Hamere Berhan | ሐመረ ብርሃን

ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት
+ ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር +
+ ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ +


Hamere Berhan | ሐመረ ብርሃን

የቀደመው ዘመን ዘመኑን ብቻ ሳይሆን ዘመናችንንም የዋጀ ነው።

የነበረው ጥበብም ረቂቅ እና የሚያድን እውቀት በመሆኑ ከዚህ እውቀት ዛሬ ድረስ ያለውን ጨለማ የሚያርቅ የቅድስና ብርሃን ፈንጥቋል።
ሐመረ ብርሃን ይህን ፍለጋ ወደ ቀድሞው ነገር የሚጓዝ የብርሃን መርከብ ነው።

ወደ ቀድሞው ስንመለስ የምናገኘው ክብሩን የሚገልጡ ቃላትን ፈጽሞ የማናገኝለት አባ ጊዮርጊስን ሲሆን ጥቂት ስንመለስ ደግሞ የምንደርሰው እንደ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ካሉ ደገኛ ሊቃውንት ነው።

የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን 600ኛ ዓመት ክብረ በዓል ለማክበር፤ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬን ለመዘከርና ሌሎችን የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ልዕልናዎች ለዚህ ዘመን ትውልድ ለማቅመስ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ "የአእላፋት ሳምንት" በሚል መጠሪያ ባዘጋጀው ዐውደ ርእይ ከሚሳተፉ ማኅበራትና ተቋማት አንዱ ሐመረ ብርሃን ሲሆን ዐውደ ርእዩ በሚካሄድባቸው 8 ተከታታይ ቀናት ሥራዎቻችንን ይዘን የምንገኝ መሆኑን እንገልጻለን።

በዐውደ ርእዩ ላይ ጥንታዊ ይዘታቸውን የጠበቁ በተቋማችን የተዘጋጁ

💠 የብራና፣ የሸራ እና የገበታ ቅዱሳት ሥዕላት
💠 በነሀስና በብር የተዘጋጁ ንዋየ ቅዱሳት
💠 ከእንጨት የተሰሩ የጥበብ ውጤቶች
💠 የልደት በዓልን አስመልክቶ
ለስጦታ የሚሆኑ ሥራዎችን

ለሽያጭ ይዘን እንቀርባለን።

ግዮን ሆቴል
ከታህሳስ 16 - 23

☎️ 0909444455
☎️ 0909444400

#ወደ_ቀድሞው_ነገር_እንመለስ #hamereberhan #janderebawmedia #የአእላፋት_ዝማሬ #exhibition

2 days ago | [YT] | 171

Hamere Berhan | ሐመረ ብርሃን

ዝክረ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ለቃለ እግዚአብሔር መፋጠን የዘመናችን ሰማዕትነት ነውና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወርኃዊ ክብረ በዓሉ ላይ ትገኙ ዘንድ "ኑ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ" ብሎ አፈወርቅ በተሰኘ አንደበቱ ጠርቷችኋል።

አዲስ መንገድ   |   ክፍል ሁለት

◈ ጥቅምት 12 / 2018 ዓ.ም (ረቡዕ)
◈ 11:00 ሰዓት
◈ ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት ግቢ
    ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ

1 month ago | [YT] | 104

Hamere Berhan | ሐመረ ብርሃን

ከዚህ ዘመን ትውልድ ለግሸን ደብረ ከርቤ
የተበረከተ ቅርስ የሚሆን ስጦታ!!

ሐመረ ብርሃን "ንግባእኬ ኀበ ጥንተ ነገር" "ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ" በማለት ከንጹሕ ኢትዮጵያዊ ምንጭ የተቀዱ ጊዜያዊ ሳይሆኑ ታሪካዊ የጥበብ ውጤቶችን በእኛው ዘመን ጥበበኛ እጆች
እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በተቋሙ ከሚሰሩት ድንቅ ሥራዎች መካከል የሆነውን በነሀስ የተለበጠ የብራና ድርሳነ ሚካኤል ዘንድሮ ለተመረቀው ለግሸን ቅዱስ ሚካኤል መስከረም 21/2018 ዓ.ም
በተከበረው ታላቅ ክብረ በዓል ላይ አበርክቷል።

ሐመረ ብርሃን ባሳለፍነው ዓመት ካበረከተው በነሀስ የተለበጠ ባለ ምልክት የብራና ቅዳሴ መጽሐፍ ቀጥሎ ለግሸን ደብረከርቤ ስጦታን ሲያበረክት ይህ ሁለተኛው ሲሆን በዘንድሮው ዓመት ታላቅ ገጸበረከት ላይ አሻራችሁን ያሳረፋችሁ ምዕመናንን እንኳን የዚህ ዕድል ተሳታፊ ለመሆን በቃችሁ እንላለን።

አሁንም ለገዳማት እና ለአድባራት ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ ምዕመናን በሐመረ ብርሃን ጥበበኛ እጆች የተዘጋጁ የብራና መጻሕፍትንና ሥዕላትን፣ ከነሀስ ከብርና ከተለያዩ ማዕድናት እንዲሁም ከእንጨት የተሰሩ ሥራዎችን በግልም ሆነ በጋራ በመግዛት ማበርከት እንደምትችሉ ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው!!!


ከዚህ በፊት ለግሸን ደብረ ከርቤ የተበረከተ ባለምልክት የብራና ቅዳሴ መጽሐፍ
👇👇👇
https://youtu.be/OYjGVpotx9U?si=NsqyI...

2 months ago | [YT] | 144

Hamere Berhan | ሐመረ ብርሃን

ዝክረ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ለቃለ እግዚአብሔር መፋጠን የዘመናችን ሰማዕትነት ነውና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወርኃዊ ክብረ በዓሉ ላይ ትገኙ ዘንድ "ኑ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ" ብሎ አፈወርቅ በተሰኘ አንደበቱ ጠርቷችኋል።

አዲስ መንገድ   |   ክፍል አንድ

◈ መስከረም 12 / 2017 ዓ.ም (ሰኞ)
◈ 11:00 ሰዓት
◈ ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት ግቢ
    ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ

2 months ago | [YT] | 134

Hamere Berhan | ሐመረ ብርሃን

ሐመረ ብርሃን ልጆቹን አስመረቀ!!

ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ስራ ድርጅት የቤተ ክርስቲያንን አደራ ተረክበው የሚያስቀጥሉ ሕጻናትን ለማፍራት እየሰራ የሚገኝበት የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዘመነ ክረምት የት/ት መርሐግብር ደቀመዛሙርትን ነሐሴ 25/2017 ዓ.ም አስመረቀ።

እድሜያቸው ከ7-14 ዓመት የሆኑ ደቀመዛሙርት የ6 ሳምንቱን ስልጠና በአዳሪ እና በተመላላሽ ሲማሩ የቆዩ ሲሆን በአጠቃላይ 366 ደቀመዛሙርት በዕለቱ የታላላቅ ገዳማት አበምኔቶችና አባቶች፣ ወላጆቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ሌሎች የክብር እንግዶች በተገኙበት ተመርቀዋል።

3 months ago | [YT] | 153

Hamere Berhan | ሐመረ ብርሃን

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገራችሁ!!

የበግ እና የፍየል ቆዳ ለሐመረ ብርሃን

ለአዲስ ዓመት / መስከረም 1, 2018 ዓ.ም

የመቀበያ ቦታ ፦
ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት ግቢ ውስጥ ብቻ !!

⚠️ ውድ የሐመረ ብርሃን ቤተሰቦች፤ ከዚህ ቀደም የቆዳ ስጦታችሁን እንቀበልባቸው የነበሩ ደብራትና ቦታዎች ላይ በዚህ በዓል የቆዳ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች የሌሉን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

3 months ago | [YT] | 76

Hamere Berhan | ሐመረ ብርሃን

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዘመነ ክረምት አዳሪ የሕጻናት ትምህርት መርሐግብር ተማሪዎች ከወላጆቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የኅብረት የእግር ጉዞ ወደ መናገሻ ጋራ መድኅኔዓለም ገዳም በዕለተ እሁድ 27/11/2017 ዓ.ም ተካሄደ።

በጉዞውም ላይ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የክርስቶስን ሕማም እያሰቡ ተራራማውን መንገድ እንዲጓዙ መምህራን አባቶች 14ቱን ፍኖተ መስቀል በመንገዳቸው መካከል እየተረኩ አስተምረዋል።

4 months ago | [YT] | 195