Live Your Dream ህልምህን ኑረው
ፅኑ ስብዕና (resilient personality) ....የወርቅ ንፅህና በእሳት ተፈትኖ እንደሚለየው የሰው ልጅ ፅናትም በመከራ ውስጥ ነው ፍንትው ብሎ የሚወጣው። ለምሳሌ ሁለት ነጋዴዎች በተመሳሳይ ጊዜ ሊከስሩ ይችላሉ። ማንነታቸው ግን የሚወሰነው በደረሰባቸው ኪሳራ ሳይሆን ለኪሳራው በሰጡት ምላሽ ይሆናል። አንዱ ተስፋ ቆርጦ ድባቴ ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፣ ሌላው ደግሞ የተሻለ ለመስራት ሊነሳሳ ይችላል። ለችግሩ እጅ የሰጠው የመጀመሪያው ሰው ደካማ የፅናት ስብዕና ያላቸው ሰዎች ምሳሌ ሲሆን፣ በችግሩ ያልተበገረው ሁለተኛው ሰው ግን የፅኑ ሰብዕና አይነተኛ ምሳሌ ተደርጎ ሊወሳ የሚችል ነው። በዚህች አጭር ፅሁፍ የፅኑ ሰብዕና ምንነትና ጥቅሞች እንመለከታለን።ፅኑ ስብዕና ምንድን ነው?ፅኑ ስብዕና ማለት በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ተፈትኖ ማለፍ፣ ወድቆ የመነሳትና ችግሮችን ወደ ዕድል የመለወጥ ማንነት ነው። ለመሆኑ፣ የሰብዕናችን የፅናት ደረጃ ከፍ ያለ ወይ ዝቅ ያለ መሆኑን እንዴት እንለያያለን? ቀጥሎ 6 ነጥቦችን አነሳለሁ፦ሀ) ቀና አመለካከት (Optimism) ለነገሮች ያላቸው አመለካከት ቀና ነው። ሁሌም ችግሮች ጊዜአዊ እንደሆኑና "ሁሉ ነገር ለበጎ ነው" የሚል አስተሳሰብ አላቸው። ለ) ተጣጣፊነት (flexibility)በታላቅ አውሎነፋስ ውስጥ ብዙ ዛፎች ተገንድሰው ሲወድቁ የዘንባባ ዛፍ 🌴ግን ያንን አውሎ ነፋስ ዝቅ ብሎ ያሳልፍና መልሶ ቀና ይላል። ፅኑ ስብዕና ያላቸው ሰዎችም ልክ እንደ ዘንባባ ለተለያዩ ችግሮች የተለያዩ ምላሾች በመስጠት ያልፉታል፤ መናገር ሲገባቸው ይናገራሉ፣ ዝም ማለት ሲኖርባቸው አያወሩም፣ አንድን ችግር ችክ ብለው በተመሳሳይ መንገድ ለመፍታት አይዳክሩም። ሐ) አለማስመሰል (Genuine)ፅኑ ሰዎች ያልሆኑትን መስለው መታየት አይፈልጉም፤ ደካማ ጎናቸውን ለመሸፋፈን አይሯሯጡም። የሌላቸውን "አለኝ" ለማለት ለታይታ ሲሉ የተለያዩ ጭምብሎችን በማጥለቅ በማጥለቅና በማውለቅ አሳራቸውን አይበሉም። መ) ተማሪነት ለመንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ስኬትም ውድቀትም፣ ማጣትም ማግኘትም፣ ከፍታም ዝቅታም አንዳች ትምህርት ጥሎ ከማለፍ ውጪ አንዳች ጠባሳ አይተውባቸውም። ረ) በሚቆጣጠሯቸው ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግየፀና ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ማድረግ በሚችሉት ጉዳይ ላይ እንጂ ከእነርሱ ቁጥጥር ውጭ ባለ ነገር ላይ አቅማቸውን አይጨርሱም። ሰ) ጠንካራ ማሕበራዊ ቁርኝትፅኑ ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ያላቸው እንጂ ብቸኞች አይደሉም። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፅኑ ሰብእና ያላቸው ሰዎች ከሌላቸው አንፃር ሲታዩ ሲበዛ ስኬታማና የተሻለ የአዕምሮና የአካል ጤንነት ያላቸው ናቸው። ስለዚህ፣ ሁላችንም አይናችን ከሚገጥሙን ተግዶቶች ላይ አንስተን የመውጫ መንገዶችን ብንመለከት፣ ከማለቃቀስ ይልቅ የማንቀይረውን የሕይወትን ሰንጣቃ ብንቀበልና በሁሉ ብንደሰት የስኬት መንገድ ላይ መሆናችን አያጠያይቅምበቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን🎯🎯🎯🎯🎯🎯🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን SUBSCRIBE ያድርጉዩቱዩብ youtube.com/@Asfawwቴሌግራም t.me/Attitudeplcፌስቡክ www.facebook.com/attitudeaseቲክቶክ tiktok.com/@asfaw_motivation ለግል ለአስተያየትዎt.me/Attitudep
5 months ago | [YT] | 2
Live Your Dream ህልምህን ኑረው
ፅኑ ስብዕና (resilient personality)
....
የወርቅ ንፅህና በእሳት ተፈትኖ እንደሚለየው የሰው ልጅ ፅናትም በመከራ ውስጥ ነው ፍንትው ብሎ የሚወጣው። ለምሳሌ ሁለት ነጋዴዎች በተመሳሳይ ጊዜ ሊከስሩ ይችላሉ። ማንነታቸው ግን የሚወሰነው በደረሰባቸው ኪሳራ ሳይሆን ለኪሳራው በሰጡት ምላሽ ይሆናል። አንዱ ተስፋ ቆርጦ ድባቴ ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፣ ሌላው ደግሞ የተሻለ ለመስራት ሊነሳሳ ይችላል።
ለችግሩ እጅ የሰጠው የመጀመሪያው ሰው ደካማ የፅናት ስብዕና ያላቸው ሰዎች ምሳሌ ሲሆን፣ በችግሩ ያልተበገረው ሁለተኛው ሰው ግን የፅኑ ሰብዕና አይነተኛ ምሳሌ ተደርጎ ሊወሳ የሚችል ነው።
በዚህች አጭር ፅሁፍ የፅኑ ሰብዕና ምንነትና ጥቅሞች እንመለከታለን።
ፅኑ ስብዕና ምንድን ነው?
ፅኑ ስብዕና ማለት በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ተፈትኖ ማለፍ፣ ወድቆ የመነሳትና ችግሮችን ወደ ዕድል የመለወጥ ማንነት ነው። ለመሆኑ፣ የሰብዕናችን የፅናት ደረጃ ከፍ ያለ ወይ ዝቅ ያለ መሆኑን እንዴት እንለያያለን? ቀጥሎ 6 ነጥቦችን አነሳለሁ፦
ሀ) ቀና አመለካከት (Optimism)
ለነገሮች ያላቸው አመለካከት ቀና ነው። ሁሌም ችግሮች ጊዜአዊ እንደሆኑና "ሁሉ ነገር ለበጎ ነው" የሚል አስተሳሰብ አላቸው።
ለ) ተጣጣፊነት (flexibility)
በታላቅ አውሎነፋስ ውስጥ ብዙ ዛፎች ተገንድሰው ሲወድቁ የዘንባባ ዛፍ 🌴ግን ያንን አውሎ ነፋስ ዝቅ ብሎ ያሳልፍና መልሶ ቀና ይላል። ፅኑ ስብዕና ያላቸው ሰዎችም ልክ እንደ ዘንባባ ለተለያዩ ችግሮች የተለያዩ ምላሾች በመስጠት ያልፉታል፤ መናገር ሲገባቸው ይናገራሉ፣ ዝም ማለት ሲኖርባቸው አያወሩም፣ አንድን ችግር ችክ ብለው በተመሳሳይ መንገድ ለመፍታት አይዳክሩም።
ሐ) አለማስመሰል (Genuine)
ፅኑ ሰዎች ያልሆኑትን መስለው መታየት አይፈልጉም፤ ደካማ ጎናቸውን ለመሸፋፈን አይሯሯጡም። የሌላቸውን "አለኝ" ለማለት ለታይታ ሲሉ የተለያዩ ጭምብሎችን በማጥለቅ በማጥለቅና በማውለቅ አሳራቸውን አይበሉም።
መ) ተማሪነት
ለመንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ስኬትም ውድቀትም፣ ማጣትም ማግኘትም፣ ከፍታም ዝቅታም አንዳች ትምህርት ጥሎ ከማለፍ ውጪ አንዳች ጠባሳ አይተውባቸውም።
ረ) በሚቆጣጠሯቸው ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ
የፀና ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ማድረግ በሚችሉት ጉዳይ ላይ እንጂ ከእነርሱ ቁጥጥር ውጭ ባለ ነገር ላይ አቅማቸውን አይጨርሱም።
ሰ) ጠንካራ ማሕበራዊ ቁርኝት
ፅኑ ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ያላቸው እንጂ ብቸኞች አይደሉም።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፅኑ ሰብእና ያላቸው ሰዎች ከሌላቸው አንፃር ሲታዩ ሲበዛ ስኬታማና የተሻለ የአዕምሮና የአካል ጤንነት ያላቸው ናቸው።
ስለዚህ፣ ሁላችንም አይናችን ከሚገጥሙን ተግዶቶች ላይ አንስተን የመውጫ መንገዶችን ብንመለከት፣ ከማለቃቀስ ይልቅ የማንቀይረውን የሕይወትን ሰንጣቃ ብንቀበልና በሁሉ ብንደሰት የስኬት መንገድ ላይ መሆናችን አያጠያይቅም
በቅንነት ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯
🔺🔻ሊንኩን አንዴ ብቻ በመጫን
SUBSCRIBE ያድርጉ
ዩቱዩብ youtube.com/@Asfaww
ቴሌግራም t.me/Attitudeplc
ፌስቡክ www.facebook.com/attitudease
ቲክቶክ tiktok.com/@asfaw_motivation
ለግል ለአስተያየትዎ
t.me/Attitudep
5 months ago | [YT] | 2