Mekdse Tube መቅደስ ቲዩብ


             💭 እውነተኛ ጾም

"ከምግብና ከመጠጥ ያልተቆጠበ ሰው ለክርስቶስ ሕይወቱን መስጠት እንደሚከብደው ግልጽ ነው። ድፍረት ያላት ነፍስ ቀጣይነት ባለው መንፈሳዊ ልምምድ ራስን መግዛት ለሥጋ ፈቃድ የሚያስፈልገውን ምግብና መጠጥ በመተው የሥጋ ፈቃድን ድል መንሳትንና የሥጋ ፈቃድ ለነፍስ ፈቃድ ማስገዛት ይቻላታል። ይህች ነፍስ የሚመጣባትን ከባድ ነገር ሁሉ እስራትም ቢሆን ግርፋትም ቢሆን መቋቋም ይቻላታል።

በእግዚአብሔርና በተጋድሎ የፀኑ ሰዎች ሥጋቸውን እስከሞት ድረስ አሳልፈው በመስጠት ሰማዕትነትን መቀበል ይቻላቸዋል። በአካላዊ ስሜት ብቻ ሳይሆን ከመጾም በሚገኘው መንፈሳዊ ጥቅም ሰማዕታት ጾምን የስልጠና ትምህርት ቤት አድርገውታል። የጾም ቀናት የሚጠቅሙን ለመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ በኃጢአታችን እንድንፀፀት እና ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ብቻ ሳይሆን ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ያለንን ፍቅር ለመግለጽም ይጠቅሙናል።

ሰማዕታት የጾምን ፣ የጸሎትን እና የብሕትውናን ሕይወት የኖሩ ናቸው። ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው "የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው በዚህችም ዓለም የሚጠቅሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ የዚህች ዓለም መልክ አላፊ ነው"1ኛ ቆሮ 7፥34፡፡ እውነተኛ ጾም አንድን ሰው ራሱን እንዴት መቆጣጠር እንዳለበት ያሰለጥነዋል። ቀሪ ሕይወቱን እንዴት መኖር እንዳለበት እንዲያውቅ ያደርገዋል። ራስን መቆጣጠር ለቅድስና ሕይወት መሠረት ነው። ጾም ቅጣት ሳይሆን ደስታ ነው።"

             የሕይወት መዓዛ መጽሐፍ
                አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ


የሣምንቱ መልእክት

<ሰንበት 'ቅድስት'ን አስቀድሰን እንቀደስባት!>

1 year ago | [YT] | 5