ጽዋዕ Tsewa'e

ጽዋዐ ሕይወት እትሜጦ ወስመ እግዚአብሔር እጼውዕ - የሕይወትን ጽዋ እጠጣለሁ፣ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለሁ፡፡ መዝ ፻፲፭፥፬።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና ኢትዮጵያን የሚመለከቱ የተለያዩ ዝግጅቶችን ይስተናገዳሉ ፡፡ ንጥር መረጃዎች፣ ትንታኔዎች፣ ታሪኮች፣ ፍልስፍናዎች እና ጥበቦች ለትውልዱ በሚመጥን ደረጃ በዓይነት በዓይነታቸው እየተሰናዱ ይቀርባሉ፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና፣ ትውፊት፣ ታሪክ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች በጥልቀት ይዳሰሳሉ፡፡



ጽዋዕ Tsewa'e

የጉራጌ ሕዝብ በተጠና ስልት መብቱን እያስከበረ ነው። ከሰሜን ዐማራ ወደ ዐዲስ አበባ የሚያስገባው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል። ዐዲስ አበባ ላይ ወሰን ማካለል የሚባል ዘመቻ በቅርቡ ይጀመራል። ምን ይበጃል?

3 years ago | [YT] | 41

ጽዋዕ Tsewa'e

ቅዱስነታቸው በዓምታዊ የጾመ ፍልሰታ መቀበያ መልእክታቸው በርካታ ነገሮችን ገላልጠዋል። በተለይም ጠላትን አሳፍረዋል። በዝርዝር እንመለከታቸዋለን።

በኢትዮጵያችን አቆጣጠር ፲፩፡ ፲፭ (11፡15) ሲኾን እንጀምራለን። እያዛመቱ (ሼር እያደረጉ) ይጠብቁን!

3 years ago | [YT] | 66

ጽዋዕ Tsewa'e

ፊደል ይገድላል፡ መንፈስ ግን ሕያው ያደርጋል እንዲል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገጸ ንባብ ብቻ መሳሳት እንዳይኖር የመጽሐፍን ምስጢር በጥንቃቄና በጸሎት መማር ያስፈልጋል። ለምሳሌ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን በወንጌል ለቅዱሳን ሐዋርያቱ እንዲህ ብሏቸው ነበር።

"እኔ ግን ሃይማኖታችሁ እንዳይጠፋ ሰለእናንተ ጸለይሁ" ሉቃ ፳፪፡፪። በዚህ ቃል ብዙዎች ይሰናከሉበታል። አይደለም ቃሉ ራሱ ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስም የማሰናከያ ዓለት ተብሏል። በእኔ የማይሰናከለው ብፁዕ ነው እንዲልም ላለመሰናከል ብቸኛው መንገድ በሃይማኖት መማር ነው።

የቃሉን እውነተኛ ምስጢር ለመረዳት ብቅ ይበሉ። በኢትዮጵያ አቆጣጠር ፲፩ (11፡00) ሠዓት ሲኾን እንጀምራለን።

3 years ago | [YT] | 54

ጽዋዕ Tsewa'e

ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን የተላለፈ ጥሪ!

ነገ በኢትዮጵያሠዓት አቆጣጠር ከቀኑ ፲፩ (11፡00) ሠዓት ላይ በእግዚአብሔር ቸርነት ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

እስከዚያው በማዛመት (share በማድረግ) ይጠብቁ።

3 years ago | [YT] | 93