EBC
ፓስፖርት ማውጣት ዜጎች የሚቸገሩበት ጉዳይ እንዳይሆን በተቋማዊ ሪፎርሙ ተሠርቷል - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ************************ ተቋማዊ የአሠራር ዝማኔ ያደረገው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፓስፖርት ማውጣት ዜጎች የሚቸገሩበት ጉዳይ እንዳይሆን መሥራቱን አስታውቋል። የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ከኢቢሲ ዳጉ መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ከአሠራር ጋር በተያያዘ ያሉ ክፍተቶች እና የሚነሡ ቅሬታዎችን ለመፍታት በትኩረት መሠራቱን ገልጸዋል። በተለይም በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የዜጎች የፓስፖርት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የአቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ስለመሰጠቱ ነው የተናገሩት። በዚህም ባለፈው የ2017 በጀት ዓመት ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች ፓስፖርት መስጠት ስለመቻሉ ዋና ዳይሬክተሯ አመላክተዋል። ይህን ቁጥር ከፍ ለማድረግ የተቋሙ ሠራተኞች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን እና አገልግሎቱ በ2 ፈረቃ መሰጠት መጀመሩን አስረድተዋል። በዚህ የሚፈጠረውን አቅም በመጠቀም በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት አራት ሚሊዮን ዜጎች ፓስፖርት እንዲያገኙ እየተሠራ ስለመሆኑ አመላክተዋል። ይህን እሙን በማድረግ ውስጥ በተለይም በተደረገ ተቋማዊ ጥናት አማካኝነት ብዛት ያላቸው ዜጎች አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጓዙበትን ርቀት በማጤን የቅርንጫፍ ማስፋፋት ስለመደረጉ ገልጸዋል። ለአራት ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ ለመሆን የሚሠሩ መሠረተ ልማቶች፣ የሚፈጠረው ብቁ የሰው ኃይል እና የሚካብተው የአሠራር ልምድ ለቀጣዮቹ ጊዜያት ላለው አሠራር አቀጣጣይ እንደሚሆን ነው የተናገሩት። አሁን ያለው የፓስፖርት ክፍያ ተመን የዜጎችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ስለመሆኑም የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሯ፣ የዶክመንቱን ደኅንነት የሚያረጋግጥ ማይክሮ ቺፕ የተካተተበት እና የማይክሮ ቺፕ ቴክኖሎጂ ውድ እና ፓስፖርቱንም ለማተም በርካታ ደረጃዎችን የሚያልፍ እንደሆነ ጠቁመው፣ የወጣው ተመን ከሌሎች ሀገራት አንፃር ሲታይ ክፍያው ዝቅተኛ ስለመሆኑ አመላክተዋል። በሀገር ውስጥ የዜጎች የመክፈል አቅም ሲቃኝም አስቻይ ስለመሆኑም ነው የተናገሩት። የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት በ2017 ዓ.ም የካቲት ወር ላይ ስለመጀመሩ አስታውሰው፣ ያንን ተከትሎ በተሻሻለው ክፍያ በተለይም ፓስፖርቱ ዘመኑን የዋጀ እና ኅብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያን የሚገልጽ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል። የክፍያ ሥርዓቱ አማራጮች ያሉት ሲሆን በ2 ወር ከ15 ቀን ለሚወሰድ ፓስፖርት 5 ሺህ ብር ሲከፈል፣ በአስቸኳይ አገልግሎት የ25 ሺህ ብር ክፍያ በ2 ቀን ፓስፖርት ማግኘት ይቻላል።
5 days ago | [YT] | 283
EBC
ፓስፖርት ማውጣት ዜጎች የሚቸገሩበት ጉዳይ እንዳይሆን በተቋማዊ ሪፎርሙ ተሠርቷል - የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት
************************
ተቋማዊ የአሠራር ዝማኔ ያደረገው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፓስፖርት ማውጣት ዜጎች የሚቸገሩበት ጉዳይ እንዳይሆን መሥራቱን አስታውቋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ከኢቢሲ ዳጉ መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ከአሠራር ጋር በተያያዘ ያሉ ክፍተቶች እና የሚነሡ ቅሬታዎችን ለመፍታት በትኩረት መሠራቱን ገልጸዋል።
በተለይም በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የዜጎች የፓስፖርት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የአቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ስለመሰጠቱ ነው የተናገሩት።
በዚህም ባለፈው የ2017 በጀት ዓመት ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች ፓስፖርት መስጠት ስለመቻሉ ዋና ዳይሬክተሯ አመላክተዋል።
ይህን ቁጥር ከፍ ለማድረግ የተቋሙ ሠራተኞች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን እና አገልግሎቱ በ2 ፈረቃ መሰጠት መጀመሩን አስረድተዋል።
በዚህ የሚፈጠረውን አቅም በመጠቀም በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት አራት ሚሊዮን ዜጎች ፓስፖርት እንዲያገኙ እየተሠራ ስለመሆኑ አመላክተዋል።
ይህን እሙን በማድረግ ውስጥ በተለይም በተደረገ ተቋማዊ ጥናት አማካኝነት ብዛት ያላቸው ዜጎች አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጓዙበትን ርቀት በማጤን የቅርንጫፍ ማስፋፋት ስለመደረጉ ገልጸዋል።
ለአራት ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ ለመሆን የሚሠሩ መሠረተ ልማቶች፣ የሚፈጠረው ብቁ የሰው ኃይል እና የሚካብተው የአሠራር ልምድ ለቀጣዮቹ ጊዜያት ላለው አሠራር አቀጣጣይ እንደሚሆን ነው የተናገሩት።
አሁን ያለው የፓስፖርት ክፍያ ተመን የዜጎችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ ስለመሆኑም የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሯ፣ የዶክመንቱን ደኅንነት የሚያረጋግጥ ማይክሮ ቺፕ የተካተተበት እና የማይክሮ ቺፕ ቴክኖሎጂ ውድ እና ፓስፖርቱንም ለማተም በርካታ ደረጃዎችን የሚያልፍ እንደሆነ ጠቁመው፣ የወጣው ተመን ከሌሎች ሀገራት አንፃር ሲታይ ክፍያው ዝቅተኛ ስለመሆኑ አመላክተዋል።
በሀገር ውስጥ የዜጎች የመክፈል አቅም ሲቃኝም አስቻይ ስለመሆኑም ነው የተናገሩት።
የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት በ2017 ዓ.ም የካቲት ወር ላይ ስለመጀመሩ አስታውሰው፣ ያንን ተከትሎ በተሻሻለው ክፍያ በተለይም ፓስፖርቱ ዘመኑን የዋጀ እና ኅብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያን የሚገልጽ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል።
የክፍያ ሥርዓቱ አማራጮች ያሉት ሲሆን በ2 ወር ከ15 ቀን ለሚወሰድ ፓስፖርት 5 ሺህ ብር ሲከፈል፣ በአስቸኳይ አገልግሎት የ25 ሺህ ብር ክፍያ በ2 ቀን ፓስፖርት ማግኘት ይቻላል።
5 days ago | [YT] | 283