Live Your Dream ህልምህን ኑረው
ራስህን “መሰብሰብ” (ክፍል ሶስት 3)“ያደነቅኩትን ሰው ሁሉ መምሰል አልችልም”ያደነቅኩትን ሰው ሁሉ መምሰል አልችልም ከሚለው አመለካከት የሚመነጨው ራስን መሰብሰብ፣ ራሴን መሆንና መኖር ትቼ ሌላው ሰው ለመምሰል ከመሯሯጥ ነጻ ወደ መውጣት መምጣት ማለት ነው፡፡ እኔን የሚመስል ሌላ ሰው ተፈጥሮ አያውቅም ወደፊትም ሊፈጠርም አይችልም፡፡ እኔ ብቻ ልሆነውና ልኖረው የሚገባ ማንነት አለኝ፡፡ ስለዚህ ማንነቴንና ሁኔታዬን ሁሉ እኔ፣ ወዳጆቼና ይህቺ አለም ስለምትፈልገው ሌላውን ሰው ወደመሆን ስሄድ ከአላማዬ እለያያለሁ፡፡ ይህንን እውነታ በሚገባ ለማብላላት የሚከተሉትን ሃሳቦች እናጢን፡፡1. ልዩ የሆንኩበትን ሁኔታዬን ማወቅ“ከቤተሰቦቼ፣ ከጓደኞቼና ከወዳጆቼ እኔን ለየት የሚያደርገኝ ተሰጥኦዬ ምንድን ነው?” “ሌሎችን የሚያታግላቸው እኔን ግን የሚቀናኝ ነገር ምንድን ነው?” ለሚሉትና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስን ማግኘት ታላቅ መሰብሰብ ነው፡፡2. ማስመሰልን ማቆምለመሰብሰብ ልወስዳቸው ከምችላቸው እርምጃዎች አንዱ፣ ለተቀባይነትም ሆነ ለተወዳጅነት ብዬ ሌላውን ሰው ወይም ቡድንን ለመምሰል ያለኝን ጥረት ማቆም ነው፡፡ በማስመሰል የማገኘው ተቀባይነት እውነተኛ ተቀባይነት አይደለም፡፡ 3. ራስን መቀበልራስን የመቀበል ሚዛናዊነት ያለው፣ በአንድ ጎኑ መለወጥ የምችለውንና የሚገባኝ ነገር መለየትና ያንን የማድረጉን ነጻነት መለማመድ ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ መለወጥ የማልችላቸውን የማንነቴን ክፎሎች በመቀበል፣ ተዳላድሎና ቀና ብሎ መኖር ማት ነው፡፡ሰሞኑ ያበረከትኩላችሁን አምስት ክፍል የያዘ “ራስን የመሰብሰብ” ሃሳብ በትእግስት በመከታተላችሁ ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን🎯🎯🎯🎯🎯🎯🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉዩቱዩብ youtube.com/@Asfawwቴሌግራም t.me/Attitudeplcፌስቡክ www.facebook.com/attitudeaseቲክቶክ tiktok.com/@asfaw_motivation ለአስተያየትዎt.me/Attitudep
7 months ago | [YT] | 2
Live Your Dream ህልምህን ኑረው
ራስህን “መሰብሰብ” (ክፍል ሶስት 3)
“ያደነቅኩትን ሰው ሁሉ መምሰል አልችልም”
ያደነቅኩትን ሰው ሁሉ መምሰል አልችልም ከሚለው አመለካከት የሚመነጨው ራስን መሰብሰብ፣ ራሴን መሆንና መኖር ትቼ ሌላው ሰው ለመምሰል ከመሯሯጥ ነጻ ወደ መውጣት መምጣት ማለት ነው፡፡ እኔን የሚመስል ሌላ ሰው ተፈጥሮ አያውቅም ወደፊትም ሊፈጠርም አይችልም፡፡ እኔ ብቻ ልሆነውና ልኖረው የሚገባ ማንነት አለኝ፡፡ ስለዚህ ማንነቴንና ሁኔታዬን ሁሉ እኔ፣ ወዳጆቼና ይህቺ አለም ስለምትፈልገው ሌላውን ሰው ወደመሆን ስሄድ ከአላማዬ እለያያለሁ፡፡ ይህንን እውነታ በሚገባ ለማብላላት የሚከተሉትን ሃሳቦች እናጢን፡፡
1. ልዩ የሆንኩበትን ሁኔታዬን ማወቅ
“ከቤተሰቦቼ፣ ከጓደኞቼና ከወዳጆቼ እኔን ለየት የሚያደርገኝ ተሰጥኦዬ ምንድን ነው?” “ሌሎችን የሚያታግላቸው እኔን ግን የሚቀናኝ ነገር ምንድን ነው?” ለሚሉትና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስን ማግኘት ታላቅ መሰብሰብ ነው፡፡
2. ማስመሰልን ማቆም
ለመሰብሰብ ልወስዳቸው ከምችላቸው እርምጃዎች አንዱ፣ ለተቀባይነትም ሆነ ለተወዳጅነት ብዬ ሌላውን ሰው ወይም ቡድንን ለመምሰል ያለኝን ጥረት ማቆም ነው፡፡ በማስመሰል የማገኘው ተቀባይነት እውነተኛ ተቀባይነት አይደለም፡፡
3. ራስን መቀበል
ራስን የመቀበል ሚዛናዊነት ያለው፣ በአንድ ጎኑ መለወጥ የምችለውንና የሚገባኝ ነገር መለየትና ያንን የማድረጉን ነጻነት መለማመድ ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ መለወጥ የማልችላቸውን የማንነቴን ክፎሎች በመቀበል፣ ተዳላድሎና ቀና ብሎ መኖር ማት ነው፡፡
ሰሞኑ ያበረከትኩላችሁን አምስት ክፍል የያዘ “ራስን የመሰብሰብ” ሃሳብ በትእግስት በመከታተላችሁ ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯
🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ
ዩቱዩብ youtube.com/@Asfaww
ቴሌግራም t.me/Attitudeplc
ፌስቡክ www.facebook.com/attitudease
ቲክቶክ tiktok.com/@asfaw_motivation
ለአስተያየትዎ
t.me/Attitudep
7 months ago | [YT] | 2