bt Abraham Tube ቤተ አብርሃም Premiere
ከዚህ ባለፈም አባ ዳንኤል በሰው ዘንድ የተናቁትንም ማክበርን ያውቅበታል:: ለምሳሌ በሴቶች ገዳም "እብድ" ናት ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማን: በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዻዻሳቱ ሳይቀር "እብድ" ነው ብለው የናቁትን ቅዱስ ምሕርካን: እብድ ሳይሆኑ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል::አባ ዳንኤል ሐዋርያዊም ነበር:: በጊዜው ጦማረ ልዮን የሚባል የኑፋቄ ደብዳቤ ይላክ ነበርና ለዚህ ኬልቄዶናዊ ኑፋቄ በትጋት ምላሽ ይሰጥ ነበር:: አንድ ቀንም በንጉሥ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ቅዱሱ ከወታደሩ ቀምቶ ስለ ቀደደው ለሞት እስኪደርስ ደብድበውታል::ጻድቁ አባ ዳንኤል አንዴ አውሎጊስ የሚባል ደሃ ድንጋይ ጠርቦ እንግዳ ሲቀበል ተመልክቶ "ጌታ ሆይ! ይህንን ደግ ሰው ለምን ደሃ አደረከው?" ሲል በፈጣሪ ሥራ ገባ::ጌታም እንደ ወትሮው በገሃድ ተገልጦ "በነፍስህ ትዋሰዋለህ?" አለው:: "አዎ ጌታየ" ስላለው ጌታችን ለአውሎጊስ ሃብትን ሰጠው:: ግን ወዲያው የጦር አለቃና ጨካኝ ሰው ሆነ::ጻድቁ ወሬውን ሰምቶ ሊጠይቅ ቢሔድ የአውሎጊስ ወታደሮች ደበደቡት:: ጌታችንም አባ ዳንኤልን ወደ ፍርድ ዙፋኑ አቅርቦ "ወዳጄን መልስልኝ" አለው:: እመ ብርሃን ግን ቀርባ የልጇን እግር ሳመች::"ልጄ ሆይ ማር!" አለችው:: ጌታም "እሺ" ብሎ ጻድቁን ወደ በአቱ: አውሎጊስን ወደ ቀደመ ግብሩ መለሳቸው:: የአባ ዳንኤል ድንቁ ብዙ ነው::ሌላው ቢቀር ሽፍታ አባ ዳንኤልን መስሎ ወደ ደናግል ገዳም: ሊዘርፍ: በማታለል ገባ:: ደናግሉም ጻድቁ መስሏቸው እግሩን አጥበው ዐይነ ስውሯን ቢቀቧት ዐይኗ በርቷል:: ሽፍታውም ደንግጦ ንስሃ ገብቷል:: አባ ዳንኤል ግን ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::<< አባ ማቴዎስ ገዳማዊ >>ጻድቁ ከታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ የመንፈስ ልጆች አንዱ ሲሆን የበርሃ ኮከቦች ከሚባሉት አንዱ ነው:: ብዙ ደቀ መዛሙርትን ያፈራ: ከግሩማን አራዊት ጋር የኖረ: ብዙ ተአምራትን የሠራ: ናዛዜ ሕዙናን የሆነ አባት ነው:: ዛሬ ዕረፍቱ ነው::የአባቶቻችን በረከት ይደርብን::=>ታሕሳስ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት1.ስብከተ ነቢያት2.አባ ዳንኤል ገዳማዊ3.አባ ማቴዎስ ገዳማዊ4.ብጽዕት ዲዮጥርስ=>ወርሐዊ በዓላት1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)4.አባ ባውላ ገዳማዊ5.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ6.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)"ይህን በመጀመሪያ እወቁ:: በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም:: ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና:: ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ::"(2ዼጥ. 1:20)<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE
5 days ago | [YT] | 5
bt Abraham Tube ቤተ አብርሃም Premiere
ከዚህ ባለፈም አባ ዳንኤል በሰው ዘንድ የተናቁትንም ማክበርን ያውቅበታል:: ለምሳሌ በሴቶች ገዳም "እብድ" ናት ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማን: በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዻዻሳቱ ሳይቀር "እብድ" ነው ብለው የናቁትን ቅዱስ ምሕርካን: እብድ ሳይሆኑ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል::አባ ዳንኤል ሐዋርያዊም ነበር:: በጊዜው ጦማረ ልዮን የሚባል የኑፋቄ ደብዳቤ ይላክ ነበርና ለዚህ ኬልቄዶናዊ ኑፋቄ በትጋት ምላሽ ይሰጥ ነበር:: አንድ ቀንም በንጉሥ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ቅዱሱ ከወታደሩ ቀምቶ ስለ ቀደደው ለሞት እስኪደርስ ደብድበውታል::
ጻድቁ አባ ዳንኤል አንዴ አውሎጊስ የሚባል ደሃ ድንጋይ ጠርቦ እንግዳ ሲቀበል ተመልክቶ "ጌታ ሆይ! ይህንን ደግ ሰው ለምን ደሃ አደረከው?" ሲል በፈጣሪ ሥራ ገባ::
ጌታም እንደ ወትሮው በገሃድ ተገልጦ "በነፍስህ ትዋሰዋለህ?" አለው:: "አዎ ጌታየ" ስላለው ጌታችን ለአውሎጊስ ሃብትን ሰጠው:: ግን ወዲያው የጦር አለቃና ጨካኝ ሰው ሆነ::
ጻድቁ ወሬውን ሰምቶ ሊጠይቅ ቢሔድ የአውሎጊስ ወታደሮች ደበደቡት:: ጌታችንም አባ ዳንኤልን ወደ ፍርድ ዙፋኑ አቅርቦ "ወዳጄን መልስልኝ" አለው:: እመ ብርሃን ግን ቀርባ የልጇን እግር ሳመች::
"ልጄ ሆይ ማር!" አለችው:: ጌታም "እሺ" ብሎ ጻድቁን ወደ በአቱ: አውሎጊስን ወደ ቀደመ ግብሩ መለሳቸው:: የአባ ዳንኤል ድንቁ ብዙ ነው::
ሌላው ቢቀር ሽፍታ አባ ዳንኤልን መስሎ ወደ ደናግል ገዳም: ሊዘርፍ: በማታለል ገባ:: ደናግሉም ጻድቁ መስሏቸው እግሩን አጥበው ዐይነ ስውሯን ቢቀቧት ዐይኗ በርቷል:: ሽፍታውም ደንግጦ ንስሃ ገብቷል:: አባ ዳንኤል ግን ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::
<< አባ ማቴዎስ ገዳማዊ >>
ጻድቁ ከታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ የመንፈስ ልጆች አንዱ ሲሆን የበርሃ ኮከቦች ከሚባሉት አንዱ ነው:: ብዙ ደቀ መዛሙርትን ያፈራ: ከግሩማን አራዊት ጋር የኖረ: ብዙ ተአምራትን የሠራ: ናዛዜ ሕዙናን የሆነ አባት ነው:: ዛሬ ዕረፍቱ ነው::
የአባቶቻችን በረከት ይደርብን::
=>ታሕሳስ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ስብከተ ነቢያት
2.አባ ዳንኤል ገዳማዊ
3.አባ ማቴዎስ ገዳማዊ
4.ብጽዕት ዲዮጥርስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ባውላ ገዳማዊ
5.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
6.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
"ይህን በመጀመሪያ እወቁ:: በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም:: ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና:: ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ::"
(2ዼጥ. 1:20)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🔵TELEGRAM 🔴 YOUTUBE
5 days ago | [YT] | 5