ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
0ረብ ሃገር ያላችሁ ወገኖች !~1- ቤተሰቦቻችሁን እርዱ። መሆንም ያለበት ነው። ግን ድጋፋችሁ የሚጠቀሙበት እንጂ የሚጎዱበት እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ለአጉል ሱሶች የሚጠፋ አይሁን።2- ራሳችሁን አትርሱ። ተቀማጭ ይኑራችሁ። ዛሬ ሰው ተጨካክኗል። እድሜ ልካችሁን ስትልኩ ኖራችሁ በህመም የወደቃችሁ እለት የሚያነሳችሁ እንኳ ላይኖር ይችላል።3- ብድር ስትሰጡ በሚገባ ተዋዋሉ። መካካድ በዝቷል። አማና የምታስቀምጡበትንም ለዩ። 4- በማይረቡ ሰበቦች የሚወጡ ወጭዎችን ቀንሱ።5- ጥሩ ክፍያ አላገኘንም እያላችሁ ለወራት ያለ ስራ አትቀመጡ።6- "አገባሻለሁ" ለሚሉ ጩልሌዎች የዘመናት ጥሪታችሁን አሟጣችሁ አትስጡ። ለትዳር ሲባል ገንዘብ መውጣቱ ችግር የለውም። ገንዘባችሁን እንጂ እናንተን በማይፈልጉ ሰዎች አትሸወዱ ።
1 year ago | [YT] | 45
ጠበቃ ዩሱፍ // Lawyer Yusuf
0ረብ ሃገር ያላችሁ ወገኖች !
~
1- ቤተሰቦቻችሁን እርዱ። መሆንም ያለበት ነው። ግን ድጋፋችሁ የሚጠቀሙበት እንጂ የሚጎዱበት እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ለአጉል ሱሶች የሚጠፋ አይሁን።
2- ራሳችሁን አትርሱ። ተቀማጭ ይኑራችሁ። ዛሬ ሰው ተጨካክኗል። እድሜ ልካችሁን ስትልኩ ኖራችሁ በህመም የወደቃችሁ እለት የሚያነሳችሁ እንኳ ላይኖር ይችላል።
3- ብድር ስትሰጡ በሚገባ ተዋዋሉ። መካካድ በዝቷል። አማና የምታስቀምጡበትንም ለዩ።
4- በማይረቡ ሰበቦች የሚወጡ ወጭዎችን ቀንሱ።
5- ጥሩ ክፍያ አላገኘንም እያላችሁ ለወራት ያለ ስራ አትቀመጡ።
6- "አገባሻለሁ" ለሚሉ ጩልሌዎች የዘመናት ጥሪታችሁን አሟጣችሁ አትስጡ። ለትዳር ሲባል ገንዘብ መውጣቱ ችግር የለውም። ገንዘባችሁን እንጂ እናንተን በማይፈልጉ ሰዎች አትሸወዱ ።
1 year ago | [YT] | 45