን
• ለእድገታቸው በቂ የሆነ የኃይል (energy)፣ ገንቢ ንጥረ ነገር፤ (protein) ቫይታሚንና መዕድናትን ያሟሉ መሆናቸው
• ደህንነታቸው የተጠበቀ ማለትም ንፅህናቸውን ጠብቀው የተሰሩና የተቀመጡ እንዲሁም ስንመግባቸው ንፅህናችንን ጠብቀን መሆኑ
• ሲርባቸው በአግባቡ ማብላትና ሲጠግቡ ማቆም እንዲሁም ጊዜውን ጠብቆ እንደዕድሜያቸው የሚያሰፈልጋቸውን ምግብ መመገብ አስፈላጊ ነው።
የአለም ጤና ድርጅት ህፃናት 6 ወር ከሞላቸው በኋላ ከጡት ወተት በተጨማሪ ምግብ መጀመር እንዳለባቸው ያስቀምጣል። ተጨማሪ ምግቦቹ መጠናቸው እንደየእድሜያቸው እየጨመረ የሚሄድ ነው።
ከ6-8 ወር በቀን ከ2-3 ጊዜ፤ ከ9-11 ወር ደግሞ ከ4-5 ጊዜ ተጨማሪ ምግብ ያስፈልጋቸዋል። ከ1 ዓመት በኋላ በቀን 1 ወይም 2 ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ ከዋና ምግቦች በተጨማሪ መክሰስ መመገብ ይኖርባቸዋል።
በተጨማሪም እንደ እድሜያቸው የምግቦቹን ይዘትና ውፍረት (texture and consistency) መጨመር አስፈላጊ ነው። ማለትም 6 ወር ላይ ምግብ ሲጀምሩ በሚገባ የላመና የተፈጨ ምግብ፤ ከ7-8 ወር ባለው ጊዜ ደግሞ ትንሽ ወፈር ያለና ውስጡ የሚታኘክ ነገር ያለው ምግብ፤ 9 ወር ከሞላቸው በኋላ በእጅ ተይዘው የሚበሉ ምግቦችን (finger foods) መልመድ መጀመር ይኖርባቸዋል። ልጆች እድሜያቸው 1 ዓመት ከሞላ በኋላ ቤተሰብ የሚበላውን ምግብ መጀመር ይኖርባቸዋል። (ይህን ስንል ግን የቤተሰቡ ምግብም የተመጣጠነና ጤናማ መሆን እንደሚኖርበት ልብ ይሏል)
በተጨማሪም ከ6-8 ወር ላሉ ልጆች ተጨማሪ ምግብ ከማብላትዎ በፊት መጀመሪያ ላይ የጡት ወተትን ያስቀድሙ።
ሌላው ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ለመታነቅና ለትንታ የሚያጋልጡ ምግቦችን (ለምሳሌ እንደ በቆሎ፤ ኦቾሎኒ የመሳሉትን) ለልጆች መስጠት ካስፈለገ እንደ እድሜያቸው እና በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል ፤ አልያም ከፍ እስኪሉ ባይሰጡ ይመከራል።
በተመሳሳይ ደግሞ ሻይ፣ ቡናና የለስላሳ እንዲሁም ሌሎች የታሸጉ ምግብና መጠጦችን ለልጆች ባይሰጡ ይመከራል፤ ምክንያቱም በውስጣቸው ለልጆች እድገት ምንም ጠቃሚ ንጥረ ነገር የሌላቸው ስለሆኑ እና ከያዙአቸው ጣፋጮች እና ተፈጥሮአዊ ያልሆኑ ግብዓቶች የተነሳ መመገብ ያለባቸውን ምግቦች በአግባቡ እንዳይመገቡ ስለሚያደርጓቸው ነው።
የፍራፍሬ ጭማቂዎችንም መስጠት ስንፈልግ እንዲሁ በብዛት መስጠት ወይም ማዘውተር አያስፈልግም ፤ ምክንያቱም ጭማቂዎች ቶሎ ሆድ ስለሚሞሉ ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን ለመብላት ፍቃደኛ ስለማይሆኑልን ነው። እንዲሁም ሙሉ ፍራፍሬውን እንዲመገቡት ማለማመድ የተሻለ የአመጋገብ ክህሎታቸውን ያግዛል እንዲሁም ከሚያስፈልጋቸው በላይ ንጥረ ነገሮችን ከተመሳሳይ የምግብ አይነት ብቻ እያገኙ እንዳይሄዱ ይረዳል።
መልካም ጊዜ!
2 years ago | [YT] | 0
View 0 replies
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
የልጆች አመጋገብ እና ሁለንተናዊ እድገት (ክፍል 1 )
ምግብ በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ልጆች ከተወለዱበት እስከ 2 አመት እድሜያቸው ድረስ ያለ አመጋገባቸው ለአእምሮአዊም ሆነ አካላዊ እድገታቸው እጅግ ወሳኝ ነው፤ ስለዚህ በዚህ ወቅት አስፈላጊው ሁሉ ተሟልቶላቸው እንዲያድጉ በልጆች ዙርያ ያሉ ሁሉ ኅላፊነት መውሰድ ይኖርባቸዋል።
በቅድሚያ ልጆችን በምንመግብበት ወቅት ማወቅ ከሚገቡን ነገሮች መካከል ማሳተፍ (responsive feeding) የምንለውን ነው ፤ ይህም ልጆች ምግብን እንዲሁም የአመጋገብ ሂደትን እንዲወዱት ይረዳናል።
ልጆችን ስንመግብ የስነ ልቦና እና ማህበራዊ እድገታቸውን ታሳቢ ያደረጉ መመርያዎችን (principles of psychosocial growth and development) መከተልም እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ እድሜአቸው ከአመጋገብ በተጨማሪ ለእነርሱ ብዙ አይነት ክህሎቶችን (life skills) የሚማሩበት ጊዜ ስለሆነ ነው።
ልጆችን ስንመግብ ተሳትፎአቸውን የምንጨምርባቸው መንገዶች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
1ኛ. ልጆች እንደየእድሜአቸው ራሳቸውን ችለው እንዲመገቡ ማበረታታት።
ጨቅላ ህፃናት በትልልቅ ሰዎች መመገብ ሲኖርባቸው ፤ ልጆች እድሜያችው ከፍ ሲልና በእጅ የሚያዝ ምግብ ካስጀመርናቸው በኋላ ግን በራሳቸው እንዲበሉ ማበረታታት እና ማገዝ (assist) ብቻ በቂ ነው፤ ሁል ጊዜ በእኛ እጅ ብቻ እንዲመገቡ መፈለግ የለብንም (ይህም ምግባቸውን እንዲወዱት እና በአመጋገብ ስርዓታቸው ላይ ኃላፊነት እንዲሰማቸው ከማድረግም በላይ በራስ መተማመናቸው እንዲጨምር ያግዛል)
2ኛ. የልጆችን የምግብ ምርጫ ማስፋት።
አንዳንድ ጊዜ ልጆች የምናቀርብላቸውን ምግብ ያለመፈለግ ሊያሳዩ ይችላሉ፤ በዚህ ጊዜ አልወደዱትም ብለን ሙሉ በሙሉ የምንተው / የምንቀይር ከሆነ ጠባብ የምግብ ምርጫ እንዲኖራቸው ወይም picky eaters እንዲሆኑ ስለሚያደርጋቸው በተለያየ ጊዜ በተለያየ አዘገጃጀት ደጋገመን መሞከር ይኖርብናል። ይህም የምግብ ምርጫቸውን እንዲያሰፉ እንዲሁም ከየምግቡ አይነት ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም ሁሉ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። እንዲሁም ይህንን በተደጋጋሚ በማድረግ ባህርይ አድርገው እንዳይዙትም ጭምር ያግዛል።
3ኛ. በምግብ ሰዓታቸው ተግባቦትን ማዳበር።
ለልጆች የምግብ ጊዜ ከመብላትም ባለፈ ከቤተሰባቸው እና አካባቢያቸው ካሉ ሰዎች ብዙ የሚማሩበት ስለሆነ እያዋራናቸው፣ እያጫወትናቸው እንዲሁም በተለያየ በሚገባቸው መንገድ communicate እያደረግናቸው ልንመግባቸው እና አብረናቸው ልንሆን ያስፈልጋል፣ በዚህ ጊዜ የተለያዩ ማህበራዊ ክህሎቶችን (social skills) እና ፍቅርን ይማራሉ፤ ስለ ምግብም መጥፎ አመለካከት ይዘው እንዳያድጉ ያደርጋቸዋል። ልጆችን በሚመግቡበት ጊዜ ከልጅዎ ጋር ጥሩ የጋራ ፣የመቀራረብ እና የአብሮነት ወይም bonding ጊዜ ያሳልፉ።
4ኛ. ልጆችን በማንኛውም ምክንያት በአመጋገብ ሁኔታቸውና በምግብ ምርጫቸው ከሌሎች ልጆች ጋር አለማወዳደር።
በማንኛውም ምክኛት በልጆች ላይ ይህን ማድረግ በፍጹም አያስፈልግም፤ ይህ ይበልጥ ምግብን እየጠሉ እንዲሄዱ እና ነፃነት እንዳይሰማቸው ከማድረጉም በላይ በራስ መተማመናቸውን የሚያወርድ ተግባር ስለሆነ ፈጽሞ ልናደርገው አይገባም።
5ኛ. ልጆችን በግድ እኛ በምንፍልገው መንገድ እና ሁኔታ እንዲመገቡ አለማድረግ።
ልጆችን ስንመግብ ማስገደድ ተገቢ አይደለም ፤ ምክንያቱም የቀረበውን ምግብም ሆነ የምግብ መብላት ስርዓቱን እንዲጠሉት ሊያደርግ ስለሚችል ነው። ልጆች እያጎረስናቸው እንዲመገቡ ማድረግ ያለብን በእጅ ተይዘው የሚበሉ ምግቦች እስኪጀምሩ ድረስ ብቻ ነው (ይህም ማለት እድሜያቸው 9 ወር እስኪሞላ ነው)፤ ከዚያ በኋላ ግን ለራሳቸው በሰሃን ሰጥተን በሚፈልጉት መንገድ እንዲመገቡ መፍቀድ ይኖርብናል።
በዚህ ጊዜ በሚገባ መረዳት ያለብን ነገር ቢኖር ፤ እኛ ባሰብነው መንገድ ላይበሉ ይችላሉ ማለትም፦
• ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ
• ራሳቸውን እና አካባቢያቸውን ሊያቆሽሹ ይችላሉ
• ምግባቸውን ሊደፉ ይችላሉ ወይም በተለያየ ምክንያት እኛ በቂ ብለን በምናስበው መንገድ ላይመገቡልን ይችላሉ።
ነገር ግን ታግሰን እንዲለምዱ ማድረግ ይኖርብናል፣ እንዲሁም እርዳታችንን ሲፈልጉ ብቻ ልናግዛቸው ይገባል። ይህም በተመሳሳይ የኅላፊነት እና ተቆጣጣሪነት (control) ስሜት እንዲኖራቸው ስለሚያደርግ የምግብ ጊዜአቸውን እንዲወዱት እና እንዳይጨነቁ ይረዳል ፤ በጊዜ ራሳቸውን እየቻሉ ስለሚሄዱም ለእኛም በአመጋገባቸው ዙርያ ጭንቀትን በሂደት ይቀንስልናል።
ከዚህም ጋር በተያያዘ ደግሞ ምግብ ሲበቃቸው ያላቸውን ስሜት ልንረዳቸው ይገባል።
6ኛ. ልጆች በልተው ሳይጨርሱ ከስር ከስር ማጽዳት (እጃቸውን ፣ ፊታቸውን እና አካባቢያቸውን መጠራረግ) የለብንም ፤ ይህም ምግብን በትክክለኛው መንገድ እንዳይረዱት ያደርጋቸዋል።
7ኛ. ለልጆች ብቻቸውን ምግብ ከመስጠት ይልቅ በተቻለ ጊዜ ሁሉ ቤተሰብ ምግብ በሚበላበት ሰዓት አብረው እንዲበሉ ማድረግ የምግብ ፍላጎታቸው እንዲጨምር፤ ትኩረታቸው ምግቡ ላይ ብቻ እንዲሆንና ለብዙ ምግቦች ተጋላጭ እንዲሆኑ (exposure እንዲኖራቸው) ይረዳል።
ተጋላጭነት (Exposure) ስንል ግዴታ ስለሚበሉት ብቻ ሳይሆን አካባቢያቸው ላይ የቀረቡ ምግቦችን ማየትን፣ ማሽተትን፣ መንካትን፣ መቅመስን ወይም መሞከርን ሁሉ እንደሚያካትት ልንገነዘብ ይገባል።
በተጨማሪም ልጆች ምግብ ሲበሉ እንደ ቴሌቪዥን ፣ ስልክ እና የመሳሰሉ ትኩረታቸውን የሚስቡ ነገሮችን ማስወገድ ያስፈልጋል። ይህም ትኩረታቸውን በመውሰድ ምግቡን እንዳያጣጥሙት ከማድረጉም በላይ ከመጠን በታች ወይም በላይ እንዲበሉ ሊያደርግ ይችላል። በቀጣይም ካለእነዚህ ነገሮች ለመብላት ስለሚያስቸግሩ ለተንከባካቢዎቻቸው አስቸጋሪ ይሆናል።
ሌላው በሚገባ ማወቅ ያለብን ህፃናት በዚህ ወቅት ያላቸው አመጋገብ በእድገታቸው እና በቀጣይ እድሜያቸው እንዲሁም ጤናቸው ላይ ያለውን አስተዋጽዖ ነው። የምግቦችን ትክክለኛ የስነ ምግብ ይዘት አለማወቅና ስለ አንዳንድ ምግቦች ያለን መጥፎ አመለካከት ልጆች ከሚመገቡት ምግብ በቂ ንጥረ ነገር እንዳያገኙና በአግባቡ እንዳያድጉ ያደርጋቸዋል።
2 years ago | [YT] | 2
View 0 replies
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
ጤና ይስጥልን!
እነዚህ ልምዶች በአመጋገብ ዘይቤዎ ውስጥ ያሉ እንደሆነ ለኩላሊት መዳከም (Renal failure) ሊያጋልጥዎ እንደሚችሉ ያውቃሉ?
1ኛ. በደምዎ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የደም ስኳር መጠን በቋሚነት ካለ (በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ሕመም ካልዎት)
2ኛ. በቋሚነት ከፍ ያለ የደም ግፊት (በቁጥጥር ስር ያልዋለ የደም ግፊት) ሕመም ካለብዎ
3ኛ. መድኃኒቶችን በተለይም የሕመም ማስታገሻዎችን አዘውትረው የሚጠቀሙ ከሆነ
4ኛ. ቀደም ብሎ ያጋጠምዎ የኩላሊት ጉዳት / በኩላሊት ላይ የደረሰ አደጋ ከነበረ
5ኛ. ሲጋራን የማጤስ እና የአልኮል መጠጦች በብዛት የመጠቀም ልምድ ካልዎ
6ኛ. በአመጋገብዎ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የጨውና የስኳር አጠቃቀም ካልዎ
7ኛ. በቂ ውሃ (ፈሳሽ) የማይጠጡ ከሆነ
በአመጋገብ እና የሕይወት ዘይቤ ምክንያት ለሚከሰት የኩላሊት መዳከም ሊጋለጡ ይችላሉ።
ጤናማ የአመጋገብ ዘይቤን በመከተል ጤናዎን ይጠብቁ!
በአመጋገብ ጤና ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ቀጠሮ ለመያዝ በ 0903832121 ይደውሉ።
2 years ago | [YT] | 1
View 0 replies
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
🌼🌼🌼በእንቁጣጣሽ ስለምንመገበው ፌጦ የጤና በረከቶች በጥቂቱ
🌼 በተለያዩ ማዕድናትና ቫይታሚኖች ማለትም አይረንና ፎሌት እንዲሁም ቫይታሚን A፣ C እና E የበለፀገ ሲሆን በተጨማሪም ከአትክልት ተዋፅኦ የሚገኝ የገንቢ ንጥረ ነገር (plant source protein) እና አሰር በጥሩ መጠን ይይዛል።
🌼 የአስምና ሌሎች ተመሳሳይ የመተንፈሻ አካላት ህመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር፤
🌼 በደም ውስጥ የሚገኝ የሄሞግሎቢን መጠንን በማሻሻል የደም ማነስን ሊያሻሸል ይችላል፤
🌼 ሆድን በማጠብ ለአንጀት ጤና አስተዋፅኦ ያደርጋል፤
🌼 የማስታወስ ችሎታን (memory) ያሻሽላል፤
🌼 የወር አበባ መዛባትን ያስተካክላል፤
🌼 ለቆዳና ፀጉር ጤንነት ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ አለው፤
🌼 የሚያጠቡ እናቶች ላይ የጡት ወተት ምርታማነተን ይጨምራል፤
🌼 የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅምን ይጨምራል፤ የደም ስኳር መጠንን ይቆጣጠራል እንዲሁም የደም ግፊትንና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ይከላከላል።
🌼 እነዚህን ጥቅሞች ለማግኘት ፌጦን በሳምንት ውስጥ ከ1-2 ጊዜ 1 የሾርባ ማንኪያ ብንጠቀም በቂ ይሆናል።
ሙሉ መረጃውን ከፈለጉ የዩትዩብ ገፃችን ላይ ማግኘት ይችላሉ።
🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት!!!🌼🌼🌼
2 years ago | [YT] | 1
View 0 replies
ኑትሪዮጵያ የስነምግብ ሕክምና NutriOpia Diet Therapy
እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ!
በበዓላት ወቅት አመጋገባችን ከወትሮው በእጅጉ የተለየ እንደሆነ ይታወቃል። በዛሬው መረጃችን ትኩረት የምናደርገው በብዛት የምንጠቀመው የምግብ ቅባት ላይ ነው።
የምግብ ቅባት ስንል ለማብሰያነት የምንጠቀማቸውን ዘይት እና ቅቤ እንዲሁም በተለያዩ የምግብ ግዓቶች ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኙትን (እንደ ቅባት እህሎች ፣ የእንስሣት ተዋጽዖዎች እንዲሁም የአትክልት ተዋጽዖዎች ) ያጠቃልላል።
የምግብ ቅባቶች እንደ ምንጫቸው እንዲሁም እንደ አጠቃቀማችን ጤናችን ላይ ያላቸው ውጤት የተለያየ ነው ፤ ስለዚህ በተወሰነ መጠን አስፈላጊ የሆኑትን የምግብ ቅባቶች እየተጠቀምን ነገር ግን ጤናችንን በማይጎዳ መልኩ ለማድረግ
1ኛ. በአነስተኛ መጠን መጠቀም።
ይህን ስንል ምግቦቻችንን ስናዘጋጅ የምንጠቀመው ዘይት ወይም ቅቤ የተመጠነ መሆን አለበት ፤ ይህም እንደ አማካይ ብንወስድ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ከ45 ሚ.ሊ (3 የሾርባ ማንኪያ) በላይ ዘይት እና ቅቤን (በድምሩ) ባይጠቀም ይመከራል።
2ኛ. አበሳሰሉን ጤናማ ማድረግ።
የምንጠቀመውን የቅባት መጠን ብናስተካክልም እንኳን የምግብ ቅባታችንን ለረጅም ጊዜ እና በከፍተኛ ሙቀት ካበሰልነው ጤናማነቱን ስለሚለቅ በመጨረሻ መጨመሩ ተመራጭ ነው።
3ኛ. ተፈጥሮአዊ እና ጤናማዎቹ የቅባት አይነቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ፤ ይህም የቅባት እህሎች እና እንደ አቮካዶ ያሉ የአትክልት ተዋፅዖ ቅባቶች ናቸው።
4ኛ. በተቻለ መጠን ጤናማ ዘይቶችን መምረጥ ፤ እነዚህም የሰሊጥ ፣ የለውዝ ፣ የአቮካዶ እና የወይራ ዘይቶች የመሳሰሉት ናቸው።
5ኛ. በተፈጥሮ የሚገኙም ቢሆኑ ጤናማ ያልሆኑ ቅባቶችን ማስወገድ ፤ ማለትም ከስጋ ላይ ጮማን እንዲሁም ከዶሮ ላይ ቆዳን ማስወገድ ጠቃሚ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በ 0903832121 ይደውሉ።
ኑትሪዮጵያ!
2 years ago | [YT] | 1
View 0 replies
Load more