ጽዋዕ Tsewa'e

ፊደል ይገድላል፡ መንፈስ ግን ሕያው ያደርጋል እንዲል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገጸ ንባብ ብቻ መሳሳት እንዳይኖር የመጽሐፍን ምስጢር በጥንቃቄና በጸሎት መማር ያስፈልጋል። ለምሳሌ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን በወንጌል ለቅዱሳን ሐዋርያቱ እንዲህ ብሏቸው ነበር።

"እኔ ግን ሃይማኖታችሁ እንዳይጠፋ ሰለእናንተ ጸለይሁ" ሉቃ ፳፪፡፪። በዚህ ቃል ብዙዎች ይሰናከሉበታል። አይደለም ቃሉ ራሱ ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስም የማሰናከያ ዓለት ተብሏል። በእኔ የማይሰናከለው ብፁዕ ነው እንዲልም ላለመሰናከል ብቸኛው መንገድ በሃይማኖት መማር ነው።

የቃሉን እውነተኛ ምስጢር ለመረዳት ብቅ ይበሉ። በኢትዮጵያ አቆጣጠር ፲፩ (11፡00) ሠዓት ሲኾን እንጀምራለን።

3 years ago | [YT] | 54