Free press

መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!

3 days ago | [YT] | 183

Free press

ሰላም እንደምን አደራችሁ፤ እንደምን ዋላችሁ፤ አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዋት ሳፕ ጻፉልን

+31645665578

1 week ago | [YT] | 124

Free press

ሰላም ውድ ተመልካቾቻችን፤ ፍሪ ፕረስ ሚዲያን ስለምትመለከቱ እያመሰግንን ፤ በሙያ፣ በእስቱዲዮ ማቴርያል እና በገንዘብ እንድትደግፉን እንጠይቃለን፡

በሳተላይት እየመጣን ነው!
+31645665578 በዋትሳፕ - አስተያየት አድርሱን : እናመሰግናለን

2 weeks ago (edited) | [YT] | 216

Free press

ጋዜጠኛ አዲሱ ደረበ በልዩ ዝግጅት ተመልሷል ፡ ሰብስክራይብ አድርጉት https://youtube.com/watch?v=HSscF-NWN...

2 weeks ago | [YT] | 7

Free press

ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ የአመራር ምደባ አድርጓል። የቀድሞወቹ ሁለት እዝ አመራሮች በጋራ በአካል በመገናኘት ባድካሄዱት ጉባኤ የተዋሃደው የጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ አመራር በሚከተለው መልኩ የኃላፊነት ምደባ ተደርጓል።
የሰብሳቢውን ቦታ አርበኛ ዮሐንስ ንጉሱ እና አርበኛ ባዬ ቀናው ለ3 ወር ያክል በጥምር የሚመሩት ይሆናል፡፡
ከሁለቱ አርበኞች በተጨማሪ:-
ተቀ/ምክ/ሰብሳቢ…………………አርበኛ ሰለሞን አጣናው
ም/ሰብሳቢ ለፖለቲካ ጉዳዮች………አርበኛ ኪሩቤል ጎቤ
ወታደራዊ አዛዥ…………………….አርበኛ ደረጀ በላይ
ምክ/ወታደራዊ አዛዥ………………አርበኛ አሻምበል አምሳሉ ማዘንጊያ
ምክ/ወታራዊ አዛዥ ለአስተዳደር ጉዳዮች....አርበኛ ሸጋ ጌታቸው
ወታራዊ አማካሪ…………………………ኮ/ል አበራ አዛናው
ፖለቲካ መምሪያ…………………..……አርበኛ አንተነህ ድረስ
ዘመቻ መምሪያ……………………….አርበኛ ተሾመ አበባው
ጽ/ቤት ኃላፊ……………………….አርበኛ በየነ አለማው
አደረጃጀት ጉዳይ …..……………..አርበኛ አበበ መልኬ
ፋይናንስና ግዥ መምሪያ……….አርበኛ ሐብታሙ ሙላው
ሎጅስቲክ መምሪያ…………….………አርበኛ በላዬ ዘለቀ
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ………….…አርበኛ ጋሻው ግዛት
ሕዝብ አስተዳደር መምሪያ………….አርበኛ ንጉሴ አዱኛ
ልዩ ዘመቻ መምሪያ..……………….አርበኛ አስፋው ሰርፀ
ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ…….……አርበኛ ጌታሰው በሬ
ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ መምሪያ…..አርበኛ ተመስገን አብርሃም
ምክ/ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ……..……አርበኛ ስጦታው ዳኛው/ባሻ
ሜካናይዝድ ጦር መምሪያ………..አርበኛ ሲሳይ አሸብር
ቴክኖሎጅና ምህንድስና መምሪያ……አርበኛ ያለው አዱኛ
ጥናትና ስትራቴጂ መምሪያ………..አርበኛ ዘመነ እረኛው
ትምህርትና ስልጠና መምሪያ……….አርበኛ ዘላለም በላይነው
ሕግና ስነ-ምግባር ጉዳይ መምሪያ……አርበኛ ማሩ ቢተው
ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ………..አርበኛ ብዙአየሁ ወንድምነው
ሴቶችና ወጣቶች መምሪያ………..አርበኝት አስምሪው መሳፍንት ተስፉ
ሰው ሃብት አስተዳር መምሪያ….……አርበኛ አዳነ ፀጋ
ሃብት አፈላላጊ መምሪያ….…………..አርበኛ ማሩ በሪሁን
ኢንዶክትሪኔሸን መምሪያ…..………አርበኛ ተመስገን ውባንተ
የውስጥ ኦዲት መምሪያ……………..አርበኛ ግዛቸው አሌ
ጤና መምሪያ……………………………አርበኛ አታለለ ሰጠኝ
እቅድ ዝግጅትና ግምገማ መምሪያ ……አርበኛ ታደሰ ወርቁ
ቁጥጥርና ኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ…………አርበኛ ባንቲደር እውነቱ
ሕግና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ…………አርበኛ ወልደአረጋይ ሸርብ
ወታራዊ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ……………..አርበኛ ታርቆ ከበደ
2ኛ. ምክትል የስራ አስፈጻሚ መምሪያዎች
ምክ/ፖለቲካ መምሪያ………………..…አርበኛ ዳኛው አጣናው
ምክ/ጽ/ቤት………………………..አርበኛ መ/አ ገዳም ካሳ
ምክ/አደረጃጀት ጉዳይ…………………...አርበኛ ብርሃኑ ነጋ
ምክ/ፋይናንስና ግዥ መምሪያ…………..አርበኛ ስጦታው መልኬ
ምክ/ሎጅስቲክ መምሪያ…………………አርበኛ ደፋሩ አቤ
ምክ/ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ…………አርበኛ ማንደፍሮ ተሰማ
ምክ/ ሕዝብ አስተዳደር መምሪያ……….አርበኛ ዋሴ ታደሰ
ምክ/ልዩ ዘመቻ መምሪያ..………………...አርበኛ ሙሉዬ ደሴ
ምክ/ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ…………ሻምበል መሳፍንት ተስፉ
ምክ/ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ………...አርበኛ እያቸው ብርሃኑ
ምክ/ሜካናይዝድ ጦር መምሪያ…….…….አርበኛ ንጋት አየለ
ምክ/ቴክኖሎጅና ምህንድስና መምሪያ…….አርበኛ አለሜ ባዬ
ምክ/ጥናትና ስትራቴጂ መምሪያ………...አርበኛ ፋሲል ሙሏለም
ምክ/ትምህርትና ስልጠና መምሪያ………..አርበኛ አብዩ ማሩ
ምክ/ሕግና ስነ-ምግባር መምሪያ………..…አርበኛ ደመቀ አለሙ
ምክ/ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ…………..አርበኛ ደምሰው ድረስ
ምክ/ሴቶችና ወጣቶች መምሪያ……………….አርበኝት ገነት ፀጋው
ምክ/ሰው ሃብት አስተዳደር መምሪያ………አርበኛ ወዳጅ አስፋው
ምክ/ሃብት አፈላላጊ መምሪያ ….…………..አርበኛ አስማማው ዋለልኝ
ምክ/ኢንዶክትሪኔሸን መምሪያ ….…………አርበኛ አዲሱ መሰለ
ምክ/የውስጥ ኦዲት መምሪያ………………..አርበኛ መ/አ ቢራራ
ምክ/ወታደራዊ መረጃና መገናኛ መምሪያ……አርበኛ ሚናስ አለማየሁ
ምክ/ጤና መምሪያ…………………………..አርበኛ ምዕራፍ ሙጨ
ምክ/እቅድ ዝግጅና ግምገማ መምሪያ……….አርበኛ መ/አ ኃይለየሱስ ታደሰ

3ኛ. ሌሎች የስራ ክፍል ኃላፊዎች፡
የሕዝብ ሰላምና ደህንነት ከፍል…………አርበኛ መለሰ ተሾመ
ምርኮኛ አስተዳደር ከፍል …………….አርበኛ አለማየሁ ሰማ
ወታደራዊ ቃል አቀባይ………………..አርበኛ ቢኒያም አለምነህ
ቀጠናዊ ትብብር……………………...አርበኛ ዘመኑ ታደሰ
ሰማዕታት ቤተሰብ ድጋፍ ክፍል………..አርበኛ አማኑኤል ተፈራ
ስንቅ አቅርቦት ክፍል…………………..አርበኛ ክንዱ ግርማ
ሒሳብ ሹም…………………………….አርበኛ አያናው አዱኛ
መሰረተ-ልማትና ኢኮኖሚ ክፍል……..አርበኛ አበበ አመኑ
ኦርዲናንስ……………………………..አርበኛ ዳንኤል አስረስ
ፐርሶኔል …………………………….አርበኛ ዮናስ አያልቅበት
ግዥ ክፍል ………………………….አርበኝት ትዕግስት ተረፈ
ገንዘብ ያዥ……………….…………..አርበኛ መላክ ተስፋ
ሕዝብ አገልግሎት ………………….አርበኛ አለባቸው ጌጡ
ኪነ-ጥበብና መዝናኛ ክፍል…………..አርበኛ አስተውል አምሳሉ
ታሪክና ማሕደር ክፍል ……………..አርበኛ አንዷለም አሰፋ
አባት አርበኞች ማደራጃ ክፍል………አርበኛ ጌትነት ስመኝ
ማሕበራዊ ፍርድ ሸንጎ………………..አርበኛ ማናለ ገላጋይ
ፕሮጀክት ቀረፃና አስተዳደር …………አርበኛ ባንቲ ጌትነት

3 weeks ago | [YT] | 118

Free press

ከዚህ ፈገግታ በፊት ብዙ ድካም፣ ብዙ ልፋት ፣ ብዙ ጭንቀት ፣ብዙ ህመም አለ፤ ይሄን ሁሉ አልፈን ለእናንተ ያዘጋጀነውን ዜና እንድትከታተሉን ፈግገ እንላለን፡ አብራችሁን ሁኑ

4 weeks ago | [YT] | 564

Free press

ከአርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት አንዳንድ ነገሮች‼️

አለም ፊቱን ዞሮበት፥ ወይንም እንደፍጥርጥሩ ለእጣፋንታው ትቶት "ረስቶት" እያለ
"መተን ቀብረነዋል" የተባለው የአማራ ህዝብ "መቃብር" ፈንቅሎ ብድግ አለ።

ያለ አንዳች መካሪና ተቆርቋሪ፥ ያለ አንድ ሰው ሃሳብ አበዳሪ ከመከራው ተምሮ፥ ከራሱ መክሮ አማራ የራሱን አቢዮት ራሱ ፈጠረ።ሲነሳ በደነገጡት ጠላቶቹ ፊት ራሱን በፍጥነት አደራጅቶ የህልውና ትግሉን ጀመረ።እፍኝ የማትሞላ ተተኳሽ በመቶ ሽዎች ብር እየገዛ፥ ታጣቂም አስታጣቂም ራሱ ሆኖ ወደ ራሱ ግብ መገስገስ ቀጠለ። እነሆ ሶስት አመት አለፈው።
ትልቁ ብሄራዊ ሃብት ሰው ነው። የሁሉም ነገር... የፖለቲካውም፥ የታንኩም፥የዲፕሎማሲውም ፥ የርእዮተ አለሙም ግርግር ማእከሉ፥ መቋጫው ሰው ነው። ለሰው ልጆች የተሻለ ነገር ለማምጣት የሚደረግ ነው። የራሱን ህዝብ በሰማይም በምድርም እሳት አሰማርቶ የሚያነድ ዘረፈጅ ሥርዐት ስለ ብሄራዊ ክብርና ሉአላዊነት የት ያውቃል? ስለ ሃገር ለማውራት ሞራሉስ ከየት ይገኛል?አንገቷ ላይ ቆሞ እያነደዳት ያለችን ሃገር እወዳታለሁ ሊለን ይሞክራል። የጥፋት ተልእኮ ይዞ ሃገር እያቃጠለ ሳያፍር ሌላውን ሃይል በተላላኪነት ሊከስ ይዳዳዋል። ለግብፅ መላላክን፥ ለፕሬዝዝዳንት ኢሳያስ መሽቆጥቆጥን፥ ለህወሃት መንበርከክን አብይና ቡድኑ እንጅ ፋኖ አያውቀውም።

በኛ በኩል የአለም ጥቅሞች ሁሉ ተሰልፈው ቢመጡ፥ መዳፋችን ላይ ቢቀመጡ አንዲት ግራም የአማራን ህዝብ ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም። የአማራ ህዝብ ህልውና፥ ጥቅሙና ምኞቱ ለድርድር አይቀርቡም፥ "ቅዱስ" ናቸው። ቅዱሱን የሚነካም የሚያስነካም ማንም የለም።ነገር ግን ካለፉት ረጅም አመታትም ፥ከራሱ ከብልፅግና ስህተትና ውደቅትም ተምረን ከቀጠናዊና አለምአቀፋዊ ልውጥውጡ የማንም ወኪል ሳይሆኑ መጠቀምን እናውቅበታለን።በሊማሊሞ ገደል አናት በተወጠረ ገመድ ላይ አይናችን ታስረን እንኳን አመጣጥነን መራመድ እና ወደ ነገ መሻገር እንችላለን። ይህ መከራ ከእድሜው በላይ ያስተማረው ትግል ነው። ስለሆነም በፍፁም አንሳሳትም። ከኢትዮጲያውያን ሃይሎች ጋር በጋራ መርፌ የመግዛት ተልእኮ እንኳን ቢኖረን የአማራ ህዝብ በይፋ ሳያውቀው የምንጓዘው አንድም እንኳን ስውር እርምጃ የለም።
ጠላት ግን ይጮሃል። "ይህን ውሃ ምን ያስጮኸዋል ቢሉት፥ በውስጡ ያለው ድንጋይ" ብሎ መለሰለት አሉ። በዚህ ወቅት ብልፅግና የተባለ የኩሬ ቦይን የሚያስጮሁት "ድንጋዮች" ሁለት ናቸው፦

1)ፍርሃት። አብይ የቀጠናውና የሃገር ውስጥ ሃይሎች ከተባበሩ እድሜዬ በአንድ እጄ እጣቶች ልክ የተቆጠሩ ናቼው ብሎ ስለሚያምን ደንግጧል። እናም ድንገት ጥቂቶችን አደናግሬ የማምሻ እድሜ ባገኝ ብሎ ሌት ተቀን ይጮሃል።ከሞት የማያድን ጩኸት።

2)ጦርነት። በአብይ አህመድ ስሌት የአማራ፥ የትግራይ፥ የአፋርና ሌሎች ህዝቦች ገና በበቂ አልደቀቁም። ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መድቀቅና መጥፋት አለባቼው። ይህ ይሆን ዘንድ ግን "ሰበብ " ያስፈልጋል። ስለሆነም አቅም አግኝቶ ነገ ወደ አንድ ተረኛ ህዝብ ቢተኩስ ለአለሙ የሚነግረው ሰበብ "ተባብረው ሊያጠፉኝ ሲሉ ራሴን ለመከላከል ጦርነት ከፈትሁ" ይሆናል ማለት ነው። ይኸው ነው።

ይህ ትግል የአማራንና የሃገራችን ህልውናን የማረጋገጥ ትንቅንቅ ብቻ አይደለም፥ ቢያንስ ለሚቀጥሉት አምስት መቶ አመታት የጥይት ድምፅ የማይሰማ ትውልድ የመፍጠር ተልእኮም ነው።
ብልፅግና ይወገዳል፥የአማራ ህልውና ይረጋገጣል። ኢትዮጲያ ለኢትዮጲያውያን የፍቅርና የደስታ ምድር ትሆናለች፥ ሰላም ትሆናለች።

ክፋት ለማንም፥ በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ ፥አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ሰኔ-21/2018 ዓ. ም!
አርበኛ ዘመነ ካሴ!

1 month ago | [YT] | 466

Free press

ትልቁ የሞራል ስንቃችን የእናንተ አብሮነት እና አስተያየት ነው፡
ለማንኛውም ጥቆማ እና አስተያየት በዋት ሳፕ +31645665578 ያድርሱን

2 months ago | [YT] | 201

Free press

ጤና ይስጥልኝ ተመልካቾቻችን፤ ሀሳብ እና አስተያየት ካላችሁ በፌስቡክ melkam selam molla ብለው ቢጽፉልን ይደርሰናለ፡ መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ።

8 months ago | [YT] | 59

Free press

በፋኖ የተሰራው የ 1 ሰአት ዶክመንተሪ ፊልም ማየት ይችላሉ https://youtu.be/OMHZtC4yFEQ

9 months ago | [YT] | 7