ይህ YouTube ቻናል በጤና በምርምርና በአዳዲስ የህክምና ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ወቅታዊ መረጃዎችን ዜናዎችንና ትንታኔዎችን ያቀርብልዎታል። ቻናላችንን ሰብስክራይብ ላይክና ሸር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፤ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ። በተጨማሪ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች (Telegram & Facebook) ይከታተሉ።
በዕረፍት ጊዜዎ ይጎብኙን!!
This YouTube channel brings you the latest health related news and analysis, researches, new medical technologies and updates. Subscribe, Like and Share our channel. Share with your friends and families. Visit us on your #HealthBreak!!
Follow us on other media options (Telegram & Facebook).
Facebook Page: www.facebook.com/profile.php?id=61550568503451
Telegram: t.me/HealthBreak
Health Break የጤና ዕረፍት
የጭንቅላት ወባ (Cerebral Malaria🧠) ምንድነው?
የጭንቅላት ወባ የሚባለው፣ የወባ በሽታ አምጪው ተህዋሲያን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአእምሮን ስራ የሚያዛባና ለህልፈት ሊያደርስ የሚችል አደገኛ በሽታ ነው። ብዙዎቻችን ወባን እንደ ተራ ትኩሳት እናያለን። ነገር ግን ወባ ለብዙዎች የድህነት በሽታ (disease of the poor) በመባል የሚታወቅ በሽታ ሲሆን በተለይም "#የጭንቅላት_ወባ" የሚባለው ደረጃ ላይ ሲደርስ ነገሩ የህይወትና የሞት ጉዳይ ይሆናል። የጭንቅላት ወባ በፍጥነት ካልታከመ በስተቀር 100% የመግደል አቅም ያለው በሽታ ነው፡፡
1. መንስኤው ምንድነው (What is the Cause)?
የጭንቅላት ወባን የሚያመጣው ፕላዝሞዲየም ፋልሲፓረም (Plasmodium falciparum) የተሰኘው የወባ ዝርያ ነው። ይህ ዝርያ ከሌሎቹ የወባ አይነቶች ለየት የሚያደርገው በጣም አደገኛና በሰውነት ውስጥ በፍጥነትና በብዛት በመሰራጨት በተለይም #ቀይ የደም ሴሎችን የማውደም ብቃት ያለው መሆኑ ነው።
2. በጭንቅላታችን ውስጥ ምን ይፈጠራል?
ከሌሎች የወባ ዝርያዎች በተለየ ሁኔታ እነዚህ ተህዋሲያን የደማችንን ቀይ ሴሎች ከወረሩ በኋላ የሴሎቹን ውጫዊ ክፍል "ተለጣፊ" ያደርጉታል። በመሆኑም የደም ህዋሶችን እንደ ሙጫ የሚያጣብቁ እንዲሆኑ በማድረግ በቀጫጭን የደም ቧንቧዎች (Capillaries) ውስጥ እንዲጣበቁ (Sequestered) እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ይህ መጣበቅ (Sequestration) የሚከሰተው በጭንቅላት ቧንቧዎች (brain capillaries) ወስጥ ሊሆን ይችላል፡፡
✅የደም የቧንቧ መዘጋት: ከላይ እንደተጠቀሰው እነዚህ ተለጣፊ የደም ሴሎች በአእምሮ ውስጥ ባሉ በጣም ደቃቅ የደም ስሮች (Capillaries) ግድግዳ ላይ ተጠጋግተው ይጣበቃሉ።
✅ኦክስጅን ማጣት: በመሆኑም ልክ የውሃ ቧንቧ በቆሻሻ እንደሚዘጋው ሁሉ፣ የአእምሮ የደም ስሮችም በእነዚህ ሴሎች ይዘጋሉ። በዚህ ጊዜ አእምሮ በቂ ኦክስጅንና ግሉኮስ (ስኳር) አያገኝም።
✅መርዛማ ኬሚካሎች: ተህዋሲያኑ በደም ስሩ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ይለቃሉ፤ ይህም አእምሮ እንዲያብጥ (Brain Swelling) ያደርጋል። በመጨረሻም በተዘጋው የደም ቧንቧ አካባቢ በመራባት የአእምሮ ስራ መታወክን ያስከትላሉ። በአጠቃላይ ይህ ሁኔታ የጭንቅላት ወባ (Cerebral Malaria) ይባላል፡፡
3. ዋና ዋና ምልክቶቹ (Clinical Features) ምንድናቸው?
⚠️ አንድ ሰው የጭንቅላት ወባ ሲይዘው የሚከተሉትን ለየት ያሉ ምልክቶች ያሳያል፡
✅ከፍተኛ የባህሪ መለወጥ (Behavioral change): በድንገት መጮህ፣ መቃዠት ወይም ሰዎችን አለማወቅ።
✅የንቃተ መቀነስ (Loss of consciousness): ጥያቄ ሲጠየቁ መልስ አለመስጠት ወይም መንቃት አለመቻል።
✅የአካል መዛልና ማንቀጥቀጥ (Seizures): እራስን መቆጣጠር አለመቻልና ልክ እንደ የሚጥል በሽታ አይነት መፈራገጥ/መውደቅ
✅እራስን አለማዎቅ/ኮማ (Deep Coma): ሙሉ በሙሉ ራስን መሳትና መናገር መብላትና መጠጣት አለመቻል ዋና ዋና ምልክቶች ሆነው ሊታዩ ይችላሉ
4. እንዴት መመርመር ይቻላል (How to Diagnose)?
✅የደም ምርመራ ማድረግ: ማይክሮስኮፕን በመጠቀም በደም ውስጥ የወባ ተህዋሲያን መኖራቸውን ማረጋገጥ ይቻላል
✅የግሉኮስ መጠን: ብዙ ጊዜ የጭንቅላት ወባ የታካሚውን ስኳር ስለሚያሳንሰው የግሉኮስ መጠንን መለካት የግድ እንደ አንድ ጠቋሚሊቆጠር ይችላል
✅ሌሎች በሽታዎችን መለየት: ምልክቶቹ ከጭንቅላት ውስጥ ኢንፌክሽን (Bacterial, Fungal and Viral Meningitis) ጋር ስለሚመሳሰሉ Lumbar puncture በመጠቀም የጭንቅላት ፈሳሽን (Spinal fluid) በመውሰድ ማረጋገጥ ሊያስፈልግ ይችላል
5. እንዴት ይታከማል? (How to treat)?
ይህ የወባ በሽታ ደረጃ ሰዎች በህክምና ተቋም ሆነው በጥብቅ የህክምና ክትትል ስር ሆኖ የሚሰጥ ስሆነ "ቤት ውስጥ" የሚታከም በሽታ እንዳልሆነ በቅድሚያ መረዳት ያስፈልጋል!
በመሆኑም እንደ አርቴሱኔት (Artesunate) ዓይነት በደም ስር የሚሰጡ ፈጣን መድሃኒቶች ይሰጣሉ። የታካሚውን የአተነፋፈስ ሁኔታ መከታተል፣ የሚጥል በሽታን መቆጣጠርና በቂ ፈሳሽ መስጠት የህክምናው አካል ነው። ታካሚው ነቅቶ ወባው ከደሙ እስኪጠፋ ድረስ የቅርብ የህክምና ክትትል ያስፈልገዋል።
6. ወባን እንዴት እንከላከል? (Prevention Strategies)
መከላከያዎቹን በዝርዝር ማወቁ በሽታው ከመከሰቱ በፊት እራስንና ቤሰብን ለማዳን ይረዳል። እንዳጠቃላይ ወባን ለመከላከል የምንከተላቸው መንገዶች በሁለት ይከፈላሉ፦
እነዚህም የትንኝ ንክሻን መከላከል እና በሽታው ከታየ በኋላ ፈጣን ምርመራና ህክምና ማድረግ ናቸው። የጭንቅላት ወባን መከላከል ማለት ወባን ከመሰረቱ መከላከል ማለት ነው። እነዚህን 4 ዋና ዋና ነጥቦች ይተግብሩ፦
A) የትንኝ ንክሻን በንቃት መከላከል (Vector Control)፦ ትንኝ እንዳትነክሰን የምናደርገው ጥንቃቄ የመጀመሪያው መከላከያ መስመር ነው ሲሆን የሚከተሉትን እርምጃዎች ይውሰዱ:
✅የአልጋ አጎበር (ITNs) መጠቀም: በፀረ-ትንኝ ኬሚካል የተነከረ አጎበርን ሁልጊዜ ማታ ማታ መጠቀም።
✅የቤት ውስጥ ኬሚካል መርጨት (IRS): በጤና ባለሙያዎች የሚረጩ ፀረ-ትንኝ ኬሚካሎችን በቤት ግድግዳ ላይ ማስረጨት።
✅የልብስ ምርጫን ማስተካከል: በተለይ ትንኝ በብዛት በሚንቀሳቀስበት ምሽትና ማለዳ ላይ ሰውነትን የሚሸፍኑ ረጅም እጅጌ ያላቸው ልብሶችን መልበስ።
✅መከላከያ ቅባቶችችን መጠቀም (Repellents): በቆዳ ላይ የሚቀቡ ትንኝ አባራሪ ቅባቶችን መጠቀም።
B) የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ማጥፋት፦ ትንኝ የሚራባው በቆመ/ባቆረ ውሃ ላይ ስለሆነ በቤት ዙሪያ የሚገኙ ኩሬዎችን፣ ክፍት የውሃ ማጠራቀሚያዎችን እና ቦዮችን ማድረቅ ወይም መክደን። የአካባቢን ንጽህና መጠበቅና ቁጥቋጦዎችን መመንጠር።
C) ቅድመ-መከላከያ መጠቀም (Chemoprophylaxis)፦ በተለይ ለጎብኝዎች፥ ለነፍሰ ጡር እናቶች እና ለህፃናት በጤና ተቋማት የሚሰጡ የወባ መከላከያ መድኃኒቶችን በወቅቱ መውሰድ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ በቅርቡ የተጀመረውን የወባ ክትባትን ልጆችን ማስከተብ ወባን ለመከላከል ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ከወባ ነፃ ከሆነ አካባቢ ወደ ወባማ አካባቢ የሚጓዙ ሰዎች አስቀድመው መከላከያ መድኃኒት (Prophylaxis) መውሰድ አለባቸው።
D) ፈጣን ምርመራና ህክምና የጭንቅላት ወባ የሚከሰተው ተራው ወባ ሳይታከም ሲቆይ ነው።
ስለዚህ፦
-ማንኛውም የትኩሳት ምልክት ሲታይ በ 24 ሰዓት ውስጥ ደም መመርመር።
-የወባ መድኃኒት ሲታዘዝልዎ መመሪያውን ጠብቆ መጨረስ። መድኃኒቱን አቋርጦ መተው ተህዋሲያኑ እንዲበረቱና ወደ ጭንቅላት ወባ እንዲቀየሩ እድል ይሰጣቸዋል።
#ማሳሰቢያ፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የወባ በሽታ ስርጭት እየጨመረ ስለሆነ፣ ማንኛውም የትኩሳት ስሜት ሲሰማዎት ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ደምዎን እንዲመረመሩ እናሳስባለን።
#ማጠቃለያ፡ የጭንቅላት ወባ ጊዜ የማይሰጥ በሽታ ነው። ከፍተኛ ትኩሳት ካለዎትና ግራ የመጋባት ምልክት ከታየብዎት፣ ወደ ህክምና ቦታ ለመሄድ በጭራሽ እንዳያቅማሙ!
#HealthBreak #MalariaAwareness #MalariaPrevention #cerebralmalaria #ኢትዮጵያ
7 hours ago (edited) | [YT] | 2
View 0 replies
Health Break የጤና ዕረፍት
የቫይታሚን D እጥረትና የጭንቀት አዙሪት!
The Vitamin D Deficiency & Stress Cycle
የቫይታሚን D እጥረት እና የጭንቀት (Anxiety/Depression/Stress) ግንኙነት በቅርብ ጊዜ በሕክምናው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት እየተሰጠው የመጣ ጉዳይ ነው።
1. ቫይታሚን D በሰውነታችን ውስጥ ሆርሞኖች እንዲመረቱ የሚያገለግል ሲሆን በአንጎላችን ውስጥ ስሜትን የሚቆጣጠሩ ክፍሎች (Receptors) ላይ በቀጥታ ይሰራል። ቫይታሚን D እንደ Serotonin እና Dopamine ያሉ የደስታ ስሜትን የሚፈጥሩ ሆርሞኖች እንዲመረቱ ይረዳል። እጥረቱ ሲኖር እነዚህ ሆርሞኖች ስለሚቀንሱ ለጭንቀትና ለድብርት እንጋለጣለን።
2. ጭንቀት በቫይታሚን D ላይ ያለው ተጽዕኖ ደግሞ አዙሪቱን የሚያጠናክረው ተቃራኒው መንገድ ነው። ሰዎች በጭንቀት/በድብርት ምክንያት ከቤት አለመውጣት ሌላው የቫይታሚን ዲ እጥረት አዙሪት ምክንያት ነው፡፡ አንድ ሰው በጭንቀት ወይም በድብርት ውስጥ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜውን ቤት ውስጥ ማሳለፍ ይመርጣል። ይህም ከፀሐይ ብርሃን (ዋነኛው የቫይታሚን D ምንጭ) እንዲርቅ ያደርገዋል። ከዛም ባለፈ ጭንቀት የምግብ ፍላጎት መዛባትን በማስከተል ጤናማ አመጋገብን እንዳይኖረን ሊያደርገን ይችላል፣ ይህም በቂ ቫይታሚን ከምግብ እንዳናገኝ ያደርጋል።
3. አዙሪቱ ምን ይመስላል?
🔁የቫይታሚን D መጠን ይቀንሳል ➡️ የድብርት/የጭንቀት ስሜት ይፈጠራል ➡️ ጭንቀቱ ይጨምራል ➡️ ሰውየው ራሱን ያገልላል፣ ቤት ይውላል፣ የፀሐይ ብርሃን አያገኝም ➡️ ፀሐይና እንቅስቃሴ ሲቀንስ - የቫይታሚን D መጠኑ ይበልጥ ይቀንሳል ➡️ ይህ ሂደት ደጋግሞ በመመላለስ ግለሰቡን በአስቸጋሪ የአእምሮ እና የአካል ጤና ቀውስ ውስጥ ይከተዋል።
4. ምን መደረግ አለበት?
✅የደም ምርመራ፡ መጀመሪያ የቫይታሚን D መጠንዎን በምርመራ ማወቅ።
✅የፀሐይ ብርሃን፡ በቀን ቢያንስ ለ15-20 ደቂቃ የጠዋት ፀሐይ መሞቅ።
✅ምግብ፡ እንደ አሳ፣ እንቁላል እና የወተት ተዋጽኦዎችን ማዘውተር።
✅ተጨማሪ መድኃኒቶች (Supplements) መውሰድ፡ ሐኪም በሚያዘው መሠረት የቫይታሚን D እንክብሎችን መውሰድ በጭንቀት ለሚሰቃዩ ሰዎች ከፍተኛ መሻሻል ሲያሳይ ይታያል። ነገር ግን ይህ የቫይታሚን D መጠን በጣም ዝቅተኛ ከሆነ በምግብ ብቻ ማስተካከል ስለሚከብድና ማሟያዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሲሆን ነው። ዓይነቱ፣ መጠኑና አወሳሰዱ በሀኪም ትእዛዝ መሰረት መሆን አለበት፡፡
☞አስታውሱ፣ ቫይታሚን D በስብ ውስጥ የሚሟሟ በመሆኑ፣ ቅባት ካለው ምግብ ጋር መውሰድ በሰውነት ውስጥ የመምጠጥ እድሉን በ 50% ይጨምራል። በተጨማሪም ብዙ ሰው የሚዘነጋው ነገር ቫይታሚን D በሰውነታችን ውስጥ እንዲሰራ ማግኒዥየም እንደሚያስፈልገው ነው።
5. እንደ ማጠቃለያ!
የትኛው ይቀድማል?
እንደ እውነቱ ከሆነ ሁለቱም ሊቀድሙ ይችላሉ።
✅ከፍተኛ ጭንቀት (High Cortisol):
ሰውነታችን በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨነቅ የሚመነጨው 'ኮርቲዞል' የተሰኘው ሆርሞን ሰውነታችን ቫይታሚን Dን እንዳይቀበል ወይም እንዳይጠቀም እንቅፋት ይሆናል። ይህም ለቫይታሚን D እጥረት ይዳርገናል።
✅የቫይታሚን D እጥረት:
በሌላ በኩል ደግሞ በቂ ቫይታሚን D በሰውነታችን ውስጥ ከሌለ፣ አእምሯችን ጭንቀትን የመቋቋም አቅሙ ይዳከማል፤ ይህም ኮርቲዞል ያለምክንያት እንዲጨምር ያደርጋል።
ባጭሩ ጭንቀቱ ቫይታሚኑን ያሳጣል፣ የቫይታሚኑ ማነስ ደግሞ ጭንቀቱን ያባብሰዋል። ስለዚህ ፀሐይ መሞቅና የተመጣጠነ ምግብ መውሰድ ለጤና ብቻ ሳይሆን ለሥነ-ልቦናዊ ጥንካሬህም (ለጭንቀት መቋቋሚያ) ቁልፍ ነው።
✍ማሳሰቢያ፦ ጭንቀት መንስኤው የቫይታሚን እጥረት ብቻ ላይሆን ስለሚችል፣ ከባለሙያ ጋር ማማከር በጣም አስፈላጊ ነው።
ለተጨማሪ መረጃዎች ቻናሉን ይቀላቀሉ
#Healthbreak #foryouシ
2 days ago | [YT] | 1
View 0 replies
Health Break የጤና ዕረፍት
"በመርፌ የሚወሰድ የኤች አይ ቪ መከላከያ መድሃኒት የFDA ፈቃድ አገኘ"
በ6 ወር አንዴ የሚወሰደውን የኤች አይ ቪ መከላከያ ጥቅም ላይ እንዲውል አሜሪካ ፈቀደች።
ሌናካፓቪር (Lenacapavir) የተሰኘው የ ኤች አይ ቪ (HIV) መከላከያ የሆነው መድኃኒት በአሜሪካው ምግብና መድኃኒት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ አግኝቷል።
በሙከራ ደረጃ 99 በመቶ ኤች አይቪን የመከላከል አቅም አለው የተባለው መድኃኒቱ በመርፌ መልክ የሚሰጥ ነው።
ከዚህ ቀደም በየቀኑ የሚወሰድ እንክብል እንዲሁም በየ 2ወሩ በመርፌ የሚሰጥ የጸረ ኤች አይቪ ኤድስ መድኃኒት ገቢያ ላይ የነበረ ሲሆን ይህ የሚለየው የመውሰጃውን ጊዜ ወደ 6 ወር በማሳደጉ ነው።
በምርምር ወቅት ከአፍሪካ ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ማሳተፍ ችሏል የተባለው ይኸው መድኃኒት በዘርፉ ትልቅ ውጤት የተመዘገበበት ነው ተብሏል።
ከአሜሪካ በተጨማሪ አውስትራሊያ፤ ብራዚል፤ ካናዳ፤ ደቡብ አፍሪካ በሂደት ላይ ያሉ ሀገራት ናቸው ተብሏል።
ምንም እንኳን ውጤታማ ቢሆን ዋጋው ውድ መሆኑ ስጋት ፈጥሯል።
#NB: ይህ መድኃኒት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎችን የሚያድን ሳይሆን ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች በቫይረሱ እንዳይያዙ የሚከላከል Pre-Exposure Prophylaxis (PrEP) ነው።
"FDA approval of injectable HIV drug lenacapavir marks progress for HIV prevention"- WHO
The World Health Organization (WHO) welcomes the approval by the United States Food and Drug Administration (FDA) of injectable lenacapavir for HIV prevention.
This milestone follows promising 2024 results from the PURPOSE 1 and PURPOSE 2 trials, which demonstrated the safety and efficacy of lenacapavir across diverse populations and settings. Administered just twice a year, lenacapavir offers sustained protection and adds to the growing range of HIV prevention options.
#WHO currently recommends oral PrEP, the dapivirine vaginal ring, and long-acting injectable cabotegravir (CAB-LA) as options for HIV pre-exposure prophylaxis (PrEP). Lenacapavir’s discreet, long-acting formulation may help overcome key barriers such as daily pill burden, frequent clinic visits, and stigma associated with HIV prevention.
“This regulatory milestone brings us one step closer to expanding access to an innovative HIV prevention option in lenacapavir,” said Dr Meg Doherty, Director of WHO’s Global HIV, Hepatitis and STI Programmes. “WHO plays a key role in supporting countries through guideline development, prequalification, and regulatory processes. We are working with partners and national authorities to ensure lenacapavir reaches people who need it most – quickly, safely and equitably.”
#WHO guidelines for injectable lenacapavir will be released on 14 July 2025, during the International AIDS Conference in Kigali.
FDA approval also paves the way for #WHO prequalification, which can accelerate national regulatory approvals following endorsement by a stringent regulatory authority (SRA) and procurement by donor agencies like the the Global Fund. In parallel, WHO is working with the European Medicines Agency (EMA) to support the Medicines 4 All (M4All) mechanism, which facilitates regulatory pathways in countries adopting lenacapavir.
Via #TikvahethMagazine #WHO
7 months ago | [YT] | 5
View 0 replies
Health Break የጤና ዕረፍት
🚨በኢትዮጵያ በኤምፖክስ በሽታ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ!
🔄#MpoxUpdate!!🚨
☞First #Mpox death recorded in Ethiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤምፖክስ) ከተያዙ ሰዎች ውስጥ የአንዱ ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ብዛት ስድስት ደርሷል።
የጤና ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውስጥ በኤምፖክስ በሽታ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ያስታወቀው ቅዳሜ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም. ባወጣው ዕለታዊ መረጃ ነው።
ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኤምፖክስ በሽታው ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ያስታወቁት ባለፈው ሳምንት እሁድ ግንቦት 17 ነበር።
በበሽታው የተያዙት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች የተገኙት ከኬንያ ጋር በምትጎራበተው ሞያሌ ከተማ አስተዳደር እንደነበር ተገልጿል። በበሽታው የተያዙት የ21 ቀን ዕድሜ ያለው ህጻን ልጅ እና እናቱ እንደሆኑም ሁለቱ ተቋማት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ወደ ጎረቤት ሀገር ተጎዞ ነበር ከተባለው የህጻኑ አባትም ጋር "የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችን የመለየት እና ክትትል የማድረግ ስራ" መጀመሩንም መግለጫው ጠቅሷል።
በበሽታው የተያዙት "ታማሚው ህጻን እና እናቱ አስቀድሞ በተዘጋጀው የለይቶ ማከሚያ ተገቢው የህክምና ክትትል" እየተደረገላቸው አንደሆነ የጠቀሰው መግለጫው፤ "የከፋ የጤና እክል አልገጠማቸውም" ብሎ እንደነበር ይታወሳል።
በበሽታው ሁለት ሰዎች መያዛቸው ይፋ ከተደረገ በኋላ አንድ ተጨማሪ ሰው በኤምፖክስ እንዳለበት የተረጋገጠው ማክሰኞ ዕለት ነው። ረቡዕ ዕለት ይህ ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ብዛት ስድስት ደርሷል። ይህ የታማሚዎች ቁጥር እስከ አርብ ድረስ በተመሳሳይ መልኩ መቀጠሉን ጤና ሚኒስቴር በየቀኑ የሚያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ጤና ሚኒስቴር ቅዳሜ ምሽት ባወጣው ዕለታዊ መረጃ በበሽታው ተይዘው ከነበሩ ስድስት ሰዎች ውስጥ የአንድ ግለሰብ ህይወት ማለፉን ይፋ አድርጓል። በበሽታው ተይዘው ከነበሩት ሰዎች መካከል የየትኛው ግለሰብ ህይወት እንዳለፈ ሚኒስቴሩ አልገለጸም።
ከዚህ በተጨማሪ ቅዳሜ ዕለት ብቻ በበሽታው እንደተያዙ በመጠርጠራቸው የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ብዛት ዘጠኝ እንደሆነ ተመላክቷል። ከረቡዕ ዕለት ጀምሮ በአጠቃላይ የተከናወኑ የላቦራቶሪ ምርመራዎች ብዛት ስድስት የነበረ ሲሆን ትናንት የተደረጉት ምርመራዎች ይህንን ቁጥር ወደ 15 አሳድገውታል።
ሞንኪፖክስ በተባለ ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox)፤ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ እብጠት፣ ሽፍታ፣ ሳል፣ የጀርባ እና የጡንቻ ሕመምን እንዲሁም የቆዳ ቁስለት እና ድካም ይታይባቸዋል።
በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት ከተከሰተ በኋላ ከፊት ጀምሮ ቀሪውን የሰውነት ክፍልን የሚያዳርስ እንዲሁም በአብዛኛው በእጅ መዳፍ እና በእግር መረገጫን የሚሸፍን ሽፍታ ያጋጥማቸዋል።
በሰውነት ላይ የሚያጋጥመው ሽፍታ በጣም የሚያሳክክ እና የሚቆጠቁጥ ሲሆን፣ በተለያዩ የለውጥ ደረጃዎች ውስጥ አልፎ በመጨረሻም እብጠት በመፍጠር ኋላ ላይም ይከስማል። ቁስለቱም ጠባሳን ትቶ ሊያልፍ ይችላል።
ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ የአፍሪካ በሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ሆኖ የታወጀው ኤምፖክስ፤ እስከ ባለፈው ሚያዝያ ወር ድረስ ጎረቤት ሀገራት ኬንያ እና ደቡብ ሱዳንን ጭምሮ በዘጠኝ የአፍሪካ ሀገራት ተከስቷል።
በዚህ የሀገራት ዝርዝር ውስጥ የተካተተችው ኢትዮጵያ፤ በሽታውን ለመከላከል ሲባል "በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ውስጥ የድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል ተቋቁሞ" እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።
በበሽታው ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች የሚቆዩባቸው "የተለዩ የጤና ተቋማት" እንደተዘጋጁ እንዲሁም የጤና ተቋማት በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ለማለም "አስፈላጊውን ዝግጅት እንዳጠናቀቁ" መነገሩ አይዘነጋም።
Source: BBC Amharic
7 months ago | [YT] | 2
View 0 replies
Health Break የጤና ዕረፍት
🚨#የጥንቃቄ_መልእክት⚠️
✅የገበታ ጨው ምርቶች ጥራት ጉድለት⚠️
በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው ላይ በተደረገ የገበያ የቅኝት ስራ የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ሳያሟሉ እንዲሁም ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ ምርቶችን #ህብረተሰቡ_እንዳይጠቀማቸው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡
ባለስልጣኑ በሰራው የገበያ ቅኝት ስራዎች 44 ዓይነት የምርት መለያ ስም ያላቸው የተለያዩ በአዮዲን የበለፀጉ የምግብ ጨው በሚል ታሽገው ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ በተጨማሪም የሀገሪቱን አስገዳጅ ብሔዊ ደረጃ፣ እና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃ ሳያሟሉና ሳይለጥፉ ሲቀርቡ የነበሩ ምርቶች መገኘታቸው አስታውቀዋል፡፡
በመሆኑም በየደረጃው ከሚካሄዱ በርካታ የቁጥጥሩ ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የገበያ ቅኝት ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ ምግቦች ላይ ባደረገው የገበያ ቅኝት በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው CES 70 2017 እና የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ያላሟሉ እና የደረጃ ምልክት ያለጠፉ ምርቶችን መለየት የተቻለ ሲሆን በምርቱ ላይ ስለምርቱ የተለጠፉ ወይም የተፃፉ የምርት ገላጭ ፅሁፍ የኢትዮጵያ እስታንዳርድ ኢንስቲቲዩት ያወጣው አስገዳጅ ደረጃ CES 73 2013 ያላሟሉ ሲሆን በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶች፦
✍የአምራች ድርጅት ስም ያልተጠቀሰ፣
✍የአምራች አድራሻ ያልተገለፀ፣
✍አስገዳጅ የደረጃ ምልክት/ የበለጸገ ምግብ ሎጎ የሌለው፣
✍የምርቱ መለያ ቁጥር የሌለው፣
✍የምርቱ ጥሬ ግብዓት ዝርዝር ያልተገለፀ፣
✍የአዮዲን መጠን ያልተጠቀሰ
✍የመጠቀሚያ እና የማብቂያ ጊዜ የሌላቸው ምርቶች መሆናቸው ተለይተዋል፡፡
የጥራት ደረጃ ሳያሟሉ የተገኙ ምርቶች ዝርዝር፦
1. አበሩሰ አዮዳይዝድ ጨው
2. ዛክ የገበታ ጨው
3. ሉሉ የገበታ ጨው
4. ሙሪዳ አዮዳይዝድ ጨው
5. እቱ የገበታ ጨው
6. እቴቴ የገበታ ጨው
7. እፍታ ጨው
8. ኤልሳ የገበታ ጨው
9. ሴፍ የገበታ ጨው
10. NS አዮዳይዝድ ሳልት
11. ማሚ የገበታ ጨው
12. ሣሊህ የገበታጨው
13. እማ የገበታ ጨው
14. አዮዲን የገበታ ጨው
15. ቃና የገበታ ጨው
16. ሀርመኒ የገበታ ጨው
17. ውዛት አዮዳይዝድ ሳልት
18. ሐበሻ ባለ አዮዲን ጨው
19. ሪል የገበታ ጨው
20. ሸጋ የገበታ ጨው
21. ጆይ አዮዳይዝድ ሳልት
22. ኮከብ የገበታ ጨው
23. ስኬት የገበታ ጨው
24. ፎር ኤም አዮዳይዝድ ሳልት
25. አዲስ የገበታ ጨው
26. ኤመሬት ጨው
27. አስቤዛ የገበታ ጨው
28. ቶም የገበታ ጨው
29. በረከት የገበታ ጨው
30. ሜናታ የገበታ ጨዉ
31. ቤስት አዮዳይዝድ ጨዉ
32. አፊአ የገበታ ጨው
33. ዋን በአዮዲን የበለፀገ የገበታ ጨዉ
34. አቢሲኒያ የገበታ ጨዉ
35. ማሩ የገበታ ጨዉ
36. ባና ኤዳይዝድ ጨው
37. ማራኪ ጨዉ
38. መክሊት የገበታ ጨዉ
39. ዳግም የገበታ ጨዉ
40. አዲስ የገበታ ጨዉ
41. አፍያ ጨዉ
42. ኦማር የገበታ ጨው
43. ገዳ የገበታ ጨው
44. ንጹህ አዮዳይዝድ ጨው
Source: #EFDA & #tikvahethmagazine
#health #HealthBreak #ጤና #tablesalt
10 months ago (edited) | [YT] | 3
View 0 replies
Health Break የጤና ዕረፍት
#OutbreakAlert🚨🚨⚠⚠
የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) ወረርሽኝ በጎረቤት ደቡብ ሱዳን መከሰቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል!
South Sudan has declared an outbreak of #mpox after the virus was confirmed on 6 February 2025.
"Ministry of Health of South Sudan, WHO and partners are enhancing control measures, including treatment, contact tracing, testing and infection prevention to curb the spread of the disease" - #WHO
Details:👇👇
www.afro.who.int/countries/south-sudan/news/south-…
11 months ago | [YT] | 4
View 0 replies
Health Break የጤና ዕረፍት
ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች፣
እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ይሁንላችሁ🙏
Wishing you a #happyepiphany!🙏
#healthbreakየጤናዕረፍ
1 year ago | [YT] | 3
View 0 replies
Health Break የጤና ዕረፍት
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የጤና ዕረፍት ቤተሰቦች በሙሉ፥
እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ🎁
Health break wishes you a happy christmas🎄
መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ እንመኛለን🎄🎄
1 year ago | [YT] | 5
View 0 replies
Health Break የጤና ዕረፍት
የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በአካባቢያዊነት የሚመደቡበትን ሥርዓት ለማቆም እየተሰራ ነው ተባለ- FBC
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዛሬው እለት [ታህሳስ -25/2017] ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በአካባቢያዊና በመንደር የሚመደቡበት ሥርዓት መቆም አለበት በሚል በርካታ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች የዓለም አቀፍ እውቀት መማሪያና የማስተማሪያ ተቋማት እንጂ የአንድ አካባቢን ሰዎች ተቀብለው የሚያስተናግዱ አይደሉም ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡
አሰራሩ ከዩኒቨርሲቲ መሰረታዊ ተልዕኮ ጋር እንደማይሄድ ጠቁመው÷አዲስ የሚመደቡና የሚቀየሩ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እንደ መርሕ በችሎታና በውድድር ብቻ የመመደብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች እውቀትና እውነት የሚገበይባቸው ትክክለኛ የማስተማሪያና የምርምር ተቋማት ሊሆኑ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
1 year ago | [YT] | 2
View 0 replies
Health Break የጤና ዕረፍት
ሰበር ዜና!
የዓለም ጤና ድርጅት (#WHO) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከጥቃት ማምለጣቸውን አስታወቁ!
#healthbreakየጤናዕረፍ
እስራኤል በየመን ሰነዓ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ከሰአታት በፊት ባደረሰችዉ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ጥቃቱ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአውሮፕላን ማረፊያው በነበሩት ወቅት መፈፀሙን ነው የተገለፀው።
እስራኤል በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ በሚገኙት የሀውቲ አማፂያን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት መፈፀሟን ይፋ አድርጋለች።
ዳይሬክተሩ በ'X' ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እርሳቸውና ባልደረቦቻቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ በአደጋው ህይዎታቸው ላለፉትና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡
Via (ባላገሩ ቴሌቪዥን)
1 year ago (edited) | [YT] | 1
View 0 replies
Load more