AG MAN 21

" ውድ እቃ ያለቦታው እርካሽ ነው...!"

አንድ አባት ከሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ልጁን እንዲህ ሲል ተናገረው "ይህ የእጅ ሰዓት አባቴ የሰጠኝ ነው፤ 200 ዓመታት ሆኖታል። ነገር ግን ላንተ ከመስጠቴ በፊት ሂድ እና ሰዓት ቤቶች ስንት ሊገዙህ እንደሚችሉ ጠይቀህ ና።" አለው።
ልጁም ጠይቆ መጣ እና "አሮጌ ስለሆነ 5 ብር እንገዛሃለን" እንዳሉት ነገረው።

አባቱም ድጋሚ ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ሱቆች ጋር ሄዶ እንዲጠይቅ ይነግረዋል። ልጁም ጠይቆ ይመጣ እና አሁንም ከ5 ብር በላይ እንደማይገዙት ይነግረዋል።
"ሙዚየም ሄደህ ጠይቅ" ይለዋል አባቱ። ልጁም ጠይቆ ከመጣ በኋላ "አንድ ሚሊዮን ብር እንደሚገዙኝ ነገሩኝ" አለ።

አባቱም "እንድታውቅ የፈለኩት የአንተንም ትክክለኛ ዋጋ (ቦታ) የሚሰጥህ ትክክለኛ ቦታ ላይ እንድትገኝ እንጂ የተሳሳተ ቦታ ላይ ሄደህ ሳይሳካልህ ሲቀር እንዳትናደድ ነው።

ምንጊዜም ያንተን ዋጋ የሚያውቁ ብቻ ናቸው ክብርም አድናቆትም የሚሰጡህ ስለዚህ የተሳሳተ ቦታ ላይ አትገኝ!!

‪@agman21‬

4 months ago | [YT] | 1