EBC
የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየታደሰ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ******** ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እንብርት የሚገኘውን የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያንን የሕንጻ እድሳት ሥራ ጎብኝተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ከዓድዋ ታሪክ ጋር በእጅጉ የተሣሠረ ታሪክ አለው፤ በዚህም የተነሣ በሁለተኛው የፋሽስት ወረራ ጊዜ እንደ ጦር ወንጀለኛ ተቆጥሮ ዋጋ ከፍሏል ብለዋል፡፡ በእሳት እስከ መቃጠልና ጥቁር ቀለም እስከ መቀባትም ደርሷል ሲሉም አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል። ቤተ ክርስቲያኑ ደረጃውን በጠበቀና ልዩ ልዩ ባለሙያዎችን ባሳተፈ መልኩ እየታደሰ መሆኑን መመልከታቸውንም አስታውቀዋል። የዓድዋ ሙዚየም በአካባቢው መገንባቱ፣ ለዳግማዊ ምኒልክ ዐደባባይ ጥገና መደረጉ እና የመመልከቻ አምፊ መሠራቱ የአካባቢውን የቱሪዝም ፍሰት ከፍ አድርጎታል ብለዋል፡፡ አካባቢው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ማዕከል እየሆነም ነው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡ አሁን የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያን ሕንጻና ግቢ ታሪካዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ መታደሱ ደግሞ፣ ታሪኩን የተሟላ እንዲሆን እንደሚያደርገው ገልጸዋል። የሕንጻው የአሠራር ጥበብ፣ የሥዕሎቹ ጥበባዊ ከፍታ፣ የብረት ሥራዎች የጥበበ ዕድ እና የጥራት ደረጃ እንዲሁም የቅርሶቹ የላቀ ዋጋ እጅግ አስደናቂ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብለዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ እና የአካባቢው ጥገና አሁን ከጀመርናቸው የከተማ ማዘመን ሥራዎች፣ የቱሪስት መዳረሻዎች እና የቅርስ አጠባበቅ ደረጃዎች ጋር ተጣጥሞ እንዲሠራ፣ የሚመለከታቸው ሁሉ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ አደራ እላለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። #ebcdotstream #EBC #Ethiopia
4 days ago | [YT] | 270
EBC
የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየታደሰ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ
********
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እንብርት የሚገኘውን የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያንን የሕንጻ እድሳት ሥራ ጎብኝተናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ ከዓድዋ ታሪክ ጋር በእጅጉ የተሣሠረ ታሪክ አለው፤ በዚህም የተነሣ በሁለተኛው የፋሽስት ወረራ ጊዜ እንደ ጦር ወንጀለኛ ተቆጥሮ ዋጋ ከፍሏል ብለዋል፡፡ በእሳት እስከ መቃጠልና ጥቁር ቀለም እስከ መቀባትም ደርሷል ሲሉም አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ቤተ ክርስቲያኑ ደረጃውን በጠበቀና ልዩ ልዩ ባለሙያዎችን ባሳተፈ መልኩ እየታደሰ መሆኑን መመልከታቸውንም አስታውቀዋል።
የዓድዋ ሙዚየም በአካባቢው መገንባቱ፣ ለዳግማዊ ምኒልክ ዐደባባይ ጥገና መደረጉ እና የመመልከቻ አምፊ መሠራቱ የአካባቢውን የቱሪዝም ፍሰት ከፍ አድርጎታል ብለዋል፡፡ አካባቢው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ማዕከል እየሆነም ነው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
አሁን የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አራዳ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያን ሕንጻና ግቢ ታሪካዊና ዘመናዊ በሆነ መንገድ መታደሱ ደግሞ፣ ታሪኩን የተሟላ እንዲሆን እንደሚያደርገው ገልጸዋል።
የሕንጻው የአሠራር ጥበብ፣ የሥዕሎቹ ጥበባዊ ከፍታ፣ የብረት ሥራዎች የጥበበ ዕድ እና የጥራት ደረጃ እንዲሁም የቅርሶቹ የላቀ ዋጋ እጅግ አስደናቂ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብለዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኑ እና የአካባቢው ጥገና አሁን ከጀመርናቸው የከተማ ማዘመን ሥራዎች፣ የቱሪስት መዳረሻዎች እና የቅርስ አጠባበቅ ደረጃዎች ጋር ተጣጥሞ እንዲሠራ፣ የሚመለከታቸው ሁሉ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ አደራ እላለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ebcdotstream #EBC #Ethiopia
4 days ago | [YT] | 270