ገብር ኄር ቲዩብ Gebr her Tube

ይህ ገብር ኄር የተሰኘው የዩቲዩብ ገጽ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ሀሳቦችና ትምህርቶች ይለቀቁበታል።
ለአስተያየት በቴሌግራም @Anteyee ላይ መልእክት ይላኩ
#SUBSCRIBE #SHARE #LIKE


ገብር ኄር ቲዩብ Gebr her Tube

እንኳን አደረሳችሁ
https://youtu.be/DLD9coGVeKs

2 months ago (edited) | [YT] | 13

ገብር ኄር ቲዩብ Gebr her Tube

ነገ ማታ ይጠብቁን

3 months ago | [YT] | 11

ገብር ኄር ቲዩብ Gebr her Tube

ቅዳሜ ከሰአት ይጠብቁን

7 months ago | [YT] | 6

ገብር ኄር ቲዩብ Gebr her Tube

እሁድ ከሰአት ይጠብቁን

8 months ago | [YT] | 16

ገብር ኄር ቲዩብ Gebr her Tube

ጉባኤ ቃና
በዓልተ ጥሪት ኮነት ወለተ ዳዊት ሳዊሱ፤
ዘዮም እደው እስመ ጥሪተ የኀሡ።

ሐሊብ ወቅብዕ ወሥጋ ነገስተ ኪራም ወነዌ፤
ግበሩ ስምዕ ዘሀሎ ግበረክሙ መርዓዌ።

ዘአምላኪየ
ለእንተ መርዓት መካህ ዓለመ ምልክዓም አሌ፤
በወርቅ እስመ ወለጣሃ ለነፍሱ ድንጋሌ
ዘከመ አበው ኢይበል በሀልተ አበው ሀሌ።

ዓለማውያን እደው መነኮሳተ አቅልሉ፤
ዘተውሕጠ እስመ ኢተረፈ ወተከስተ ኩሉ፤
ሰብአ ሰብአ ኢይበሎሙ ለእሉ።

ሚ በዝኁ
መትልወ ሰሎሞን ሑር ወእደ ሀሎ መርዓት ዘመደ ሥጋ ምድረ ዐፀባ፤
ለዘመደ ሥጋ መርዓት እስመ በአካል ትረክባ፤
ወለእመ ዘመድ መርዓት ኀሠሥካ ለሊከ ኢይከልአከ አባ።

ዋዜማ
ኢታርኢ መነኮሰ ለወለተ ዳዊት ወላድ ወለተ ዳዊት ሠርዌ፤
መነኮሰ ለእመ ትሬኢ ኢይብልዓ አርዌ
ለወለተ ዳዊት ፈራህ መነኮሰ ዝ ጽማዌ፤
ዳእሙ ለእህት እንተ ነነዌ፤
አሪእያ ሠናየ መርዓዌ።

ሥላሴ
ኢቀዋሚሆሙ ለአሚነ ኪሩቤል ወሱራፊ ወጽድቀ አፍኒን ጻድቅ ጻድቃነ ታሕቱ ወላዕሉ፤
ቅብዐተ ለእመ ረከበ ቅብዐተ ይተሉ፤
ወእመ ጸጋ ይረክብ ምስለ እለጸጋ ይሄሉ፤
ወለተዋሕዶ እንተ ያደሉ፤
ብእሴ ይመስል በአምሳሉ፤
ለዘጠፍአ ወኢኮነ ኩሉ።

ዘይእዜ
እፎ ትርኅቅ ዘእመርዓዊ ወኀበ መርዓዊ ትጸልዕ ዘመደ መርዓዊ አሐዱ፤
እስመ ኀቃፊሃ ወሰዋቂሃ መርዓ ዮሴፍ ወመርዓ መርዓዊ ወዛብሎን እዱ፤
ለእደ ይሁዳ ወስምዖን ወእደ ዛብሎን በሙራዱ፤
ወምስለ ዛቲ መርዓት እመ ታንቀዓዱ፤
ኀበ መርዓዊ መርዓት ለመርዓ ዮሴፍ ዘመዱ፤
ወምስለ ዛቲ መርዓት እመ ታንቀዓዱ።

መወድስ
እግዝእተ ኀልዮ ሐዊረ ሀገረ ሀገሩ ለሀገረ ዳዊት ሰሎሞን ወእመ ሰሎሞን ወሳቤላ፤
ዘቅድመ ዋሕድ አክዓብ መክብበ ሆሴዕ ወኤላ፤
ሕዝበ እስራኤል ለእስራኤል እመ ኀልቁ ኃይላተ ብእሲ ዘኢኀልቀ ኀይላ፤
ወኩሉ ማእከለ እዳ ለእመ ፈረስ ይጠፍእ ትጼውእ ሠረገላ፤
ያብጽሃ ወያልጽቃ መንገለ ክፍላ፤
ለመርዓት ሠረገላ ሠረገላ ዳዊት አኃዜ ኩላ፤
ወከመ ኀበ አይ ተሐውር ዘምስለ እጓላ፤
መርዓት ለመርዓት ዘዘተሰአለት ይሴአላ፤
አኅዘ ሠረገላ ዐቢይ ዐቢየ ዘካርያስ ተድላ፤
መርዓት ለመርዓት ዘዘተሰአለት ይሴአላ።

8 months ago | [YT] | 8

ገብር ኄር ቲዩብ Gebr her Tube

ጾመ ገሃድ/ጋድ
በመምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ
ገሃድ፡- መገለጥ፣ ማታየት፣ መታወቅ፣ ማለት ሲሆን፤
ጋድ፡- ማለት ደግሞ ምትክ፣ ለውጥ፣ ቅያሬ ማለት ነው፡፡
በዓለ ልደት በመጣ ጊዜ ሁሉ በተለይም በዓሉ ዓርብና ረቡዕ ከዋለ ጥያቄዎች ይበዛሉ፡፡ የጥያቄው ምክንያት ደግሞ ደንታቢስነት፣ አለመማር፣ ጥያቄን እንጂ መልስን አለመያዝ ያመጣው ጣጣ ነው፡፡
ማንኛውም ክርስቲያን ስለ ሰባቱ አጽዋማት በቂ ዕውቀት መያዝ አለበት፡፡ ትምህርቱም ከአንድ ቀን የማያልፍ ግፋ ቢል በሁለት ቀን ቁጭብሎ መማር በሚገባ ሊታወቅ የሚችል ቀላል ትምህርት ነው፡፡ አብዛህኛው ክርስቲያን ግን ለሃይማኖታዊ ጉዳዮች የሚሰጠው ጊዜና ትኩረት ዝቅ ያለና በደንታ ቢስነት የተመላ ስለሚሆን እንደዚህ ያሉ ቀላል ጉዳዮች ሳይቀሩ በየዓመቱ ጥያቄ ሁነው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል፡፡
ወቅሶ ከማለፍ ድርሻን መወጣት ይሻላልና ቀላል ትምህርት ነው ያልኩትን ጾም ከተነሣሁበት ከገሃድ ጀምሬ ለማብራራት ልሞክር ሰባት ዓመት የሞላው ጤነኛ ክርስቲያን ሊጾማቸው የታዘዙ ሰባት የአዋጅ አጽዋማት አሉ እነርሱም
1. ገሃድ/ ጋድ ትርጉሙን ከላይ ስላስቀመጥኩት ወደምሥጢሩ ስገባ ይህ ጾም የልደትና የጥምቀት ማዜማ ነው ፍትሐ ነገሥቱ አንቀጽ 15 ቁጥር567 ላይ ‹‹ እንደ ዐቢይ ጾም በመጠንቀቅ የሚጾም አለ ብሎ ሌሎቹን ከዘረዘረ በኋላ…ወጾመ ድራረ ልደት ወጾመ ድራረ ጥምቀት፡- የልደትና የጥምቀት ዋዜማ ጾም ነው ይላል፡፡ አንዳንዶች በጾም ላይ ጾም የለምና ለገና ጋድ የለውም ለማለት ይሞክራሉ ቁምነገሩ ግን ጾሙን ደርበን ሳይሆን ለብቻ አንድ ዕለት ጨምረን ነው እየጾምን ያለንው፡፡
ከኅዳር 15 እስከ ታኅሣሥ 28 ያለው ቀን ሲቆጠር 44 ነው፡፡ ይኸውም 40ው የነቢያት ጾም ነው ሦስቱ ቀናት አንዱ የመበሥር የጌታ፣ ሁለተኛው የተበሣሪ የእመቤታችን ሦስተኛው የአብሣሪ የቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በሌላ መንገድ ሦስቱ ቀን የአብርሃም ሦርያዊ ጾም ነው፡፡ ይህ አባት በሦስት ቀን ሱባኤ ተራራ ማፍለሱን ታኅሣሥ 6 የሚነበበው ስንክሳር ይነግረናል፡፡ ስለዚህ ከ44ቱ ቀናት 40ው የነቢያት፣ ሦስቱ የጌታ፣ የእመቤታችን፣ የቅዱስ ገብርኤል/የአብርሃም ሦርያዊ/ የፊልጶስ ደቀመዛሙርቱ ሊቀብሩት ሥጋው ተሠውሮባቸው ሦስት ቀን ጹመው ያገኙበት/፣ 44ኛዋ ቀን ግን ያለምን ተቀናቃኝ ገሃድ ወይም ጋድ ናት፡፡ ገሃድ መገለጥ ነው በባሕርየ መለኮቱ የማይታየው ጌታ በተዋሕዶተ ትስብእት ስለተገለጠልን መቀበያ አድርገን እንጾመዋለን።

ጋድ ባለው ግን የጥምቀትና የልደት በዓል ዓርብና ረቡዕ ቢውሉ ጾም የለምና ለዚያ ምትክ ማለት ነው፡፡ ይህንን ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር566 እንዲህ ይገልጾታል (ወዓዲ ረቡዐ ወዓረበ በኵሉ ሱባኤ ዘእንበለ መዋዕለ ሃምሳ ወበዓለ ልደት ወጥምቀት ሶበ ኀብሩ ቦሙ፡- ዳግመኛም ረቡና ዓርብን በየሳምንቱ ሊጾሙ ይገባል፤ ከበዓለ ሃምሳ በስተቀር እንዲሁም ልደትና ጥምቀት ጊዜ ገጥሟቸው ረቡና ዓርብ ከሚውሉበት ጊዜ በቅር፡፡) ከዚህ የምንረዳው ልደትና ጥምቀት ዓርብና ረቡዕ ሲውሉ ጾም አለመኖሩን ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በምትካቸው አንድ ቀን የምንጾምላቸው መሆኑ ነው፡፡
የጥር 11 ቀን ስንክሳርም እንዲህ ይላል ከላይ የገሃድን ነገር እያብራራ ከመጣ በኋላ …በዚች ዕለት ምእመናን እስከምሽት እንዲጾሙ ያዘዙበት ፣ምክንያቱ ይህ ነው፡፡ የልደትና የጥምቀት በዓል በረዱዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ሃምሳ የሚበላውን የትሉላት መብል(ሥጋ ወተት ዕንቁላል) በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲያከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላት ናቸውና፡፡
እኛ በዚህ በኃላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን…እያለ ይቀጥላ፡፡ ይህ ሁኖ ሳለ አንዳንድ ሰዎች በዚሁ በጥር 11 ቀን ስንክሳር መጨረሻ ላይ ያለውን አርኬ ጠቀሰው ከላይ የተነበበውን ሙሉ ንባን ዘንግተውና ትተው ለገና ገሃድ የለውም ለማለት ‹‹ ሰላም እብል ለጾመ ዕለት ዋሕድ፤ ዘስሙ ገሃድ፡- ስሙ ገሃድ ለሚባል የአንድ ቀን ጾም ሰላም እላለሁ የሚለውን ይጠቅሳሉ ጥቅሱ ቁርበተ ነክ ነው ሙሉ ስንክሳሩ ሲነበብ አንቀላፍቶ ወይም ስንክሳሩን ሳይሰማ ከአርኬው ብቻ ለደረሰ ሰው ይመስለዋል እንጂ የጥር 11ዱ ስንክሳርስ በማያሻማ ሁኔታ በግልጽና በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡ ገሃድም ለለልደትም ለጥምቀትም የተሠራ ነው፡፡ ዋሕድ ያለው የልደትና የጥምቀጥ ገሃድ አንድ ተብሎ ስለሚቆጠር ነው 44ቱ ጾመ ነቢያት አንድ ተብሎ እንደሚቆጠር፡፡
ገሃድ የሌላቸው ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ፍልሰታ ፋሲካቸው ከረቡዕና ከዓርብ ላይ ሲሆን ይጾማሉ፡፡
2. ከላይ ዝርዝሩን የገለጽንው ጾመ ነቢያ ከኅዳር 15-ታኅሥሥ28
3. ጾመ ነነዌ የነነዌ ሰዎች ከእሳት የዳኑበት
4. ዐቢይ ጾም ዐቢይ እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሁኖ የጾመው
5. ጾመ ሐዋርያ አባቶቻን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ለስብከተወንጌል ከመውጣታቸው በፊት የጾሙት
6. ጾመ ፍልሰታ ለማርያም/ጾመ ማርያም ሐዋርያት የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት ለማየት ያበቃቸው ጾም
7. ጾመ ረቡዕ ወዓርብ፤ ረቡዕ የጌታችን ሞቱ የተወሰበት ዓርብ ተሰቅሎ የሞተበት ነው ይህን ዐውቆ የማይጾም እየጸመም የማያውቅ ክርስቲያን ሰነፍ ደካማ ይባላልና እናት ተምራ ለልጇ፣ አባ ተምሮ ለልጁ ሊያተምረው ይገባል፡፡ መልካም ገሃድ፡፡

11 months ago | [YT] | 10

ገብር ኄር ቲዩብ Gebr her Tube

ነገ ከሰአት ይጠብቁን

1 year ago | [YT] | 12