እንኳን ወደ ቀናንሞስ ሚዲያ በሰላም መጣችሁ በዚህ ቻናል የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ የቪድዮ ትምህርቶች፣ መዝሙሮች፣ እና ወቅታዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መረጃዎች፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት፣ ሥርዓት፣ ትውፊትና ታሪክ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን የሚቀርብበት ዩትዩብ ቻናል ነው።
👉በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣በዋትሳፕ፣ እንድሁም የፅሁፍ መልዕክት በ0927275152 እንቀበላለን።
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።
27 minutes ago | [YT] | 4
View 0 replies
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
የአእላፋትን ዝማሬ እንዴት እንተቸው?
የቢሆንና ትቸት ምልከታየ ነው ።ያላየሁትን ጨምሩበት
ከስሙ ብንነሳ እንኳን ዝማሬ የተገለጠው በአእላፋት አገልግሎት መሆኑን ያሳየናል ።የመጀመሪያወቹ አእላፋትም አመስግነው የማይደክሙ የሰማይ መላእክት ሲሆኑ ዝማሬም ጥንተ ሀገሩ ሰማይ ነው። የልደት ዕለት ደግሞ አእላፋት መላእክት ከሰው ልጆች ጋራ በጋራ ዘምረዋል። በብርሀን ተጥለቅለቀው በቤተልሔም በጋራ አመስግነዋል።
ባለፈው ዓመት በቦሌ መድኃኔዓለም የተመለከትነው የአእላፋትዝማሬም በጋራ መዘመርን በኅብረት ማመስገንን መሠረት ያደረገ መሰባሰብን የፈጠረ ድንቅ ተስፋ ያለው የዐውደምሕረት ጅማሬ ነው። መስቀል አደባባይ የሚሉም አሉ። እርሱ ግን በልደት ዋዜማ አይመችም።
የአእላፋት ዝማሬ አሠራሩን ማስፋት ያለበት ድንቅ ጅማሬ እንጅ በአጭሩ እንዲጨናገፍ የምንፈልገው መሆን የለበትም። በኔ እይታ መርሓግብሩ በውሱን ቦታና በውሱን ማኅበራት ሳይታጠር ሁሉምን ያሳተፈ የጋራ ዝግጅት ታክሎበት ሀገር አቀፍ የአእላፋት ዝማሬ ተጧጡፎ ከዚህ በላይ ሰፍቶ ማየት ትክክለኛ ትውልዱንና ቤተክርስቲያንን የማሥተሳሰር አንድ እርምጃ ነው።
ብዙዎቹ ወጣቶች የልደት ዋዜማን የሚያሳልፉት በአልባሌ ቦታዎች በኮንሰርት ዝግጅች በከፍተኛ መጠጥና በጭፈራ ቤት እንደነበር በዓላት በመጡ ቁጥር በየሚዲያው የሚሠራጩ ማስታወቂያዎች ራሳቸው ምሥክሮቻችን ናቸው።
መቸም መጠጥ ቤቶችና የጨፈራ ቦታቦች የልደት ኮንሰርት ሲያዘጋጁ የእስልማና (የፕሮቴስታንት)ወጣቶችን ታሳቢ በማድረግ አልነበረም።
አብዛኛው የነዚህ አስረሽ ምችው አድማቂ ወጣቶች እኛ የረሳናቸው በአግባቡ ያልሰበሰብናቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ናቸውና።
የዛሬ ዓመት ከበዓል ማግሥት ያገኘሁት አንድ የራይድ ሹፌር የነገረኝን አስተማሪ ገጠመኝ ላካፍላችሁ።
አገልጋይ መሆኔን ነገሬው ጥቂት ከተነጋገርን በኋላ የአእላፋት ዝማሬ ሒደው ነበር በማለት ጠየቀኝ። እኔ አልሔድኩም አንትስ ? ሹፌሩ እንዲህ አለኝ ።አባዬ እኛማ ጉድ ሆንልዎት ከጋደኞቸ ጋራ እየጠጣን ነበር የምናመሸሸው ስለአእላፋት ዝማሬ ስንሰማ ከመዝሙሩ ተመልሰን እንጠጣለን ተባብለን ወደቦሌ መድኃኔዓለም ብናቀና በዚያው ሳንመለስ አደርን
ጓደኞቸም ሰዓቱ ስለሔደ መጠጥ ቤት ከዚህ በኋላ አንሔድም አሉኝ። ድሮ ባለቤቴ ስትደውል ሠክሬ ነበር ስልክ የማነሳላት በዚያ ሌሊት ቤተክርስቲያን መሆኔን ስነግራት ግን ማመን አቃታት።
የልደት ዕለትም ለመጀመሪያ ጊዜ ሳንጣላ በደስታ አከበርን በማለት የመለወጥ ጅማሬውን አካፈልኝ።
የአእላፋት ዝማሬ ለካስ የምእመናን መያዣ መረብ መሆን ጀምሯል ።በመጠጥ በጭፈራ በሱስ በጥርጣሬ የተያዙትን ከተከማቹበት የመጥፋት ባሕር እየመዘዘ የሚያጠምዳቸው ሁኗል ።በማለት ውስጤ በጣም ተደሰተ።
በእውነት የአእላፋት ዝማሬን ማቃናት ማድነቅና ማረም እንጅ ማክስምን የሚያስከትል ትችት መሰንዘር እንደማይገባን ተገነዘብኩ። የገዳማትን ጉዞ ያስቀርብናል የሚል ስጋት ያደረባቸው ቀናዎችም ትችቱን ተጋርተውት ተመልክቻለው።
በኔ ምልከታ ግን እንኳን የላሊበላን ጉዞ ሊያሰናክል ይቅርና የአእላፋት ዝማሬ የጉዞ አገልግሎት የሚያጠናክር በሕግ የታቀፈ አስተባባሪ ቢኖርና መርሓ ግብሩ ሀገር አቀፍ ቢሆን ይሔ የተሰበሰበ ወጣትም ዓቅሙ የፈቀደለት ሁሉየሚሳተፍበት የጉዞ አገልግሎትን እያሰፋ ይሔዳል እንጅ እየታረመ እየተገመገመ የሚዘረጋ መስመር ከተፈጠረለት በፍጹም መሰናክል የሚሆንበት አጋጣሚ አይታየኝም።
ወጣቱ ከሰዓታት ዝማሬ ባለፈ ሥጋውን ደሙን መቀበል እንዲችል ማድረግና ከበዓላት ዝግጅት ወደሕይወት ዝግጅት ማሸጋገር ደግሞ ከመርሓ ግብሩ አዘጋጆች የሚጠበቅ ከባድ የቤት ሥራ ቢሆንም።ለጊዜውም ከሐጢአት ጎዳና ነጥቆ ይኽን ሁሉ ወጣት እውነተኛ ቤቱ ውስጥ መደበቅ በራሱ እጅግ የሚደነቅ ደግሞም የሚወደድ ዋጋም የሚያሰጥ አገልግሎት ነው።
ነገርግን
ጎልተው መታረም ይኖርባቸዋል ብየ የማስባቸውንው ለመግለጽ
1በየቦታው የሚታረዱ የሚሳደዱ ክርስቲያኖችን በጸሎት በማሰብና ጠንካራ የአንድነትና የትብብር ጥሪ ማበድረግ መጠናቀቅ መቻል አለበት እንጅ የሠርገኛ ስብስብ ብቻ መምሰል የለበትም ብ
2ዓውደምሕረቱን ወደቲያትርነት እየለወጥነው እስኪመስል ድረስ በዓለማዊ ሥራቸው አንቱ የተባሉ ግለሰቦችን የነፍስ አርዓያ አስመስለን ከምእመንነት ያለፈ ማስታወቂያ ለንስሓ የማያበቃ ተአብዮን የሚያስከትል ገጽታ ግምባታ ማድረግ ጉዳቱ ስለሚከፋ መስተካከል ይኖርበታል።
3ዝማሬው የመላዋ ቤተክርስቲያን ሁኖ ሳለ በማኅበር ብቻ የታጠረ የባለቤትነት እንቅስቃሴ ስክነትና ግራቀኝ ምልከታ የሚያስፈልገው መሆኑን ማስገንዘብ ያስፈልጋል።
4የሚመረጡ የዓውደምሕረት መዝሙራት በመጠኑ የተሻሉ የዜማና የግጥም ሥርዓት ያላቸው እንዲሆኑና ሁሉን ለማስደሰት በማሰብ ቤተክርስቲያንን እንዳንጎዳ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
5ሌሎች ወንድሞችና እህቶች ያነሷቸውን በጎ እርማቾች በመቀበል የሚስተካከሉ ነገሮችን ሁሉ በቀናነት በማስተካከል ቤተክርስቲያንን ማዕከል ያደረገ ቋሚ የመሰባሰቢያ መንገድ እንዲሆን የድርሻችን ማገዝ ይኖርብናል።
6የወጣቶቹን በመንፈሳዊ ስሜት መሰባሰብና በተስፋ መገኘታቸውን ተጠቅሞ ሌሎችን ለማጥቃት የሚደረጉ የሐሳብ የቃልና የተግባር እንቅስቃሴዎች ተፈጥረው ሌላ የመከፋፈል አደጋ እንዳያስከትሉ መጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን ተባብሮ መሥራት ሐሳብን ማጋራት የጋራ ማድረግ በዕጅጉ ያስፈልጋል።
ከዚህ በተረፈ ለቤተክርስቲያናችን ከልክ በላይ ዋጋ እየከፈልን ስለዶግማ ለቀኖናዋና ለሥርዓቷና ከልብ እየተቆረቆርን ነገር ግን ሁሉንም በመርገም ሁሉን በመተቸት የምንጠመድ ከሆነ የቤክርስቲያኗን በጎ መዓዛ ማራኪ ማንነት እየሸፈንን ምሬትን ብቻ እያስተማርን ትውልዱ ከሩቅ ተስፋ ቆርጦ እንዲቀር እያደረግን ከሆነ የነገ ጸጸት እንዳይሆንበት ማበርታት ማገዝ ማረም መመረቅን ጎን ለጎን ማስኬት ይኖርብናል።
ቸሩ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን ከፈተና ሕዝቡን ከመከራ ይጠብቅልን አሜን።
2 days ago | [YT] | 39
View 0 replies
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።
5 days ago | [YT] | 96
View 2 replies
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ለቅዳሴ ቤቷ አደረሳችሁ።
6 days ago | [YT] | 102
View 3 replies
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ።
6 days ago | [YT] | 25
View 0 replies
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
ታኅሣሥ 3
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው፣ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፣ የጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስ ዕረፍታቸው ነው።
በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም
ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው ። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና።
እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች ። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ ።
ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ።
ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም በመኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲፈጸምላት እርሷ ለእግዚአብሔር የተሰጠች የስዕለት ልጅ ናትና ለሚጠብቃት ይሰጧት ዘንድ ካህናት እርስበርሳቸው ተማከሩ በሴቶች ላይ የሚደርስ በርሷ ላይም ይደርስባታል ብለው ስለፈሩ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይተዋት ዘንድ ለእርሱ ትክክል መስሎ አልታያቸውም ስለዚህም ሊጠብቃት ለሚገባው በእርሷ ላይ እጮኛ ሊአኖሩ ወደዱ።
ከዚህም አስቀድሞ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልጄ ማርያም ሆይ አንቺ እንዳደግሽና ለአካለ መጠን እንደደረስሽ ዕወቂ ልትታጪ ትወጃለሽን እግዚአብሔርን የሚፈራ መልካም የሆነ የተባረከ ጐልማሳ እንፈልግልሽን ወይም በሕይወትሽ ዘመን ሁሉ በቤተ መቅደስ ተቀምጠሽ እግዚአብሔርን ልታገለግዪው የምትሺ ከሆነ በሴቶች ላይ የሚደርሰው በሚደርስብሽ ወራት ወደ ቤተ መቅደስ ደጅ ከመግባት ትጠበቂ ዘንድ በኦሪቱ የተጸፈውን የርግማን ሥርዓት በአንቺ ላይ እንሠራለን አላት ።
ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋዩ በፊታችሁ ነኝ አባትና እናት የሉኝም ስሙ ቡሩክ ምስጉን ከሆነ ከእግዚአብሔር በታች በእናትና አባት ፈንታ እናንት ናችሁና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደምታውቁ አድርጉ ብላ መለሰች።
ካህናቱና ማኅበሩም ሁሉ ዘካርያስን ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ ስለዚች ብላቴና ማርያም ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት ዘካርያስም ገብቶ ሲጸልይ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ ወጥተህ ከዳዊት ወገን ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሁሉ ወንዶች ሰብስብ የየአንዳንዱንም በትር ከስሙ ጋር ውሰድ ወደ ቤተ መቅደስም በምሽት አግብተህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይበት በነጋ ጊዜም በትሮቻቸውን አውጣ እግዚአብሔርም በበትሩ ላይ ምልክት ለገለጠልህ ለዚያ ሰው ማርያምን ተቀብሎ ሊጠብቃት ይገባዋል።
ካህኑ ዘካርያስም ወጥቶ አንድነት ለተሰበሰቡት ሕዝብ የእግዚአብሔር መልአክ የነገረውን ነገራቸው በዚያንም ጊዜ ከዳዊት ወገን ጐልማሳም ቢሆን ሽማግሌም ቢሆን ሚስቱ የሞተችበት ሁሉ በኢየሩሳሌም ወደአለ ቤተ መቅደስ ይሒድ እያሉ ዓዋጅን ዙረው የሚናገሩ በእስራኤል አገር ሁሉ ላከ ።
ከዳዊት ወገን የሆነ ጠራቢው ዮሴፍም በሰማ ጊዜ በትሩን ይዞ ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ካህኑ ዘካርያስም የሁሉንም በትሮች ተቀብሎ ስማቸውን በላያቸው ጻፈ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሆነ ዘካርያስም በትሮችን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ውጭ ቁመው ይጸልዩ ነበር ዘካርያስም ጸሎቱን በፈፀመ ጊዜ ለየአንዳንዱ በትራቸውን አውጥቶ ሰጠ ጠራቢው ዮሴፍም በትሩን ሊቀበል በቀረበ ጊዜ ከእርሷ ነጭ ርግብ የመሰለች ተገለጠች እየበረረችም ሒዳ በጠራቢው ዮሴፍ ራስ ላይ ተቀመጠች ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ አይተው እጅግ አደነቁ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
ዘካርያስም ዮሴፍን ዮሴፍ ሆይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እንደ ተናገረ ድንግል ማርያምን ወደ ቤትህ ወስደህ ጠብቃት አለው ዮሴፍም ቅድስት ድንግል ማርያምን ከካህናት እጅ ተቀበላት በእርሱም ዘንድ ኖረች ። ከዚህም በኋላ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ስለ እግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ሁኖ ስለመወለዱ በዮሴፍ ቤት አበሠራት።
ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሼር አድርጉ
1 week ago | [YT] | 95
View 0 replies
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ኤልያስ_ርዕሰ_ነቢያት
በዚህችም በታኅሣሥ አንድ ቀን በእስራኤል ፊት ነቢይ ኤልያስ የተገለጠበት ነው። ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ ቶና ነው።
ስለርሱም እንዲህ ተነገረ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው እነርሱም ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን፣ በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን፣ ወይም እስራኤልን በሰይፍና በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን ተባባሉ።
በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ ነገሥት ተጽፎአል ። ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል።
በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ ዮሐንስ ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግሮአል። ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ በ #እግዚአብሔር ፊት የሚያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው አለ።
ከጠላቶቻቸውም ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸዋለች የሚጠሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ። ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ በሰማይ ላይ ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል።
ምስክርነታቸውንና ትንቢታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከባህር የወጣው አውሬ ከእሳቸው ጋር ይጣላል ድል ነስቶም ይገድላቸዋል ። አስከሬናቸውንም ፍጥሞ በምትባል በታላቂቱ አገር ያስጥለዋል ይችውም በምሥጢር ሰዶም ግብጽ የተባለች ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።
አስከሬናቸውንም ሕዝብና አሕዛብ በሀገርም ያሉ ነገዶች ሦስት ቀን ተኩል ያዩታል አስከሬናቸውንም በመቃብር ይቀብሩት ዘንድ አያሰናብቱም። በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ሞት ደስ ይላቸዋል እርስበርሳቸውም በደስታ እጅ መንሻ ይሰጣጣሉ እሊህ ሁለቱ ነቢያት በምድር በሚኖሩ ሰዎች መከራ አጽንተውባቸዋልና ይላሉ።
ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከ #እግዚአብሔር ዘንድ የሕይወት መንፈስ መጥታ ታድርባቸዋለች ተነሥተውም በእግራቸው ይቆማሉ በሚያዩዋቸው ላይም ጽኑ ፍርሀት ይሆናል።
ከወደ ሰማይ ቃል መጥቶ ወደዚህ ውጡ ይላቸዋል ከዚህ በኋላ ጠላቶቻቸው እያዩአቸው በደመና ያርጋሉ። በዚያችም ሰዓት ጽኑ መነዋወጥ ይሆናል የዚያችም አገር ዐሥረኛ እጅዋ ይጠፋል በዚያም መነዋወጥ ሰባት ሽህ ሰዎች ይሞታሉ የቀሩት ግን ደንግጠው የሰማይ አምላክን ፈጽመው ያመሰግናሉ።
ለ #እግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ነብይ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
1 week ago | [YT] | 53
View 1 reply
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ እና አማላጅነቱ አይለየን‼️
1 week ago | [YT] | 104
View 2 replies
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
ቸሩ መድኃኔዓለም በዕለተ ቀኑ ከጭንቀት እና ከመከራ ያውጣችሁ።
2 weeks ago | [YT] | 108
View 2 replies
ቀናንሞስ ሚዲያ - Qenanmos Media
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አቡነ_ኢየሱስ_ሞዓ_ዘሐይቅ
ኅዳር ሃያ ስድስት በዚህች ዕለት አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ዘሐይቅ እረፍታቸው ነው። በጐንደር ክፍለ ሀገር ስማዳ ወረዳ ዳህና ሚካኤል በተባለው ቦታ ከአባታቸው ከዘክርስቶስና ከእናታቸው ከእግዚእ ክብራ በ1210 ዓ.ም ተወለዱ። ዕድሜያቸው 3ዐ ዓመት እስከሚደርስ ከቤተሰቦቻቸው ትምህርተ ሃይማኖትንና ግብረ ገብን ሲማሩ ከቆዩ በኋላ በ124ዐ ዓ.ም ይኼንን ዓለም በመተው ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ገቡ። በደብረ ዳሞ ገዳም መነኰሳቱን እየረዱ፣ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን እያጠኑ፣ ትምህርተ ቅዱሳት መጻሕፍትን እየገለበጡ ለሰባት ዓመታት ከቆዩ በኋላ የደብረ ዳሞ 3ኛ አበ ምኔት ከሆኑት ከአባ ዮሐኒ ምንኩስናን ተቀበሉ (1247 ዓ.ም.)።
አንድ ቀን ሌሊት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደርሳቸው መጥቶ (ገድልህና ትሩፋትህ በዓለም ሕዝብ ሁሉ ትተህ የስምህ መክበርያ ወደሆነው ሐይቅ ወደ ተባለው ሥፍራ ሂድ) አላቸው። አባታችን "ቦታውን እንዴት ዐውቀዋለሁ" በማለት ቢጠይቁት "ተነሥ። ጉዞህን ጀምር ቦታውን እኔ አሳይሃለሁ" አላቸው። አባ ኢየሱስ ሞዓ በመልአኩ እንደታዘዙት ከበአታቸው ተነሥተው ተከተሉት። የብዙ ወራት መንገድ የሆነው ጐዳናም በስድስት ሰዓት አለቀላቸው።
በዚያን ወቅት ከሐይቅ ገዳም በስተ ሰሜን ወደነበረው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ደረሱ። ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከመግባታቸውም በፊት ለ6 ወራት ያህል በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አገልግለዋል። ያገለግሉበት በነበረው ቤተ ክርስቲያን ቀን ቀን ሕዝቡን ሲያስተምሩ በመዋል ሲመሽ ወደ ሐይቁ በመግባት ሲጸልዩ ያድሩ ነበር። በሐይቅ እስጢፋኖስና በዙርያው ለነበሩ አበውም ማታ ማታ አንድ ብርሃን ወደ ሐይቁ ሲገባ ጠዋት ጠዋትም ሲወጣ ይታያቸው እንደነበር ዛሬ በገዳማቸው የሚገኘው ገድለ ኢየሱስ ሞዓ ያስረዳል።
በመጨረሻም በገዳሙ አባቶች ልመናና በልዑል #እግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ ሐይቅ ገዳም ገብተው አበምኔት ሆኑ። ሐይቅ እስጢፋኖስ ማለት ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሲሆን የመሰረቱት ካልዕ ሰላማ የተባሉ ግብጻዊ ጻድቅ ናቸው፤ ገዳሙን ከሰሩ በኃላ የማንን ታቦት እናስገባ ብለው ሲያስቡ ቶራ የምትባል እንስሳ ጭነት ተጭና ከመካከላቸው ተገኘች፤ ጭነቱን አውርደው ቢያዩት በሐር ጨርቅ የተጠቀለለ ሁለት ታቦት አገኙ አንዱ የቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ የቅዱስ ጊዮርጊስ " ይህንን ታቦት በእየሩሳሌም የሚኖሩ የተሰወሩ ቅዱሳን ከ #እግዚያብሔር ታዘው የላኩት ነው" የሚል ጽሑፍም አገኙ ይላል። ይህ ከሆነ ከ 400 ዘመን በኃላ ነው አባ እየሱስ ሞኣ ወደዚህ ቦታ የመጡት ለ 52 ዓመት ቀን ቀን መንፈሳዊ ስራቸውን ይሰራሉ ሌሊት ሌሊት ሐይቁ ውስጥ ቆመው ሲጸልዩ ያድራሉ።
አባ ኢየሱስ ሞዓ በሐይቅ እስጢፋኖስ በአበምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ከየገዳማቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በመገልበጥና በማስገልበጥ ብሎም በማሰባሰብ የመጀመርያው ዘመናዊ የቤተ ክርስቲያን ቤተ መጻሕፍት በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም እንዲቋቋም አድርገዋል። በዚሁ ገዳም ውስጥም የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ቋሚ ትምህርት ቤት በማቋቋም 8ዐዐ መነኮሳትን በትምህርተ ሃይማኖት አሠልጥነው በንቡረ ዕድነት ማዕረግ በመላ ሀገሪቱ እንዲሠማሩ አድርገዋቸዋል።
ከተማሪዎቻቸውም መካከል አቡነ ተክለ ሃይማኖት (ዘደብረ ሊባኖስ)፣ አባ ተክለሃይማኖት ያመነኮሱ አባት ናቸው። አባ ኂሩተ አምላክ (ዘጣና ሐይቅ)፣ አባ ጊዮርጊስ (ዘጋሥጫ)፣ አባ ዘኢየሱስ፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ አባ አሮን (ዘደብረ ዳሬት) ጥቂቶች ናቸው። አፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት ያነፁት እርሳቸው ናቸው።
እንደዚህ ነው የመነኮሳት አባት እንጦንስ ነው እንጦንስ መቃርስን ወለደ መቃርስ ጳኩሚስን ጳኩሚስ አቡነ አረጋዊን አቡነ አረጋዊ አባ ዮሐኒን አባ ዮሐኒ የሐይቁን አባ እየሱስ ሞአን ወለዱ አባ ኢየሱስ ሞዓ ደግሞ ተክለሃይማኖትን ወለዱ።
በዮዲት ጉዲት ተጐድታ የነበረችው ሀገራችን ዳግም የወንጌሉ ብርሃን እንዲበራባት ሊቃውንት እንዲይነጥፉባት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዳይቆነጻጸሉ፣ መነኮሳት አባቶች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወርደው ገዳማትን እንዲያስፋፉ ያደረጉት አባ ኢየሱስ ሞዓ ናቸው። በተለይም የሐይቅ እስጢፋኖስ ያፈራቸው 8ዐዐ ሊቃውንት በመላዋ ሀገሪቱ በመሠማራታቸው ዛሬ የምናያቸውን አብዛኞቹን ገዳማትና ቅዱሳት መጻሕፍት አቆይተውናል።
አባታችን አባ ኢየሱስ ሞዓ ለ45 ዓመታት ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከቆዩ በኋላ ኅዳር 26/1292 ዓ.ም በዕለተ እሑድ በ82 ዓመታቸው ዐረፉ። በዚያች ዕለትም በቦታው የታየው ብርሃን ሀገሪቱን መልቷት እንደነበረ ገድላቸው ይመሠክራል።
#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አቡነ_ሀብተ_ማርያም
በዚህችም ቀን የተመሰገነና የከበረ ንጹሕም የሆነ የኢትዮጵያዊ አባታችን የሀብተ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።
የዚህ ቅዱስ አባት የትውልድ አገሩ የራውዕይ በምትባል በስተ ምሥራቅ ባለች ሀገር ውስጥ ነው በዚያም ስሙ ፍሬ ቡሩክ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ይህም ክቡራንና ታላላቅ ከሚባሉት ከዚች አገር ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነው ። እጅግም ሀብታም ነበር ብዙ ንብረትም አለው በሕጋዊ ጋብቻም ስሟ ዮስቴና የምትባል ብላቴና ድንግልን አገባ ይቺም የተመረጠች በበጎ ሥራ የተሸለመችና ያጌጠች ናት።
ነገር ግን አስቀድመን በዚህ ዓለም ከሕግ ባሏ ጋር በንጹሕ ጋብቻ #እግዚአብሔርን በመፍራት ምጽዋትን በመስጠት የዋህነትን ትሕትናን ፍቅርን ትዕግሥትን ገንዘብ አድርጋ በጾም በጸሎት ተወስና እንደኖረች እንነግራችኋለን ። በእንደዚህም ሳለች #ጌታችን በወንጌል ሰው ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ካጠፋ ምን ይጠቅመዋል እንዳለ ላንቺ በዚህ ዓለም መኖር ምን ይረባሽ የሚል ሐሳብ መጣባት ።
ከዚህም በኋላ ወጣች ፈጥናም በሀገርዋ ትይዩ ወደሆነ ምድረ በዳ ደርሳ ወደ መካከሉ ገባች በዚያም በረሀ አራዊት እንጂ ሰው አይኖርበትም በዚያም ደጃፍዋ የተከፈተ ታናሽ ዋሻ አግኝታ ምንም ምን ሳትነጋገር ወደ ውስጧ ገብታ ቆመች የቅዱስ ዳዊትንም መዝሙር የሚጸልይ ሰው አይታ ደነገጠች።
እርሱም ባያት ጊዜ ፍርሀትና መንቀጥቀጥ በላዩ ወረደበት በ #መስቀል ምልክትም በላይዋ አማትቦ የ #እግዚአብሔርን ስም ጠራ እንዳልሸሸችም አይቶ ሰው መሆንዋን አወቀ በአወቀም ጊዜ እንዲህ ብሎ ገሠጻት ወደዚህ ምን አመጣሽ ለእኔ እንቅፋት ልትሆኚ ነውን አሁንም ከዚህ ፈጥነሽ ሒጂ አላት ።
እርሷም አባቴ ሆይ አንተ እንዳሰብከው አይደለሁም እኔ ለሕያው #እግዚአብሔር ልጅ ለ #ኢየሱስ_ክርስቶስ አገልጋዩ ነኝ እንጂ በእርሱ ፍቅርና በእናቱ በእመቤቴ በቅድስት ድንግል #ማርያም ፍቅር ያለኝን ሁሉ ትቼ ንቄ ከዓለም ወጥቼ ወደዚህ መጣሁ በዚህ ቦታም ከአራዊት በቀር ሰው እንዳለ አላወቅሁም አሁንም አባቴ ይቅርታ አድርግልኝ ወደ ሌላ ቦታ እሔዳለሁ አለችው ።
2 weeks ago | [YT] | 96
View 1 reply
Load more