EBC
‘ፋይዳ’ ለሌሎች ሀገሮች ያስገኘው ፋይዳ ************************* በአውሮፓውያኑ 2024 በዓለም ዙሪያ 5 ቢሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ዲጂታል መታወቂያ እንደያዙ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ዜጎች ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ፍትሐዊ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ በርካታ ሀገራት የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ደኅንነቱ የተረጋገጠ ልዩ መለያ በማቅረብ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለማግኘት እንዲሁም የሰነዶች ማጭበርበርን ለመከላከል የሚረዳው ዲጂታል መታወቂያ ቀልጣፋ ሥርዓት በመገንባት ረገድ ያለው ዓለም አቀፍ ተጠቃሚነት ምን ይመስላል የሚለውን ጥቂት እንመልከት። የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን በአፍሪካ እንደ ኢትዮጵያ (ፋይዳ)፣ ናይጄሪያ (ኤን አይ ኤን)፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ያሉ ሀገሮች የተሻለ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለመፍጠር ጥቅም ላይ እያዋሉት ይገኛሉ። ይህም ሥርዓቱ በአፍሪካ እየተስፋፋ መምጣቱን ያመላክታል። ኢስቶኒያ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የዲጂታል መታወቂያ ተደራሽነትን በቀዳሚነት በመምራት የምትታወቅ ነች። ‘ኢ አይ ዲ’ ተብሎ የሚጠራው የኢስቶኒያ ዲጂታል መታወቂያ ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በንፍታሌም እንግዳወርቅ ሙሉ መረጃውን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ:- www.ebc.et/Home/NewsDetails?NewsId=3516
3 days ago | [YT] | 360
EBC
‘ፋይዳ’ ለሌሎች ሀገሮች ያስገኘው ፋይዳ
*************************
በአውሮፓውያኑ 2024 በዓለም ዙሪያ 5 ቢሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ዲጂታል መታወቂያ እንደያዙ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ዜጎች ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ፍትሐዊ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ በርካታ ሀገራት የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ደኅንነቱ የተረጋገጠ ልዩ መለያ በማቅረብ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለማግኘት እንዲሁም የሰነዶች ማጭበርበርን ለመከላከል የሚረዳው ዲጂታል መታወቂያ ቀልጣፋ ሥርዓት በመገንባት ረገድ ያለው ዓለም አቀፍ ተጠቃሚነት ምን ይመስላል የሚለውን ጥቂት እንመልከት።
የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን በአፍሪካ እንደ ኢትዮጵያ (ፋይዳ)፣ ናይጄሪያ (ኤን አይ ኤን)፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ያሉ ሀገሮች የተሻለ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለመፍጠር ጥቅም ላይ እያዋሉት ይገኛሉ። ይህም ሥርዓቱ በአፍሪካ እየተስፋፋ መምጣቱን ያመላክታል።
ኢስቶኒያ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የዲጂታል መታወቂያ ተደራሽነትን በቀዳሚነት በመምራት የምትታወቅ ነች። ‘ኢ አይ ዲ’ ተብሎ የሚጠራው የኢስቶኒያ ዲጂታል መታወቂያ ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
ሙሉ መረጃውን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ:- www.ebc.et/Home/NewsDetails?NewsId=3516
3 days ago | [YT] | 360