እንኳን በደህና መጡ
Welcome
ወደዝህ ቻናል ስቀላቀሉ
👉ምክረ አበዉ በማያሰለች በአጭሩ
👉 መንፈሳዊ ድራማ
👉 ለወጣቶች የምሆን አጫጭር ትምህርቶች
👉የህብረት መዝሙሮችን
👉የሰርግ መዝሙሮችን
👉ወረብ ወይም ያሬዳዊ ዝማሬዎችን
✝️በአጫጭር መልኩ የምቀርብበት ብቸኛዉ ቻናላቹ ነዉ
✝️When you join your channel
👉 The advice is short and tireless
👉 Spiritual drama
👉 Short lessons for young people
Union songs
👉 wedding songs
👉 Wereb or Yaredawi chants
✝️ It is the only channel where I can be presented in a short form
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም
ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው ። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና።
እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች ። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ ።
ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ።
ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም በመኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲፈጸምላት እርሷ ለእግዚአብሔር የተሰጠች የስዕለት ልጅ ናትና ለሚጠብቃት ይሰጧት ዘንድ ካህናት እርስበርሳቸው ተማከሩ በሴቶች ላይ የሚደርስ በርሷ ላይም ይደርስባታል ብለው ስለፈሩ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይተዋት ዘንድ ለእርሱ ትክክል መስሎ አልታያቸውም ስለዚህም ሊጠብቃት ለሚገባው በእርሷ ላይ እጮኛ ሊአኖሩ ወደዱ።
ከዚህም አስቀድሞ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልጄ ማርያም ሆይ አንቺ እንዳደግሽና ለአካለ መጠን እንደደረስሽ ዕወቂ ልትታጪ ትወጃለሽን እግዚአብሔርን የሚፈራ መልካም የሆነ የተባረከ ጐልማሳ እንፈልግልሽን ወይም በሕይወትሽ ዘመን ሁሉ በቤተ መቅደስ ተቀምጠሽ እግዚአብሔርን ልታገለግዪው የምትሺ ከሆነ በሴቶች ላይ የሚደርሰው በሚደርስብሽ ወራት ወደ ቤተ መቅደስ ደጅ ከመግባት ትጠበቂ ዘንድ በኦሪቱ የተጸፈውን የርግማን ሥርዓት በአንቺ ላይ እንሠራለን አላት ።
ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋዩ በፊታችሁ ነኝ አባትና እናት የሉኝም ስሙ ቡሩክ ምስጉን ከሆነ ከእግዚአብሔር በታች በእናትና አባት ፈንታ እናንት ናችሁና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደምታውቁ አድርጉ ብላ መለሰች።
ካህናቱና ማኅበሩም ሁሉ ዘካርያስን ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ ስለዚች ብላቴና ማርያም ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት ዘካርያስም ገብቶ ሲጸልይ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ ወጥተህ ከዳዊት ወገን ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሁሉ ወንዶች ሰብስብ የየአንዳንዱንም በትር ከስሙ ጋር ውሰድ ወደ ቤተ መቅደስም በምሽት አግብተህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይበት በነጋ ጊዜም በትሮቻቸውን አውጣ እግዚአብሔርም በበትሩ ላይ ምልክት ለገለጠልህ ለዚያ ሰው ማርያምን ተቀብሎ ሊጠብቃት ይገባዋል።
ካህኑ ዘካርያስም ወጥቶ አንድነት ለተሰበሰቡት ሕዝብ የእግዚአብሔር መልአክ የነገረውን ነገራቸው በዚያንም ጊዜ ከዳዊት ወገን ጐልማሳም ቢሆን ሽማግሌም ቢሆን ሚስቱ የሞተችበት ሁሉ በኢየሩሳሌም ወደአለ ቤተ መቅደስ ይሒድ እያሉ ዓዋጅን ዙረው የሚናገሩ በእስራኤል አገር ሁሉ ላከ ።
ከዳዊት ወገን የሆነ ጠራቢው ዮሴፍም በሰማ ጊዜ በትሩን ይዞ ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ካህኑ ዘካርያስም የሁሉንም በትሮች ተቀብሎ ስማቸውን በላያቸው ጻፈ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሆነ ዘካርያስም በትሮችን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ውጭ ቁመው ይጸልዩ ነበር ዘካርያስም ጸሎቱን በፈፀመ ጊዜ ለየአንዳንዱ በትራቸውን አውጥቶ ሰጠ ጠራቢው ዮሴፍም በትሩን ሊቀበል በቀረበ ጊዜ ከእርሷ ነጭ ርግብ የመሰለች ተገለጠች እየበረረችም ሒዳ በጠራቢው ዮሴፍ ራስ ላይ ተቀመጠች ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ አይተው እጅግ አደነቁ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
ዘካርያስም ዮሴፍን ዮሴፍ ሆይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እንደ ተናገረ ድንግል ማርያምን ወደ ቤትህ ወስደህ ጠብቃት አለው ዮሴፍም ቅድስት ድንግል ማርያምን ከካህናት እጅ ተቀበላት በእርሱም ዘንድ ኖረች ። ከዚህም በኋላ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ስለ እግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ሁኖ ስለመወለዱ በዮሴፍ ቤት አበሠራት።
1 week ago | [YT] | 486
View 0 replies
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
ምድራዊዋ እናቴ ለግዜዉ ነዉ ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነዉ አረ ስንቱን ላዉራ
🥰😍🥰🥰🥰🥰
3 weeks ago | [YT] | 842
View 8 replies
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
ክብር ለሚገባዉ ክብርን እንሰጣለን
ንጉስ ለወደደዉ እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለም ለምድር ሹማምንት
🥰😍🥰😍🥰😍😍😍
የመላክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን ይማረን
1 month ago | [YT] | 1,008
View 13 replies
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
ጻዲቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ከክፉ ሁሉ ይጠብቁን
ምልጃ ጸሎታቸዉ አይለየን
ሀገራችንን ሀይማኖታችንን ከክፉ ሁሉ ይጠብቁልን
አሜን
1 month ago | [YT] | 811
View 6 replies
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
ሰማዕተ እየሱስ የእዉነት ምስክር
ሄያዉ ነዉ በሰማይ ብጹዕ ነዉ በምድር
ድራጎንን በጦር ወግቶ ገደለና
ከሞት አፍ አዳነን ጊዮርጊስ ደረሰና
🥰😍🥰😍🥰😍😍🥰😍🥰
ሰማዕቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን 🙏🙏🙏
1 month ago | [YT] | 612
View 11 replies
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
ውድ ኦርቶዶክሳዊያን እንኳን
ለበዓለ ደብረ ቁስቋም አደረሳችሁ
« አንቺ የሰላም መፍሰሻ
አንቺ የደስታ መገኛ ሆይ፥
ተመለሽ ሰላምን እናይብሽ
ዘንድ ተመለሽ 🙏 »
ወይናችን እንዲያፈራ፤
አበባም በምድራችን ላይ
እንዲታይ በመርከቧ ውስጥ
ያለን እኛ ልጆችሽ ምድርን
እንድንወርሳት ሱላማጢስ
ሆይ ተመለሽ
1 month ago | [YT] | 404
View 2 replies
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
መዳኒአለም ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን ። ሁላችንንም በሰላም ወተን በሰላም ያስገባን
1 month ago | [YT] | 985
View 11 replies
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
እመብርሃን እመብርሃን እመአምላክ እመአምላክ ድንግል ድንግል ቅድስት ቅድስት እመብዙሀን አመብዙሀን ንፅሂት ንፅሂት ማርያም ማርያም፤
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
አማልጂኝ እናቴ
እኔ በራሴ ምን አቅም አለኝ ፤
በደሌ ገኖ እየተታወሰኝ ፤
ክፋቴ ገኖ እየተቃወመኝ፤
የኔው ህሊና እየተካሰሰኝ፤
ምን እረፍት አለኝ፤
የቱ ቁም ነገር የቱ ስራ ነው
ከእግዚአብሔር ፊት እኔን ሚያቆመኝ፤
ምልጃሽ ካልሆነ የሚደግፈኝ፤
ከድካም ሀጥያት የሚያሳርፈኝ፤
ያ ቃልኪዳንሽ ኔን ባያተርፈኝ፤
የኔው ለራሴ መቼ ተረፈኝ።
1 month ago | [YT] | 940
View 9 replies
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
እንኳን ለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን 🥰😍🥰😍
1 month ago | [YT] | 584
View 3 replies
Habta Tube ሀብታ ቲዩብ
👉"ኢየሱስም፦ እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ . . . አለው።"
- ዮሐ. 21፥22
👉"በዚችም ቀን የታላቁና የከበረው አባታችን አረጋዊ ዘሚካኤል የሚባለው መታሰቢያው ነው . . . በእግዚአብሔር ቸርነት እንደ ሄኖክና እንደ ኤልያስ ከሞት ገጽ ተሰወረ።"
- ስንክሳር ዘጥቅምት 14 ቁጥር 53-56
#ለአቡነ #አረጋዊ #የተሰጣቸው #ቃል #ኪዳን!
"ጌታችን በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ቃል ኪዳን ሰጠው ዳግመኛም ጸሎትህ እነሆ በኔ ዘንድ ደርሶ ተሰምቷል።
ስለዚህም ከድካም ወደዕረፍት ከኀዘን ደስታ ወዳለበት ከኃሣር ወደክብር በታላቅ ደስታ እወስድህ ዘንድ ወደአንተ መጥቻለሁ አለው።
የዚህን የሀላፊውን ዓለም ክብር ስለናቅህ በመንግስተ ሰማያት የማያልፈውን የማይጠፋውን ክብር አቀዳጅሃለሁ።
በዚህ ዓለም የሐሩን ልብስ የወርቅና የብሩን ጌጥ እንደናቅህ እኔ አይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን አለብስሃለሁ አስጌጥሃለሁ።
ከትውልድ ሀገርህ ወጥተህ በባዕድ አገር ስለኖርክ እኔ ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን እሰጥሃለሁ የሚያልፉ የሚፈርሱ የዚህን ዓለም ቤት ንብረት ስለናቅህ የማይፈርስ የማያልፍ የሕይወት ቤት እኔ እሰጥሃለሁ።
መታሰቢያህን ያደረገ በጸሎትህም የተማመነውን ሁሉ እኔ በመላእክት ፊት ሞገስን ባለሟልነትን እሰጠዋለሁ።
በእውነተኛ ሃይማኖት ሁኖ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈ ያጻፈ የተረጎመ እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ።
መታሰቢያህ በሚደረግበት ዕለት የራበውን ያጠገበ የጠማውን ያጠጣ እኔ የሕይወት እንጀራ አበላዋለሁ የሕይወት ጽዋም አጠጣዋለሁ።
በዓልህ በሚከበርበት ዕለት ለራበው ምሳውን ያበላ እኔ በምሳሐ ደብረ ጽዮን የምሳ ግብዣ አደርግለታለሁ።
በስምህ በተሠራው ቤተ መቅደስ ውስጥ የጸለየ የለመነ ፈጥኜ ጸሎቱን እሰማዋለሁ ልመናውንም እቀበለዋለሁ ቤተ ክርስቲያንህንም ለሠራ ዐሥራ ሁለት የብርሃን አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ።
የገድልህን መጽሐፍ በመታመን በንጽሕና አድርጎ በቤቱ ያስቀመጠ ወረርሽኝ በሽታ ወይም ቸነፈር በቤቱ አይገባም ድንገተኛም የሰውና የእንስሳ ሞት አይደርስበትም የእህል ችግርም አይኖርበትም።
በጥቡዕ ልብ ሆኖ የገድልህን መጽሐፍ የሰማ ያለስንፍና በፍጹም መታመን የንባቡን ኃይለ ቃል የሰማ እኔ ለችግሩ ሁሉ ፈጥኜ እደርስለታለሁ።
ለቤተ ክርስቲያንህ መባ ያገባ ዕጣን ወይም ቅብዓ ሜሮን ወይም ዘይት የሰጠ እኔ በሰማያዊት መንግሥቴ አስገባዋለሁ።
ንጉሥም ቢሆን ለቤተ ክርስቲያንህ የሐር መጎናጸፊያ ቢሰጥ በዓልህ በሚከበርበት ዕለት ቢያከብር እኔ በመንግሥቴ አከብረዋለሁ በጠላቱም ላይ ድልን አቀዳጀዋለሁ ከመኳንንቱ ከመሳፍንቱ ጋር ሰላምን እሰጠዋለሁ በምድርም ላይ ዘመኑን ወይም ዕድሜውን አረዝምለታለሁ።
ከሁሉም ይልቅ የሞት ጥላ አያርፍብህም መልአከ ሞትም ሊያስደነግፅህ አይችልም እንደ ነቢያቶቼ ኤልያስና ሄኖክ ትሠወራለህ እንጂ።
በቡሩካን እጆችህ የቀበርካት እናትህ ዕድናንም በትንሣኤ ሕይወት እስካስነሣት ድረስ መቃብሯን አፍርሶ ሌላ ሰው እንዳይቀበርበት ወይም ለማንም እንዳይታይ እንደ እንበረም ልጅ እንደሙሴ መቃብር ይሰወራል።
ይህቺን ቤተ መቅደስህንም ታላቅና የተከበረች አደርጋታለሁ የበቁ የደጋግ ነገሥታትና ጳጳሳት የመቃብራቸው ወይም የማረፊያቸው ቦታ ትሆናለች።
ጌታችንም ይህን ቃል ኪዳን በሰጠው ጊዜ ክቡር አባታችን አቡነ አረጋዊ ጌታችንን አቤቱ በፊትህ ሞገስ አግኝቼስ ከሆነ እናገር ዘንድ ይፈቀድልኝ አለው።
ጌታም ወዳጄ አረጋዊ ሆይ ፈቅጄልሃለሁ ተናገር ከኔ የምትፈልገውንም ሁሉ ጠይቅ ወይም ለምን አለው።
ከዚያም አባታችን አቡነ አረጋዊ ይህን ሁሉ ለሰጠኸኝ እስከ ዘላለሙ ድረስ ስምህ የተመሰገነ የጌትነትህም ክብር የተባረከ ነው ብሎ አመሰገነ።
አሁንም ጌታ ሆይ መታሰቢያየን ያደረገ የገድሌን መጽሐፍ የጻፈ በጸሎቴ የተማመነ እስከ ስንት ትውልድ ድረስ ትምርልኛለህ አለው።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እስከ ዐሥራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አለው።
አባታችን አቡነ አረጋዊም አቤቱ ይህች ቦታ የነገሥታት የጳጳሳት የክቡራን መኳንንትና መሳፍንት ብቻ መቀበሪያ ሁና አትቅር ነገር ግን ለተገፉ ለነዳያን አባት እናት ለሞቱባቸው ለዕውራንና ለሐንካሳን መጠጊያ ትሆን ዘንድ ማንኛውም ግለሰብ ይቀበርባት እንጂ እኔ በዚች አገር እንግዳና ስደተኛ ነኝና አለው።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የተመሰገንህ አረጋዊ እንደ ቃልህ ይደረግልህ አለው።
አባታችን አቡነ አረጋዊም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አቤቱ ከሩቅ ወይም ከቅርብ መጥተው ንስሐ ሳይገቡና በድንገተኛ ሞተው በዚች በአፀደ ቤተ ክርስቲያኔ የተቀበሩትን ሁሉ ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው አለ።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳንስ በተራራው ጫፍ ላይ የተቀበረ ይቅርና ከተራራው ሥር እንኳ ቢሆን ይልቁንም በስምህ የተሰየመ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ በዚያ የተቀበረው ኃጢአቱ ይሠረይለታል እነዚህንም ሁሉ ዓሥራት አድርጌ ሰጠሁህ አለው።
አባታችን አቡነ አረጋዊም አቤቱ ይህችን ቤተ መቅደስና በውስጡዋም የሚኖሩትን ባርክ አለው።
መድኃኒታችንም ይህች ቤተ መቅደስህ የተባረከች የተቀደሰች ትሁን በውስጧም ሰው አይታጣ መብራቷ አይጥፋ ሥጋዬና ደሜ በውስጧ በተዘጋጀ ጊዜ ልምላሜ ሙቀት ያልተለየው የሠመረ በፊቴም ተቀባይነት ያለው ይሁን አለው።
አባታችን አቡነ አረጋዊም መልሶ አቤቱ ይህችን መንፈሳዊ ማኅበር ልጆቼንና ቅዱሳኖቼንም ሁሉ ባርክ አለው።
ይህች ማኅበር የተባረከች ትሁን የችግረኞች መጠጊያ የተራቡ የሚጠግቡባት የታረዙ የሚለብሱባት ወይም ለተራቡት ምግብ ለተራቆቱት ልብስ ትሁን አለው።
እሊህ ቅዱሳን ልጆችህም እልፍ አእላፋት ይሁኑ እንደባህር አሸዋ እንደሰማይ ከዋክብትም ትውልዱ ነገዱ እንደተስፋፋ ዘሩም እንደበዛ እንደ ያዕቆብ ልጆች የበዙ ይሁኑ።
ድንገተኛ በሽታ መቅሠፍት ሰውነትን የሚያዝግ የሚያጠወልግ ሕማም ወደነሱ አይቀርብም።
አባታችን አቡነ አረጋዊ አቤቱ ይህችን የማድርባትን በዓቴንና ከአንተም ጋር ቆሜ ቃል ኪዳን የተቀበልኩባትን ቦታ ባርክ።
ይልቁንም ይህቺ እግርህ ከቆመባት መሬት አፈሯን ወስደው በመቀባት መድኃኒት ትሆናቸውና ወይም ከሕመማቸው ይፈወሱ ዘንድ ባርካት አክብራትም።
ሕመም ያለበት ቢኖር ፈጥኖ ይወገድለት በፍጹም መታመን በአንገቱ ላይ እምነቱን ቢአሥር ከክፉ ደዌ ከሚያንቀጠቅጥ ወይም ከሚያንዘፈዝፍ በሽታ ይድን ዘንድ መሬቱን ወይም እምነቱን በተቀባ ጊዜ በሱ ላይ ድንቅ ድንቅ ተአምር ተፈጽሞ ከሕመሙ ነፃ ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን በማለት አባታችን አቡነ አረጋዊ ለመነ።
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይሁን ይደረግልህ በማለት በማይታበል ቃሉ ቃል ኪዳን ገባለት።"
+++አሜን+++
ምንጭ፦
ገድለ አቡነ አረጋዊ፤ ዘሰኔ፤ ምዕራፍ 2፤ ከቁጥር 1 – 36፤ 1978 ዓ.
1 month ago | [YT] | 294
View 1 reply
Load more