Welcome to TM Zone!
Your go-to destination for
At TM Zone, we bring you like weekly videos, tutorials, reactions, or discussionsyou’ve come to the right place!
Don’t forget to like, subscribe, and hit the bell icon so you never miss an update.
Join the TM Zone community today!
TM Zone
Tm
3 months ago | [YT] | 0
View 0 replies
TM Zone
You have to watch this video
4 months ago | [YT] | 0
View 0 replies
TM Zone
Singer Tigist Bekele with her husband and children. Where do you love her? 🥰l
4 months ago | [YT] | 1
View 0 replies
TM Zone
FOR A HAPPY LIFE GIVE THE MONEY TO YOUR WIFE”
4 months ago | [YT] | 0
View 0 replies
TM Zone
ቀ.ኃ.ሰ በአባይ ግድብ ዙሪያ የተናገሩት አሳዛኝ ማሰታወሻ ‼️
" እኛ አባይን እንገድብ ብንል አቅም የለንም : የውጭ ሀገራት ደግሞ አባይን ለመገደብ እርዱን ብንል ግብጥን ( ግብፅን ) ላለማሰቀየም ፈቃደኛ አይሆኑም :: ቀጣዪ ትውልድ ግን በራሱ ንዋይ ( ገንዘብ ) ይገነባዋል :;
ጥናቱ በክብር ይቀመጥ " !!
ቀዳማዊ ሀይለሰላሴ. 💚💛❤️
5 months ago | [YT] | 1
View 0 replies
TM Zone
ናሳ የሚለው ቃል የተወሰደው ከአማርኛ መሆኑን ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?!
አሜሪካዊው ሳይንቲስት ዶ/ር ሁይ ደራይደን ወይም ጓደኞቹ እንደሚጠሩት ደራ በሀገራችን አቆጣጠር በ1947 ዓ/ም ኢትዮጵያን ለመጎብኘት መጥቶ ንጉሱን ማግኘት ፈልጎ ነበር እና እሳቸው አናሳ ማህበረሰብን አያገኙም ብለው መለሱት። ነገሩ ትንሽ ከንክኖት ወደሀገሩ የተመለሰው ደራ ከሁለት አመታት በኋላ በወቅቱ የነበሩት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአሜሪካውያን ኩራት የሚሆን የምርምር ተቋም ማቋቋም አለብን አንተ ደግሞ ተቋሙን ምራው ብለው ሲያማክሩት እሺ አለ። ኋላ ላይም ተቋሙን ምን እንበለው የሚለው ነገር ሲመጣ የደራ አእምሮ ላይ ብልጭ ያለችው አናሳ የምትለው ቃል ነበረች። ከብዙ ክርክርና ማሳመን በኋላም እንዳይነቃብን በማለት " አ "ን ገድፈው " ናሳ " ን መጠሪያቸው አደረጉት።
አለም የኛ የሆነን ነገር ሁሉ የሚፈልግበት ሚስጥር የገባኝ በሰባት አመት የናሳ ቆይታዬ ነው። በዚህ የሰባት አመት ቆይታዬም ሁለት ጊዜ ጨረቃ ላይ ወጥቼ ኢትዮጵያውያንን የመመልከት እድልም ነበረኝ። በእውነት በተለይ አብዛኛው በሚባል ደረጃ ወጣቶች ማታ ማታ ማንም አያየንም በማለት ጥንድ ጥንድ እየሆኑ የሚያደርጉት ነገር ይገርመኝ ነበር።
5 months ago | [YT] | 1
View 0 replies
TM Zone
የምንሊክን አገር ዘርፈው ሊወጡ ሲል በምኒልክ ብርጌድ ጋማ ተብለው ከዘረፉት እቃ ጋር ገቢ የተደረጉ የሊጥ ሌ*ቦች... ‼️
4 years ago | [YT] | 5
View 0 replies
TM Zone
ማስተባበያሽን ዋጭው.....
የስዊስ ዜግነት ያላት ዶክተር እሌኒ ገብረመድህን ስሜ የትግሬ ስለሚመስል ላፍቶ የሚገኘው ቤቴ ላይ ፍተሻ ተደረገበት ብላ ከሦስት ቀናት በፊት ብስጭቷን ትዊተር ገጿ ላይ ገልፃ ነበር ። ከትላንት በስቲያ ደግሞ በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ የሚመራው እና ዶክተር እሌኒም በአባልነት የምትሳተፍበት Peace and Development Center International (PDCI) የተባለው ድርጅት አዘጋጅነት በኢትዮጵያ መንግሥት ለውጥ እና ቀጣዩ መንግሥት የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ላይ የኦንላይን ውይይት ካደረጉት አንዷ ነበረች ።
ሕዝቡ እንዲታደምበት ባልተደረገ በድብቅ ያካሄዱት የሴራ ውይይት በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ ካናዳዊው የታሪክ ተመራማሪው ጄፍ ፒርስ ይፋ ተደርጎ ሕዝቡ እንኳንም አወቅንሽ በማለት አይንሽን ላፈር ሲላት ደግሞ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ጋብዞኝ እንጂ ስለስብሰባው የማውቀው ነገር አልነበረም ፣ ሕገወጥ በሆነ መልኩ የሚደረግ የመንግሥት ለውጥን አልደግፍም በማለት ከደቂቃዎች በፊት በትዊተር ገጿ ለማስተባበል ሞክራለች ።
እሷ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት አባል ሆና እያለ በኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ከተባለ አካል ጋር ያለ መንግሥት እውቅና ውይይት ማድረግ ወንጀል መሆኑን ለማወቅ እድሜና እውቀቷ አይፈቅድላት ይሆን?
የሽግግር መንግሥት ተወካይ ነኝ ላሉት አምባሳደር ብርሃኔ በቀጣይ መስራት ስለሚገባው የኢኮኖሚ ግንባታ መርህ የሰጠችው ምክር አሁን ያለው ሕጋዊ መንግሥት እና መሪ እንደሚወገድ ታሳቢ በማድረግ አይደለምን ?
ሕወሓትን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ዳግም ለመጫን እየሰራች ቤቴ ተፋተሸ ብላ ማልቀሷ እጅግ ያሳፍራል። የኢትዮጵያ ደህንነት መስሪያ ቤት የግለሰቧን አሰላለፍ ቀድሞ ማወቁ ሊያስመሰግነው ይገባል ። ማስተባበያሽን ዋጪው ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት አባልነት በአስቸኳይ እንዲያስወግዷት ለኢትዮጵያ ህልውና ሕይወታቸውን እየሰጡ ባሉ መሥዋዕቶች ስም በአክብሮት እጠይቃለሁ ።
4 years ago | [YT] | 2
View 0 replies
TM Zone
#GMN | ከአሁን በኋላ አሜሪካ በአፍሪካ አታስፈልግም
____________________________________
በአሜሪካ የሚመራው የኢምፔሪያሊስት ሀይል ኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ወረራ አጥብቄ አወግዛለሁ ሲል ዓለም አቀፉ የጥቁር ህብረት ለሰላም ተቋም አስታወቀ።
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ትልቁ የጥቁሮች መብት ተሟጋች ተቋም Black Alliance for Peace /BAP/ ትላንት በመላው ዓለም የተደረገውን የኢትዮጵያዊያን ሰልፍ አስመልክቶ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ከአሁን በኋላ አሜሪካ በአፍሪካ አታስፈልግም No More U.S. in Africa በማለት ገልጿል።
“እኛ የጥቁር ህብረት ለሰላም አባላት በአሜሪካ የሚመራው ኢምፔሪያሊስት ሀይል በኢትዮጵያ እና በጎረቤቶቿ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና በሌሎችም ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት ያለማመንታት እንቃወማለን” ያለው መግለጫው የአሜሪካ-አውሮፓ ህብረት-ኔቶ የአገዛዝ ዘንግ በመጨረሻም አፍሪካ ውስጥ የሞት አልጋውን በፓን አፍሪካውያን እጅ ያገኛል ሲል ገልጿል።
የተቋሙን ሙሉ መግለጫ እዚህ ያገኛሉ፦ blackallianceforpeace.com/bapstatements/nomoreusin…
4 years ago | [YT] | 4
View 0 replies
TM Zone
መጠናናት
(በእውቀቱ ስዩም)
አንድ በድሜና በምጣኔ ሀብት የሚበልጠኝ ወዳጅ ነበረኝ ፤ አንዳንዴ በግድግዳ ስልክ ደውየ “ ለጥብቅ ጉዳይ ስለምፈልግህ እንገናኝ” ስለው " ጋብዘኝ፥ ሊፍት ስጠኝ፥ ገንዘብ አበድረኝ፥ ዋስ ሁነኝ፥ ሽማግሌ ሆነኝ አትበለኝ እንጂ ለጥብቅም ሆነ ለላላ ጉዳይ ልታገኘኝ ትችላለህ ” ብሎ ይመልስልኝ ነበር ፤ እና እኔንም ፖለቲካ ጻፍ አትበሉኝ እንጂ ፌስቡክ ላይ ለማንዣበብ ቃል እገባለሁ::
“እስቲ አንዴ እንደማመጥ !” አለ የዳምጠው ሹፌር፤
ድሮ ከትዳር በፊት መጠናናት የሚባል ነገር ነበር፤ አባቶቻችን ውሃ አጣጫቸውን ሲያጠኑ “ ሙሽራዋ የማን ልጅ ናት? ዶሮ መበለት ትችላለች? ቤተእግዚሀር ትስማለች ?” በሚሉ ጉዳዮች ላይ ብቻ ይወሰኑ ነበር፤ የሙሽራዋ መልክ ራሱ በጫጉላው ቀን ብቻ የሚገለጥ “Top secret ነበር :: ዛሬ ከትዳር ቀርቶ ከድርያ በፊት ያለው መጠናናት እጅግ በጣም ተራቋል፤
ባለፈው ባለቀ ሰአት ትዳር ውል ብሎብኝ እዚህ ጎረቤት አገር ካለች ቀንበጥ ጋራ እንዴት ነሽ እንዴት ነህ ስንባባል ባጀን:: ባንድ ምሽት ድንገት “ ከወገብህ በታች አወላልቀህ ፎቶ ተነስተህ ላክልኝ አለችኝ” ፤ ተገረምሁ፤ ብሎም ደነገጥሁ፤ ግን ስሜቴን ዋጥ አድርጌ ” ከወገቤ በታች ያለው ጓዝ ባንድ የሞባይል ፎቶ የሚወሰን አይደለም፤ ራሱን የቻለ የናሺናል ጆግራፊ ዶከመንተሪ የሚፈልግ ፕሮጀክት ነው፤ ባይሆን ከወገቤ በላይ አወላልቄ ልላካልሽና ገምግሚኝ” አልኳት::
በስንት ልምምጥ ተስማማች ::
አምሳ ፎቶ ተነስቼ፤ አርባ ዘጠኙን ደምስሼ አንዱን ሰደድኩላት::
“ ሲክስ ፓክ አለኝ ብለኸኝ ነበርኮ”
“ ከራት በፊት ሲክስ ፓክ ነበረኝ፤ ከራት በሁዋላ ሲክስ ባግ ሆኗል “ አልኳት::
“No way ! ሆድህ ትልቅ ያፈር ገንፎ ነው እሚመስለው “
“ ደረቴ ላይ ብታተኩሪ ደስ ይለኛል ”
“ ደሞ ሁለት እምብርት ነው ያለህ እንዴ ? ”
‘አንደኛው ትርፍ አንጀት ያስወጣሁበት ጠባሳ ነው ! ምናለ ደረቴ ላይ ብናተኩር”
“ ኦኬ! ደረትህ ከየት ነው እሚጀምረው?”
ይሄንን አሳዛኝ ጭውውት ለቀጣዩ ላሳድርና ሌላ ገጠመኝ ላውጋችሁ::
በቀደም ዲሲ ኡበር ታክሲ እየነዳሁ አለምአቀፉን ማህበረሰብ ሳገለግል አንዱ አበሻ ተሳፈረ፤ ሰውየውን የት ነው የማውቀው እያልሁ እያሰበኩ ፊቱን ለጥቂት ደቂቃ አጠናሁት፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የሸግግር መንግስት ለመመስረት ተሰባስበው ፎቶ ከተነሱት አንዱ ወጣት መሆኑን ተገነዘብኩ ፤ ሰውየው ከሁዋላ ወንበር ለጠጥ ብሎ ተቀመጠ፤ አቀማመጡን በማየት ብቻ ለንግስና የተፈጠረ መሆኑን መገመት ይቻላል :: ረጅም ሎጋ ከመሆኑ የተነሳ በቂጡ የቆመ ነው እሚመስለው፤ ጭራሽ በwhite house በዋይታ-ውስ በኩል ስናልፍ እጁን በመስኮት አውጥቶ አውለበለበ :: ለአሜሪካ አቻው ሰላምታ ማቅረቡ መሰለኝ :: ሰፈሩ ሲደርስ ቀልጠፍ ብየ ወረድሁና በሩን እንደ ጋሻጃግሬ ከፍቼ “ እንግዲህ በመንግስትህ አትርሳኝ “ ብየ አሰናበትኩት:: ቤቴ ደርሼ መኪናየን ስፈትሽ ሰውየው ሳምሶናይቱን ጥሎ መሄዱን ተረዳሁ ፤ ቦርሳውን ከፍቶ የማየት አሳብ መጥቶብኝ ትንሽ ከራሴ ጋራ ታገልኩ፤ ኢትዮጵያን እጣ ፈንታ የሚወስን ነገር በጄ ገብቶ ቢሆንስ ? የመጣው ይምጣ! ሳምሶናይቱን ስከፍተው ያገኘሁት ገረመኝ- አንድ ፌስታል ድርቆሸ፥ ስድስት ብልቃት ሚጥሚጣ; አንድ ፌስታል ኤልሳ ቆሎ፤ፌርሙስ የሚያክል የብብት ፊሊት… ከስር አንድ ወረቀት አየሁ፤ አሃ! ይሄ የሽግግር መንግስቱ ሰነድ ፥ አለዚያም የአዲሱ ህገ -መንግስት ረቂቅ መሆን አለበት ብየ ገለጥ አደረኩት፤ የኪራይ ቤት ውል መሆኑን ሳውቅ ግን እጢየ ዱብ አለ፤ እጢየን ወደ ነበረበት ሰቅየ ውሉን በጥሞና ማንበብ ጀመርኩ ፤ No shoe inside the house ይላል የመጀመርያው አንቀጽ፤
ከጥቂት ሰአታት በሁዋላ ሰውየው ሳምሶናይቱን ሊቀበለኝ ሲመጣ “ ዠለስ! የሽግግር መንግስት ነው ፤ወይስ የችግር መንግስት ያሰብክልን? እስቲ ኢትዮጵያን ከመግዛትህ በፊት መጀመርያ ቤት ግዛ “ ብየ ገሰጽኩት !
ፖለቲካ አልጽፍም ያልኩትን ከምኔው ዘነጋሁት በሞቴ !
4 years ago | [YT] | 2
View 0 replies
Load more