ህግና ህግ ነክ ጉዳዮች ፣የፍታብሄርና የወንጀል ጉዳዮች ፣አገራዊ እና አለም አቀፋዊ ህጎች ይዳሰሱበታል ። የህግ ምክሮችና ትንታኔዎች ይሰጥበታል‼
በ facebook ገፃችን መከታተል ለምትፈልጉ___www.facebook.com/TebeqaYusuf/
በ Telegram ቻናላችን መከታተል ለምትፈልጉ____Yusuf Akeberegn Law Office
የሀገራችን የህግ ጉዳይ ይዳሰስበታል! !
t.me/TebeqaYesufAkeberegn
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
መነጋገር እና እርቅ ዋጋ አለው !!
9 months ago | [YT] | 60
View 3 replies
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
ለባለይዞታዎች‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ለ8ኛ ጊዜ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ እና ምዝገባ ስራ ሊያከናውን ነው ‼️
👉የይዞታ ማረጋገጫ ከታህሳስ 10-ሚያዚያ 15 ይከናወናል ብሏል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ግፋ ወሰን ደሲሳ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ኤጀንሲው ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ከጀመረበት 2007 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ 7 ጊዜ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ በማካሄድ በ 337 ቀጠናዎች ላይ የማረጋገጥ ስራ ማከናወኑን ተናግረዋል ፡፡
በዚህ መሰረት በያዝነዉ በጀት አመት ለመጨረሻ ጊዜ ለስምንተኛ ዙር ቀሪ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉትን ያልተረጋገጡ 136 ቀጠናዎች የሚገኙ ቁራሽ መሬቶችን አረጋግጦ ለመመዝገብ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ዛሬ ታህሳስ 10/4/2017 ዓ.ም እወጃ ማካሄዱን ገልፀዋል ፡፡
የይዞታ ማረጋገጡ ስራ በተመረጡ ስድስት ክፍለ ከተሞች ማለትም የካ ክፍለ ከተማ( በወረዳ ወረዳ1፤2፤ 3፤9፤10፤11፤12 በ 25 ቀጠናዎች በለሚ ኩራ በወረዳ 2፣3፤4፤5፤6፤9፤10፣ 13 እና 14 በ 44 ቀጠናዎች፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣3፣4፤6፣ 9፣13 በ 19 ቀጠናዎች ንፋስ ስልክ ላፍቶ በወረዳ 6 ፣7፣8፤9፤10፣11፣14 የሚገኙ በ 22 ቀጠናዎች ቦሌ በ ወረዳ 11፡12፤13 በ 15 ቀጠናዎች ኮልፌ ቀራኒዮ በወረዳ 3፤11 በ 11 ቀጠናዎች አጠቃላይ በ 136 ቀጠናዎች (በ 467 ሰፈሮች) ያልተረጋገጡ ይዞታዎችን የማረጋገጡ ስራ በስልታዊ ዘዴ / በመደዳ / የማረጋገጥ ስራ የሚከናወን ሲሆን ስራውም ከ ታህሳስ 10/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ወራት ውስጥ እስከ ሚያዝያ 15 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ሙሉ ወጪውም በመንግስት እንደሚሸፈን ተናግረዋል፡፡
ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዋስትናና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ባለይዞታዎች ከታህሳስ 20/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስፈላጊውን መረጃ ይዘው የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንድታቀርቡ በድጋሜ አሳስበዋል፡፡
ኤጀንሲው የይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ከጀመረበት 2007 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ 7 ጊዜ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ በማካሄድ በ337 ቀጠናዎች ላይ የማረጋገጥ ሥራ ተካሂዷል፡፡ በዚህም በቁራሽ መሬት 219 ሺ 722፣ በጋራ መኖሪያ ቤት 173 ሺ 136 በመብት 400 ሺ 84 ይዞታዎች ላይ የይዞታ ማረጋገጥ ሥራ በመስራት የአዲስ አበባን ከጠቅላላው የቆዳ ስፋት 54% መሸፈኑ ይታወቃል፡፡
11 months ago | [YT] | 76
View 11 replies
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
★ ነገ አሃዱ ኤፍ ኤም ላይ ታገኙኛላችሁ ★
*****************************
ነገ ሚያዚያ 17. ከረፋዱ 5_6 ሰዓት በአሐዱ ኤፍ ኤፍ 94•3 ላይ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በቲክቶክ ለተቸገሩ ሰዎች በሚል የተሰበሰበ ገንዘብን ለግል ጥቅም ማዋልና ማታላል እንዲሁም ሰውን እየደበደቡ ቀርፆ መልቀቅ ላይ በህግ ያለውን ተጠያቂነት በተመለከተ ቆይታ አደርጋለሁ፣ እንድትከታተሉ እጋብዛለሁ‼
1 year ago | [YT] | 97
View 9 replies
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
★*★ በማህበራዊ ሚዲያ በ Youtube, በ telegram,በ Tiktok, በ facebook, በ Instgram በፍትህ ዘርፍ ለኢትዮጵያዊያን አስተዋፅኦ ካደረጉ ግለሰቦች ተመራጭ ተወዳዳሪ ሆኛለሁ‼ በመሆኑም ከዚህ በታች ባስቀመጥኩት የቴሌግራም ቻናሌ ገብታችሁ በምታገኙት bot መሰረት ልትመርጡኝ ትችላላችሁ ‼ አመሰግናለሁ ‼ t.me/TebeqaYesufAkeberegn
1 year ago | [YT] | 510
View 26 replies
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
*★★ የአክሲዮን ማህበር የሚፈርስባቸው ምክንያቶች *★★
***********************************
በጠበቃ ዩሱፍ አከበረኝ
የአክሲዮን ማህበር የፈርስባቸው ምክንያቶች በአዲሱ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 473 ስር በዝርዝር ተደንግጎ ይገኛል። እነዚህም ምክንያቶች _
1ኛ/ የአክሲዮን ማህበሩ አባላት ቁጥር በህግ ከተፈቀደው ዝቅ ሲልና በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሌላ አባል መተካት ካልተቻለ የንግድ ማህበራትን የሚመዘግበው የመንግስት አካል አክሲዮን ማህበሩ እንዲፈርስ ውሳኔ ይሰጣል። የአክሲዮን ማህበር አባላት ዝቅተኛ ቁጥር ከ 5 ማነስ ስሌለበት ከዚህ ቁጥር ካነሰ ማለት ነው። ነገር ግን የንግድ ማህበራትን መዝጋቢው አካል አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው የ 6 ወር ጊዜውን ሊያራዝመው ይችላል።
2ኛ/ አክሲዮን ማህበሩ የሚያስተዳድሩት የአስተዳደር አካላት ( የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ተቆጣጣሪ ቦርድ፣ስራ አስኪያጅ… ) የሌሉት መሆኑ ሲረጋገጥ ማህበሩ እንዲፈርስ ማህበራትን የሚመዘግበው የመንግስት አካል ውሳኔ ይሰጣል። ማህበሩ የአስተዳደር አካላትን አሟልቶ መቀጠል የሚችል ከሆነ ሊፈቀድለት ይችላል።
3ኛ/ አክሲዮን ማህበሩ ሲከስርና በዚህ ኪሳራውም የማህበሩን ዋና ገንዘብ 3/4ኛ ሲያጣ። ይህ በሚሆንበት ጊዜም የዳይሬክተሮች ቦርድ የማህበሩን መፍረስ ወይም መቀጠል የሚወስን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት አለበት። ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት ካልቻለ ጥቅም ባለው ሰው በፍርድ ቤት በሚቀርብ ክስ ማህበሩ በፍርድ ቤት ውሳኔ ይፈርሳል።
1 year ago | [YT] | 80
View 1 reply
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
🔥⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ሰላም ጤና ይስጥልኝ የማከበራችሁ የቻናሌ ቤተሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ በፍትህ ዘርፍ ለህዝብ አስተዋፅኦ ካደረጉ መካከል ተወዳዳሪ እንድሆን ታጭቻለሁ ፣ በመሆኑም በዚህ ሊንክ ባለው bot ገብታችሁ ከተዘረዘሩት ውስጥ በፍትህ ዘርፍ በሚለው ስር እኔን በመምረጥ፣የእኔን ስም " አቶ ዩሱፍ አከበረኝ ዘይኑ " ብለው በመፃፍ ይምረጡኝ እና የእኔ ቤተሰብ መሆንዎን በተግባር ያስመስክሩ።
የመምረጫ bot በዚህ የቴሌግራም ቻናሌ አለ ይህንን ሊንክ ይንኩትt.me/TebeqaYesufAkeberegn
1 year ago | [YT] | 40
View 15 replies
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
ሰላም ጤና ይስጥልኝ የማከበራችሁ የቻናሌ ቤተሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ በፍትህ ዘርፍ ለህዝብ አስተዋፅኦ ካደረጉ መካከል ተወዳዳሪ እንድሆን ታጭቻለሁ ፣ በመሆኑም ከታች ባለው ሊንክ ቴሌግራም ቻናሌ ውስጥ የምታገኙትን የምርጫ bot ጠቅ በማድረግ ከተዘረዘሩት ውስጥ " በፍትህ ዘርፍ" በሚለው ዘርፍ ስር እኔን በመምረጥ፣የእኔን ስም " አቶ ዩሱፍ አከበረኝ ዘይኑ " ብለው በመፃፍ ይምረጡኝ ፣ የእኔ ቤተሰብ መሆንዎን በተግባር ያስመስክሩ። የቴሌግራም ቻናሌ ይህ ነው t.me/TebeqaYesufAkeberegn
1 year ago (edited) | [YT] | 599
View 76 replies
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ኮርፖሬሽን አውጥቶት የነበረው የመኖሪያ ቤት እና የንግድ ቤት ጨረታ አሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆኖል !! በዚህ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ ስለምታገኙት ማየት ትችላላችሁ !! t.me/TebeqaYesufAkeberegn
1 year ago | [YT] | 26
View 1 reply
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በዋና መስሪያ ቤቱ መግለጫ ይሰጣል ‼
1 year ago | [YT] | 69
View 2 replies
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
0ረብ ሃገር ያላችሁ ወገኖች !
~
1- ቤተሰቦቻችሁን እርዱ። መሆንም ያለበት ነው። ግን ድጋፋችሁ የሚጠቀሙበት እንጂ የሚጎዱበት እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ለአጉል ሱሶች የሚጠፋ አይሁን።
2- ራሳችሁን አትርሱ። ተቀማጭ ይኑራችሁ። ዛሬ ሰው ተጨካክኗል። እድሜ ልካችሁን ስትልኩ ኖራችሁ በህመም የወደቃችሁ እለት የሚያነሳችሁ እንኳ ላይኖር ይችላል።
3- ብድር ስትሰጡ በሚገባ ተዋዋሉ። መካካድ በዝቷል። አማና የምታስቀምጡበትንም ለዩ።
4- በማይረቡ ሰበቦች የሚወጡ ወጭዎችን ቀንሱ።
5- ጥሩ ክፍያ አላገኘንም እያላችሁ ለወራት ያለ ስራ አትቀመጡ።
6- "አገባሻለሁ" ለሚሉ ጩልሌዎች የዘመናት ጥሪታችሁን አሟጣችሁ አትስጡ። ለትዳር ሲባል ገንዘብ መውጣቱ ችግር የለውም። ገንዘባችሁን እንጂ እናንተን በማይፈልጉ ሰዎች አትሸወዱ ።
1 year ago | [YT] | 45
View 11 replies
Load more