Ze michael _Media ዘ ሚካኤል ሚዲያ
ህዳር 26/2018 #ፃድቁ_ሐብተ_ማርያም #ፆመ_ነብያት_12ኛ_ቀን ⭐በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሐብተ_ማርያም አመታዊ የእረፍት በአል መታሠቢያ እንኳን አደረሰን ⭐ኢትዮጲያዊዉ ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው #ፍሬ_ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት #ዮስቴና ትባላለች በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር⭐ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት ከማሕጸንሽ ደግ #የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 #አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች⭐ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር⭐የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው #በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል⭐ፃድቁ አባታችን በዝመታኘንትና በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት #አክሱም_ኢየሩሣሌም_ምድረ_ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል ⭐ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድን ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል ⭐ፃድቁ አባታችን #ማእጠንት ሲያጥኑ መንበረ ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር ፃድቁ በዚህ እለት የእረፍት በአላቸዉ ሲሆን ራሳቸዉ በገደሙት ገዳም ተቀብረዋል ⭐የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን #ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን "አሜን"⭐Uበዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን ረድኤትና በረከት #የአበዉ_ነብያት የከበረዉ #ቃል_ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️🥰🙏🏻🤲🏻
2 weeks ago | [YT] | 272
Ze michael _Media ዘ ሚካኤል ሚዲያ
ህዳር 26/2018 #ፃድቁ_ሐብተ_ማርያም
#ፆመ_ነብያት_12ኛ_ቀን
⭐በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሐብተ_ማርያም አመታዊ የእረፍት በአል መታሠቢያ እንኳን አደረሰን
⭐ኢትዮጲያዊዉ ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው #ፍሬ_ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት #ዮስቴና ትባላለች በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር
⭐ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት ከማሕጸንሽ ደግ #የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 #አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች
⭐ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር
⭐የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው #በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል
⭐ፃድቁ አባታችን በዝመታኘንትና በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት #አክሱም_ኢየሩሣሌም_ምድረ_ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል
⭐ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድን ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል
⭐ፃድቁ አባታችን #ማእጠንት ሲያጥኑ መንበረ ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር ፃድቁ በዚህ እለት የእረፍት በአላቸዉ ሲሆን ራሳቸዉ በገደሙት ገዳም ተቀብረዋል
⭐የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን #ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን "አሜን"
⭐Uበዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን ረድኤትና በረከት #የአበዉ_ነብያት የከበረዉ #ቃል_ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️🥰🙏🏻🤲🏻
2 weeks ago | [YT] | 272