ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

"የልባሞች መብራት"


ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

💦 ውኃ ወደ ወይን!🍷
​"ሙሽራው ሙሽራውን ይመስላል፤ ሰርገኛውም ሰርገኛውን ይመስላል" እንዲሉ ሊቃውንቱ
🙏 ዛሬ ሰማያዊው ሙሽራ ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ ተገኝቶ የሰርጉን ቤት ባረከ።
​ታቦታችንን በክብር ሸኝተን፣ የቅዱስ ሚካኤልን ጥበቃ እና በረከት አግኝተናል ።
​በዚህ በዓል፦
​"አንተስ መልካሙን ወይን እስከ አሁን አቆይተሃል" (ዮሐ. ፪፥፲)
​ተብሎ እንደተጻፈ
እግዚአብሔር ለሕይወታችን መልካሙን ነገር ያቅርብልን። የጎደለው ይሙላ፣ የተበላሸው ይስተካከል፣ የጠፋው ይገኝ።
​መልካም የቃና ዘገሊላ እና የቅዱስ ሚካኤል በዓል!
ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
ጥር 12/2018 ዓ.ም ቦሌ ገርጂ

2 days ago | [YT] | 2,363

ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

6ቱ ቁልፎች

5 days ago | [YT] | 36

ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው

6 days ago | [YT] | 55

ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
​የአብ፣ የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ቸርነትና ምህረት በሁላችንም ላይ ይሁን። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ ይሁንልን።
#ኦርቶዶክስ #ቅድስት_ሥላሴ #Tewahedo #EthiopianOrthodox #Selassie

1 week ago | [YT] | 1,759

ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

🌟 እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የግርዘት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!🌟
​"ተገዝረ በሥጋ፤ ከመ ይፈጽም ሕገ..."
(ሕግን ይፈጽም ዘንድ በሥጋ ተገዘረ)
​ዛሬ ዓመታትን ያዘመነ፣ ሕግን የሠራ አምላክ፤ "ሕግን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም" ብሎ የተናገረውን ቃል በተግባር ያጸናበት ልዩ ቀን ነው። በተወለደ በስምንተኛው ቀን እንደ ኦሪት ሥርዓት ተገዘረ፤ አስቀድሞም በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ለእናቱ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እንደነገራት ቅዱስ ስሙ "ኢየሱስ" (መድኃኒት) የተባለበት ታላቅ ቀን። (ሉቃ ፪፥፳፩)
ለእኛም ​የዛሬው በዓል፡-
🕊️ የፈጣሪያችንን ፍጹም ትህትና የምናይበት፣
🕊️ ስሙን ጠርተን የምንቀደስበት፣
🕊️ በረከት የምናገኝበት ዕለት ነው።
​ የጌታችን የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታው ቸርነቱ ለሁላችንም ይደረግልን፣በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር ይሁንልን!
​መልካም በዓል! 🌼
#በዓለ_ግዝረት #ኢየሱስ_ክርስቶስ #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #EOTC #Ethiopia

1 week ago | [YT] | 1,645

ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

እንኳን ለነባቤ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
ምስጢር ተገልጦለት እንደ ንስር ወደ ሰማይ በመምጠቅ "ቃል ስጋ ሆነ" ብሎ ያበሰረን የጌታ ወዳጅ፣ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን በአደራ የተቀበለ፣ በአራቱ ወንጌላውያን ዘንድ በንስር የሚመሰለው የአቡቀለምሲስ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ዓመታዊ በዓል ነው።
ምልጃ ጠብቆቱ ቃልኪዳኑ አይለየን
​የፍቅሩ ተካፋዮች ያድርገን።
​በረከቱ በቤታችን ይግባ።

1 week ago | [YT] | 2,041

ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

ፊደል ነሽ የኛ መማሪያ

1 week ago | [YT] | 41

ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

!!! ልደተ ክርስቶስ !!!
​"ዛሬ የጊዜያት ጌታ ወደ ጊዜ ገባ፤ ከአባት ያለ እናት የነበረው ዛሬ ከእናት ያለ አባት ተወለደ።" (ቅዱስ ኤፍሬም)
​የማይታየው የታየበት፣ ሩቁ የቀረበበት፣ ንጉሡ በግርግም የተገኘበት አስደናቂ ቀን!
ውድ የቀንዲል ሚዲያ ቤተሰቦቼ ልደቱ ለሁላችንም፡-
​የተዘጋው የሚከፈትበት፣
​የጠፋው የሚገኝበት፣
​የራቀው የሚቀርብበት፣
የበረከት በዓል ይሁንልን።
ቸሩ መድኃኔዓለም ​መልካም በዓል ያድርግልን እርስዎ ለወዳጅ ዘመድዎ ሁሉ!
ስለ ተወዳጁንም እናመሰግናለን ❤

2 weeks ago | [YT] | 1,656

ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

✝️ ​ጭንቀት እያቃጠለህ ነው? እግዚአብሔር ረስቶኛል ብለህ አስበሃል?
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ማዕበል መምጣቱ አይቀርም፤ ዋናው ነገር በማዕበሉ ውስጥ ሆኖ ክርስቶስን መጥራት ነው" ይለናል።
​ዛሬ ለተሰበረ ልብ፣ ለተጨነቀ አእምሮ የሚሆን ፍቱን "መንፈሳዊ መድኃኒት" ይዘንላችሁ ቀርበናል። ጭንቀትን ወደ ጸሎት እንዴት መቀየር እንዳለብን እና የእግዚአብሔርን ዝምታ እንዴት መረዳት እንዳለብን ሊቃውንቱ ይመክሩናል።

​👇 ሙሉ ትምህርቱን እዚህ ይከታተሉ፡

https://youtu.be/nCPmRsU8SCI?si=USoEr...

​ሼር በማድረግ ለተጨነቁ ወገኖች ያድርሱ!
#OrthodoxTewahedo #Sibket #EOTC #Faith #Hope

2 weeks ago | [YT] | 1,143

ቀንዲል ሚዲያ - Kendil Media

የገና አባት እና X - mass

2 weeks ago | [YT] | 65