Live Your Dream ህልምህን ኑረው

ፅናት (persistence):

ፅናት ምንድን ነዉ? ለምንስ ያስፈልጋል?

ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ሰኬታማ እንዲሆኑ ከሚያደርጋቸዉ ብቃት አንዱ ፅናት መኖር ነዉ፡፡ ፅናት በአንተርፕረነርሽፕ ትለቅ ስፈራ ይዞ የሚገኝ የአንተርፕረነር ባህሪ ነዉ፡፡
ዐላማ ያላቸዉ ሰዎች ፅናት ከሌላቸዉ ዋጋ የለዉም፡፡ በአለም ላይ ስኬታማ የሆኑ ሰዎች የፅናት ተምሳሌት ናቸዉ፡፡ ማንም ሰዉ አለማዉን ለማሳከት ፅናት ካለዉ በእርግጠኝነት ማሳካት እንደሚችል ታመኖበታል፡፡ ችግር ባይኖር ኑሮ ፅናት አያስፈልግም፡፡ ጽናት ችገሮችና መሰናክሎች እንዴት እንደሚፈቱ ያሰተምረናል፡፡ ፅናት አንድን አላማ እሰከሚሳካ ድረስ ተስፋ ሳይቆረጡ ደጋግሞ መመኮር ማለት ነዉ፡፡ ስኬታማ ሰዎች ባለ ራእይ ናቸዉ፡፡ ራእያቸዉ በረዥም ጊዜ ከፋፍለዉ ማለት በ5፡በ10፡በ15 ወዘተ የሚሳካ ብለዉ ያሰቀምጣሉ፡፡ይህንን የረዥም ጊዜ ራእይ ለማሳካት ጽናት እንደሚስፈለግቸዉ ያምናሉ፡፡ እርስዎስ እንዴት ነዎት? በቀላሉ ችግር ስያጋጥመዎት ተስፋ የሚቆርጡ ነዎት ወይስ ፅናት ያለዎት ሰዉ ነዎት? እስኪ አሁን ደግሞ የፅናት አርአያዎች ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ እንይ፡፡
1) ሄለን ኬለር----እንደተወለዱ በ13 ወራቸዉ ማየትም መስማትም የተሳናቸዉ ነበሩ፡፡ሔለን እየተመሩ በዳሰሳ የዩኒቨርሲቲ ትምህረታቸዉ ጨርሰዋል፡፡ 13 መፅሃፍትን ፅፈዉ ለአለም አበርክተዋል፡፡ቡዙ ንግግሮችን አድረገዋል፤ አስተምረዋል፡፡
2) ጃኒ ኢሬክሰን----ከአንገታቸዉ በታች አይሰራም፡፡ ነገር ግን በጥርሳቸዉ መፃፍ በመለማመድ 35 መፅሓፍ ፅፈዉ ለአለም አበርክተዋል፡፡ በብዙ ቋንቋዎችም ተተርጉመዋል፡፡
3) ክሪስት ብራዉን---ሲወለዱ ጀምሮ አካላቸዉ የመይታዘዝላቸዉ ነበሩ፡፡ነገርግን ሁለት የእግር ጣቶች የሚታዘዝላቸዉ ነበር፡፡በእነኚህ ሁለት የእግር ጣቶቻቸዉ በመጠቀም 8 መፅሓፎች ፅፈዋል፡፡በብዙ ቋንቋዎችም ተተርጉመዋል፡፡
4) ቶማስ ኤድሰን----መብራትን ለመስራት 9999 ሙከራዎችን ከሞኮሩ በሃላ በ10ኛዉ ሺ ሙከራዉን ተሳክቶላቸዋል፡፡
5) ስንታየሁ ተሻለ----በኣዲስ አበባ የሚኖር ሲሆን በተቀሩት የእግር ክፍሎቹ ወንበር፤ጠረጴዛ እየሰራ ቤተሰቡን ያስተዳድራል፡፡
6) ቅዱስ ያሬድ---በታሪክ የምናዉቀዉ ቅዱስ ያሬድ 6 ጊዜ ወድቆ በሰባተኛዉ በመነሳት ቡዙ የቤተክርስተያን መፅሓፍቶችን ደርሰዋል፡፡
ዐላማን ለማሳካት ከነዚህ ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ፅናት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንማራለን፡፡ እነዚህ ሰዎች ይህንን ከሰሩ እኛም ያሰብነዉን አላማ ለማሳካት ምንም የሚያግደን የለም፡፡ ፅናት ካልዎት አላማዎን እዉን ይሆናል፡፡ ፅናት ይስጣችሁ፡፡

2 months ago | [YT] | 2