ዓባይ ዜና - Abbay News

#ማሳሰቢያ

ዓባይ ቴሌቪዥን ወደ ውድ ተመልካቾቹ ከሚያደርሳቸው ተወዳጅ እና ከፍተኛ ተመልካች ካላቸው ዝግጅቶች አንዱ ‹ማን ይቀነስ› የተሰኘው መሰናዶ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን በጥያቄና መልስ የታጀበ የመዝናኛና የጠቅላላ ዕውቀት መመዘኛ ፕሮግራም በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በተለይም በቲክቶክ በመቆራረጥ ላልተገባ ዓላማ የሚያውሉ አካላት እንዳሉ ደርሰንበታል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ በዝግጅቱ አቅራቢ የተላለፉ ጥያቄዎችን በተለያዩ ጊዜያት ከተሰጡ የተወዳዳሪ ምላሾች ጋር በማገጣጠም ያልተገቡ ፖለቲካዊ ትርጉሞችን በማሰጠት የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እናሳስባለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ የዓባይ ቴሌቪዥን ትክክለኛው የቲክቶክ አድራሻ ከ967 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ውድ ተመልካቾቻችን በተዛቡ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ግራ እንዳትጋቡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

በተጨማሪም ሌሎቹ የዓባይ ቲቪ ትክክለኛ ማህበራዊ ሚዲያ አድራሻዎች የሚከተሉት ናችው፡፡

ዓባይ ቲቪ መዝናኛ (YouTube) : youtube.com/@abbay-tv
ዓባይ ዜና (YouTube) : youtube.com/@AbbayTV
ቲክቶክ: www.tiktok.com/@abbay_tv
ኢንስታግራም: www.instagram.com/abbay.tv
ፌስቡክ: www.facebook.com/AbbayTV


ዓባይ ቲቪ
የኢትዮጵያ ምርጥ

5 days ago (edited) | [YT] | 14