ይህ የሀዋሪያት መንገድ የተሰኘ የሀዋሪያት የግል መዝሙሮችን ፣ አምልኮዎችን ፣ መንፈሳዊ ፕሮግራሞችን የሚያገኙበት የመንፈሳዊ ቻናል ነው ። የአገልግሎቱ ተከፋይ ለመሆን ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ። የምንለቃቸው ነገሮች ከተመቻችሁ ላይክ በማድረግ ፣ ኮመንት በመፃፍ አገልግሎቱን ያበረታቱ ።


Apostolicway

እንኳን ለ4ኛው ዓመት የአረካ ሳሌም ወጣቶች የወንጌል ኅብረት ጉባዔ በሠላም አደረሳችሁ❕

ሠላም የተወደዳችሁ የአንድ አምላክ ልጆች የሆናችሁ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን ቆያችሁ❓

"ወጣቱ ብንያም በጕልበቱ በዚያ አለ፥" በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ በሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በደቡብ ኢትዮጵያ ሰበካ በአረካ እናት አጥቢያ "የአረካ ሳሌም ወጣቶች የወንጌል ኅብረት" የተሰኘ ልዩ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ይገኛል።

ይኸውም ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜ 01 ድረስ ለ2 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስሆን በዚህ ልዩ ግብዣ ላይም፦
✅ የእግዚአብሐር ቃል፣
✅ የህብረት እና የግል ዝማሬዎች፣
✅ እንዲሁም የተለያዩ ወጣት ተኮር የሆኑ አዝናኝና አስተማሪ ዝግጅቶች ተሰናድተዋል።

ስለሆነም ሁላችሁም መጥታችሁ የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጥሪ እናቀርባለን ተባረኩ❕

የአረካ ሳሌም ወጣቶች የወንጌል ኅብረት

1 week ago | [YT] | 146

Apostolicway

እንኳን አደረሳችሁ

2 weeks ago | [YT] | 129

Apostolicway

እንኳን አደረሰን

3 weeks ago | [YT] | 128

Apostolicway

አፖስቶሊክ ሶንግስ ዛሬ 10 ዓመት ሞላው። 🎶

ከ10 ዓመት በፊት ቅዱሳን አፑን ተጠቅመው የመዝሙሩን ግጥም ብቻ ማየት ይችሉ ነበር።

ዛሬ ግጥሙንም እናነባለን፣ መዝሙሩንም እናዳምጣለን። በስልክ፣ በላፕቶፕ እና በቢሮ ኮምፒውተር ተጠቅመን የፂዮንን መዝሙር ማዳመጥ ችለናል።

ከ1000 በላይ መዝሙሮች።
ከ50,000 በላይ ተጠቃሚዎች፣ በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም።

ይህ ሁሉ የሆነው በእናንተ ነው። ስላዳመጣችሁ፣ ስላጋራችሁ እና
ስለጸለያችሁልን እናመሰግናለን።

ይህ ገና መጀመሪያው ነው።

Apostolic Songs is 10 years old today. 🎶

When we started ten years ago, the app did one thing. It showed the lyrics.

ten years later, you can read the words and hear the song. n your phone, on your laptop, and on your computer at the office.

1000+ songs.
50,000+ saints listening, in Ethiopia and across the world.

We started with the words. You gave them a voice.

Thank you for being part of the journey.

This is just the beginning.

📱 Play Store / App Store: Apostolic Songs
💻 open.asmeklit.com

"ሰዎች የዘመሩትን ሥራውን ታከብር ዘንድ አስብ።" (ኢዮብ 36፥24)
"Remember to magnify His work, of which men have sung." (Job 36:24)

#ApostolicSongs #SongsOfZion #10Years #አፖስቶሊክሶንግንስ #መዝሙር #10ኛዓመት

3 weeks ago | [YT] | 116

Apostolicway

የምስራች

በሀዋሳ ሆንሴ ሚሊንየም በተካሄደው የመላው ሲዳማ ሰበካ አመታዊ የወጣቶች ኮንፈረንስ ላይ 144 አዳዲስ ነፍሳት ለኃጢአታቸው ስርየት በኢየሱስ ስም ተጠምቀዋል።

ክብር ለኢየሱስ ይሁን!

3 weeks ago | [YT] | 285

Apostolicway

እንኳን አደረሳችሁ

3 weeks ago | [YT] | 92

Apostolicway

በአዲስአበባ ሰበካ አመታዊ ወጣቶች ኮንፈረንስ 173 አዳዲስ ነፍሳት ለኃጢአታቸው ስርየት በኢየሱስ ስም ተጠምቀዋል።

ክብር ለኢየሱስ ይሁን!

1 month ago | [YT] | 327

Apostolicway

መልካም ዜና

በሻኪሶ በተደረገው አመታዊ ጉባኤ 246 አዳዲስ ነፍሳት ለኃጢአታቸው ስርየት በኢየሱስ ስም ተጠምቀዋል። ክብር ለመከሩ ጌታ ለኢየሱስ ይሁን!

1 month ago | [YT] | 247

Apostolicway

የምስራች ዜና✅

#‎በኢትዮጵያ_ሐዋርያዊት_ቤቴክርስትያን በሐንጠጤና ዳራራ ቅ/ሰበካ በአርገዳ ንዑስ ከቀን 24-26/2018 በታላቅ ድምቀት ስካሄድ የነበረ ጉባኤው በሰላም ተጠናቀቀ፡፡

#በዚህ ጉባኤ 120 ነፍሳት በኢየሱስ ስም ተጠመቀው በእኛ ላይ ስለተጨመሩ ፡፡ክብሩን ኢየሱስ ይውሰድ

#ለለም ቦታም በመሐል ሲዳማ ቅ/ሰበካም በቡልታ ጎሮ ንዑስ ሰበካ በጉባኤው 6 አዳዲስ ነፍሳት በኢየሱስ ሰም ተጠምቋል ፡፡

#በኢትዮጵያ ሐዋረያዊት ቤተክርስቲያን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሰበካ ከሐምሌ 24/11/18_26/11/18 ድረስ በነበረው ጉባዔ እግዚአብሔር በትልቅ ሰማያዊ በረከት እያባረከ በታላቅ ድል ተጠናቋል ፡፡
‎ በጉባኤው 53 አዳዲስ ነፍሳት በኢየሱስ ሰም ተጠምቋል ።
‎ በድምሩ 179 ነፍሳት በኢየሱስ ተጠምቀዋል፡፡
‎እኛ የሰማይ ልጆች
#እንወርሳለን
#እናጠምቃለን
#እንበዛለን::
‎እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል በዚያን ቀን እግዚአብሔር አንድ ስሙም አንድ ይሆናል ትንቢተ ዘካርያስ 14፡9

1 month ago | [YT] | 377

Apostolicway

አመታዊ የወጣቶች ኮንፍረንስ

በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን
የአዲስ አበባ ሰበካ አመታዊ የወጣቶች ኮንፈረንስ እንኳን አደረሳችሁ።

ነሐሴ 1-3 በሚካሄደው በዚህ ታላቅ ኮንፈረንስ ተገኝተው የረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በክብር ተጋብዘዋል።

በዚህ ኮንፈረንስ
• የማለዳ ጸሎት
• የማለዳ ትምህርት
• ዝማሬና በተጋበዥ ኳይሮች የሚቀርብ መስዋዕት
• እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል በተወዳጅ የእምነት አባቶቻችንና ወጣት አገልጋዮች ይቀርባል።

ብቻውን የሆነው ጌታ ኢየሱስ በክብር ይመለካል፣ ልጆቹንም በታላቅ በረከት ይባርካል።

ከነሐሴ 1-3/2018 ዓ.ም
በእናት አጥቢያ ጎፋ ጸሎት ቤት

ኑ አብረን እንባረክ!
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

1 month ago | [YT] | 280