Yidnekahew Melis mella

በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሐዱ አምላክ አሜን። አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅድስ ሰም ከልዩ ልዩ ድንጋፄና ፍርሃት እድን ዘንድ ይህንን የ ቅዱስ ገብርኤልን ድርሳን እጸልያለሁ እንዲህ እያልኩ ፣ መድኀንኤል ፣ሕያውታኤ፣ አውካኤል ፣ ተርቡታኤል ፣ ግኤል ፣ ዝኤል ፣ ቡኤል ፣ ይህን አስማተ መለኮት እግዚአብሔር ለቅዱስ ገብርኤል የሰጠው መልአኩ ከዲያብሎስ ጋር ክርክር በጀመረ ግዜ ድል እንዲነሳበት እና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለማብሰር በተላከ ግዜከቃሉ ግርማ የተነሳ

እንዳትደነግጥ እንዳትፈራ

መጽንዔ ኃይል እንዲሆናት ነው። አቤቱ ለእኔ

ለአገልጋይህም እንደዚሁ ኃይል ጽንዕ ሰጥተህ ከመዓልትና

ከሌሊት ድንጋጼ አድነኝ አሜን።

ማርያም የተላክህ ገብርኤል ሆይ

ከላይ ከሰማይ ወደ ድንግል ሰላም እልሃለሁ። ደስታን እልሃለሁ። ፅንሰ ቃልን

አብሣሪ መልአክ ሆይ ሰላም

አስተምረህ የመታሳምን መልአክ

ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ሰማያዊ

ነድ እሳት ዖፈ ርግብ ሆይ ሰላም

እልሃለሁ። ፍጹም ደስታን

ተናጋሪ መልአክ ሆይ ሰላምእልሃለሁ። ከእደ ሞት የምታድን መልአክ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። የአንተን አማላጅነት በመዓልትም በሌሊትም ተስፋ ሰለምናደርግ ጥበቃህ አይለየን ። የእግዚአብሔር ልዩ ባለሟል ነህና ለዘላለሙ አሜን። አቡነ

ዘበሰማያት

1 week ago | [YT] | 14,057