በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ይህ ማህበር 'ማህበረ ኪዳነ ምህረት' መሰረቱን በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረገ ሲሆን አላማውም:
1 ግልጽ እና ተዓማኒነት ያለው የቤተክርስትያን አገልግሎት ፤
2 በአጓጉል ምክንያት ከቤተክርስቲያን መባንና አስራትን ለማያስገቡ ምዕመናን ተጨባጭ መረጃዎችን በማቅረብ እና ሁሉም የማህበሩ አባላት ሊያጣሩ በሚችሉበት አሰራር የጠፉትን ወደ ቤተክርስቲያናችን ስርዐት መመለስ፤
3 በ3 የማይተዋወቁ ነገር ግን በትልቅ ጥንቃቄ በተመረጡ ክርስቲያኖች ስም በተከፈተ የባንክ ቁጥር ሚስጥራዊነቱ እንዲሁም ግልፀኝነቱ በተጠበቀ ሁኔታ አስራት በኩራትን መሰብሰብ፤
4 በተሰበሰበው መባ በአመት 1፣2 ወይም3 ጊዜ እንደ አቅማችን የሚወሰን ሲሆን የተረሱ፣ አስታዋሽ ያጡ አብያተ ክርስቲያናትን ማሳደስ እንዲሁም የአብነት ትምህርት እንዲስፋፋ ማገዝ፤
5 አቅማችን ሲጨምር አብያተ ክርስቲያናትን ማነፅ እና ለህብረተሰቡ ማበርከት ናቸው።
አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈፀመን ለልዑል እግዚአብሔር ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ምስጋና ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።