Kidus ዘ ተዋሕዶ

Kidus Zetewahdo is a spiritual medium that mainly helps Oriental Orthodox Christians to persevere in their faith and know their faith and Live their faith. Kidus Zetewahdo has been working hard on raising awareness on various spiritual issues for the past 3 years. This medium is popular with many Ethiopian Orthodox Christians and has led to many life changes.


Kidus ዘ ተዋሕዶ

የማኅበራችንን 10ኛ አመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ሙሉ መርሐግብር እየገባችሁ ተከታተሉ!!!

9 months ago | [YT] | 0

Kidus ዘ ተዋሕዶ

እንዳያመልጣችሁ🥰🙏

11 months ago | [YT] | 0

Kidus ዘ ተዋሕዶ

እንኳን ለእናታችን ለእግዝእትነ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ የምወዳችሁ❤

1 year ago | [YT] | 97

Kidus ዘ ተዋሕዶ

የምንናፍቀው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመቱ ህዳር 12 ደረሰ እንዴት እንደጓጓው !
ቅዱስ ሚካኤልን እንዴት እንደምወደው በቃላት መግለፅ ይከብደኛል። እስቲ እንደእኔ የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ ረድኤትና በረከቱ ያልተለያችሁ የታላችሁ?🥰

የእናንተው አክባሪ - የቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ
[ ቅዱስ ዘተዋሕዶ ]

1 year ago | [YT] | 87

Kidus ዘ ተዋሕዶ

                           †                           

      [   🕊 ድንግል ሆይ ፦  🕊    ]  

🌼▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🌼

🌹 ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ 🌹

🕊

❝ ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር ❞


[ የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው ፤ እነሆ የተወደደ [ መልካም ] ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ [ በዕቅፍሽ ] እንዲጠጋ [ እንዲደገፍ ፣ እንዲንተራስ ] በርሱ ዐማጽኚ፡፡ ]

[ አባ ጽጌ ድንግል [ ማህሌተ ጽጌ ] ]

🕊

" ሱላማጢስ ሆይ ተመለሺ ! " [መሓ. ፯:፩]

†                       †                      †
💖                    🕊                   💖

1 year ago | [YT] | 107

Kidus ዘ ተዋሕዶ

እመቤታችን እና እመቤታቸው

ከምናቃቸው ሥዕለ ማርያም ምስለ ፍቁር ወልዳ አንዳንዶቹ ሥዕሎች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የሚወክሉ አይደሉም እንደውም በወላዲተ አምላክ ተመሳሳይ የምትሳል ክርስቲያን ባልሆኑ አህዛብ ዘንድ እመቤታችን የሚሏት እራሷን የቻለች ሌላ ሴት ናት።

ክርስቲያኖች የአምላክን እናት አመቤታችን እናታችን እንደምንል ሁሉ። ከክርስትና ውጪ ያሉ አህዛብም እመቤታችን የሚሏት ሴት አለች እሷን ሥዕሏን ይስሉላታል፣ ይሰግዱላታል፣ ያመሰግኗታል።
ይህ ልማድ ከትንጥ ጀምሮ የነበረ ነበር

እውነተኛው ክርስቶስ እንዳለ ሃሳዊው ክርስቶስ አለ... እውነተኛው ክርስቶስ የወለደችው ወላዲተ አምላክ እንዳለች ሁሉ ደግሞ የሃሳዊው ክርስቶስ እናትም አለች... አህዛብ ይህቺን የሃሳዊውን ክርስቶስ እናት ይወዷታል፣ ያከብሯታል ፣ ያመሰግኑአታል እናታችን ይሏታል

አባቶቻችን የአምላክን እናት እና የሃሳዊውን ክርስቶስ እናት ልዩነት ጠንቅቀው የተረዱ ስለነበር ሥዕል ሲስሉ ወላዲተ አምላክ ሥዕሉ ወስጥ ግዴታ መኖር የነበረባቸው ገጽታዎች ነበሩ። ከዛ የወጣ ወይም የተጨመሩ ነገሮች ያሏቸውን ሥዕሎች ለጸሎት እና ለአምልኮ አይጠቀሙም ነበር ምክንያቱም የሃሳዊውን ክርስቶስ እናትም በተመሳሳይ ሁኔታ ተስላ ጥቂት ልዩነት ብቻ ተደርጎባት እንደምትቀርብ ስለሚያውቁ ነው

አሁን ግን ግዜው ተቀይሮ የ የሃሳዊውን ክርስቶስ እናት ሥዕል በቤትክርቲያናችን ወስጥ ባሉ መናፍቃን ወደ ቤተመቅደስ ሆን ተብሎ እንዲገባ ሥዕሏ እንዲለመድ ትክክለኛውን የድሮ አባቶቻችን የሚጠቀሙበትን ሥዕለ ማርያም ደግሞ ተገፍቶ እንዲወጣ ክርስቲያኑም ህሊና እንዲረሳ ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል

አብዛኛው ክርስቲያን ሁሉንም ህጻን ልጅ የያዘች ሴት ምስል ሲያይ
እመቤታችን ነው የሚለው። ከየት መጣ ማን ሣለው ወዘተ አይጠይቅም.... ያገኘነው ሥዕል እንሳለማለን... ያገኘነው ሥዕል እንሰግዳለን... ችግሩ ግን ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ ከውጪ ሃገር ተሥለው የሚመጡ ስዕሎች የአምላክን እናት ለመሳል ፈልገው በገባቸው መጠን የሳሉት ሳይሆን የራሳቸውን እመቤታችን የሚሏትን ከጥንት ጀምሮ የሚያመልኳትን ሴት ምስል ነው ስለው የሚያሰራጩት... ሲጀመር የአምላክን እናት አያውቋትን እሷንም መሳል ፈጽመው አይፈልጉም

እኛ ግን በየዋህነት እና ባለማወቅ ያገኘነው ሥዕል እንሰግዳለን ግን አለማወቃችን ጉዳት ላይ ጣለን እንጂ አላስጠቀመንም ስለዚህ ለጽሎት እና ለአምልኮት የምንጠቀምባቸውን ስዕሎች በደንብ መመርመር ፣ መፈተሽ፣ ማስተካከል ይኖርብናል።

1 year ago | [YT] | 9

Kidus ዘ ተዋሕዶ

ስለሰው ልጆች ሁሉ መዳን በቀራንዮ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ኃያል ፍቅሩን ለገለጠልን የአብ የባሕርይ ልጅ ለሆነው በግርማው ቀኝ ለተቀመጠው ዳግም ለፍርድ ለሚመጣው መቶም በሰማያት ባዘጋጀልን ዘለዓለማዊ ስፍራ ለሚወስደን ለኃያሉ ጌታችን እና አምላካችን እና ስለ እኛ ዕለት ዕለት ለሚጨነቀው አባታችን ብርሃነ ዓለም መድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ❤✝️

1 year ago | [YT] | 95

Kidus ዘ ተዋሕዶ

ከእኛ በላይ ስለእኛ የሚጨነቅ የሚያስብ ድንቅ አባት አለን✝️ ተመስገን🙏

1 year ago | [YT] | 58

Kidus ዘ ተዋሕዶ

ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የምታስቡ ሁሌ ይህንን አስታውሱ!!!

በዕለት ውስጥ አንድ ሳታደርጉት የማታልፉት ነገር ምንድን ነው? ለምሳሌ ስልክ🤳 መጠቀም እንበል ስልክን ዕለት ዕለት ሳንጎበኘው አናልፍም። ስለዚህ ዕለት ዕለት ከስልካችን🤳 ጋር ሳንገናኝ ፤ ከሰዎች ጋር ሳንገናኝ እንደማንውለው የፍጥረታት ሁሉ ባለቤት ኃያሉ አምላካችን እኛ ስንጠራው "አባታችን" እርሱ ሲጠራን "ልጆቼ " የሚለንን አምላካችንን 24 ሰዓት የሰጠንን ጌታ ቢያንስ 1 ሰዓት ከአባታችን ጋር በፀሎት እናሳልፍ! በፀሎት እናሳልፍ ማለት የፀሎት መፃሕፍትን ዝም ብሎ አብዝቶ ማንበብ ሳይሆን በትንሹ አባታችን ሆይ እያልን መዝሙረ ዳዊትን ከልባችን እየፀለይን የዕለቱን ውዳሴ ማርያም እያደረስን ከልባችን የሚሰማንን በፀሎት ለአባታችን ለእግዚአብሔር እንናገር! ከፊታችን ያለው "አባታችን" ነውና🥰✝️🙏

አንድ ምድራዊ ንጉስ ቢቀጥረን ምን ይሰማናል? የነገሥታት ንጉሥ የሆነው አባታችን ሁሌ ዕለት ዕለት ቀጥሮ እንድናወራው ይጠብቀናል! እርሱን ለማውራት እንዴት አንጓጓም?

አሳ ከውሀ ፣ እፅዋት ከአፈር ተለይተው ሕይወት እንደሌላቸው እኛም ከሕይወት ውሀ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእውነተኛ ግንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ተለይተን ሕይወት የለንም! የእርሱ አካል ብልቶች ነንና🥰 (ሮሜ 12÷4-5) (1ቆሮ 12÷12-27)

"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለዕለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል"
[ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ]

" የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው "
[ ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ ]

በተጨማሪም እነዚህን መፃህፍት አንብቧቸው👇
[ ተግባራዊ ክርስትና ]
[ ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና መንፈሳዊ አገልግሎቱ ]

1 year ago | [YT] | 34

Kidus ዘ ተዋሕዶ

ስንቶቻችሁ የነገን ብርሀን በማየታችሁ ፈጣሪን ታመሰግናላችሁ?

ብዙዎች የነገን ብርሀን ማየታቸውን ተኝተው መነሳታቸውን እንደቀላል ያዩታል ነገር ግን ፈጣን እንደ ፃድቁ እዮብ ለማመስገን በቂ ነው ብዙዎች የነገዋን ብርሀን ለማየት እየናፈቁ ብዙዎች በተለያየ ምክንያት አልፈዋል እኛም የነገዋን ብርሀን እንደምናይ ምንም ማረጋገጫ የለንም የነገን የሚያውቅ ሕያው አምላካችን ነውና ነገር ግን በሰጠን ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን እናመስግን የነገዋ ብርሀን የነገዋ ቀን በምንም ዋጋ የምትገመት አይደለችም የማይተኛ አምላካችንን አምነን ስንተኛ ልባችን እንዲመታ የደም ዝውውራችን እንዳይቆም እስትንፋሳችንን የሚቆጣጠርልን እንዲሁም በቸርነቱ ጠብቆ የነገዋን ብርሀን ስለሚያሳየን እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይድረሰው🙏 አሜን🙏

1 year ago | [YT] | 3